loading
ፈረንሳይ በምስራቃዊ ሜዲትራንያን አካባቢ ወታደራዊ ሀይሏን ለማጠናከር እያሰበች ነው ተባለ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ7፣ 2012 ፈረንሳይ በምስራቃዊ ሜዲትራንያን አካባቢ ወታደራዊ ሀይሏን ለማጠናከር እያሰበች ነው ተባለ:: ፓሪስ ሁለት ተዋጊ ጀቶችን ጨምሮ የባህር ሃይል እዝ ወደ ቀጠናው ለመላክ መዘጋጀን ተናግራለች፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፈረንሳይ ይህን የምታደርገው ቱርክ ወደስፍራው የጦር መርከቦችን መላኳን ተከትሎ በአንካራ እና በአቴንስ መካከል ውጥረት በመፈጠሩ ነው ተብሏል፡፡ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአካባው የተፈጠረው ሁኔታ በሁለቱ ሀገራት መካከል […]

ጀርመን ለሊባኖስ የምታደርገው ድጋፍ ገሀሪቱ ከምታርገው ሪፎርም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገለፀች::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ7፣ 2012 ጀርመን ለሊባኖስ የምታደርገው ድጋፍ ገሀሪቱ ከምታርገው ሪፎርም ጋር የተያያዘ መሆኑን ገለፀች:: የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ሄይኮ ማስ ድጋፉን አስመልክተው ሲናገሩ ቤይሩት ከደረሰባት አደጋ እንድታገግም ብቻ ሳይሆን ወደፊት ለሚጠብቃት የፖሊሲ መሻሻያ ጭምር ነው የምንደግፋት ብለዋል፡፡ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ጀርመን በአደጋው ከባድ ጉዳት ለደረሰባት ቤይሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የ1.18 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በሊባኖስ ቀይ […]

የፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ለምርጫ በእጩነት መቅረብ ኮትዲቯራያዊያንን አስቆይቷል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ08፣ 2012የፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ለምርጫ በእጩነት መቅረብ ኮትዲቯራያዊያንን አስቆይቷል:: ፕሬዚዳንቱ ለሶስተኛ ጊዜ እንዲወዳደሩ የሀገሪቱ ህገ መንግስት ስለማይፈቅድላቸው ቦታውን ለሌሎች ይልቀቁ የሚል ጥያቄ ይዘው ነው ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት፡፡ ዛሬ ለተቃውሞ የወጣነው ህግ ሲጣስ እያየን ዝም አንልም ብለን ነው ያሉት ተቃዋሚዎቹ መላው የኮትዲቯር ህዝብ ተቃውሞውን እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የቀድሞውን የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት ሎረን ባግቦን ጨምሮ […]

ኒው ዚላንድ የኮሮናቫይስን ለወራት ተቆጣጥራ ከቆየች በኋላ አዲስ ታማሚዎችን ማግኘቷ ትልቅ ስጋት ፈጥሮባታል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ08፣ 2012ኒው ዚላንድ የኮሮናቫይስን ለወራት ተቆጣጥራ ከቆየች በኋላ አዲስ ታማሚዎችን ማግኘቷ ትልቅ ስጋት ፈጥሮባታል:: ሀገሪቱ ከ100 ቀናት በላይ ዜጎቿ ከኮቪድ19 ነጻ ሆነው የከረሙ ሲሆን ሰሞኑን አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል ተብሏል፡፡ከሶስት ቀናት ባልበለጠ ገዜ የታማሚዎቹ ቁጥር ወደ 17 ከፍ ማለቱ መሰማቱን ሲ ጂ ቲ ኤን  በዘገባው አስነብቧል፡፡ የኒው ዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደርን የበሽታው […]

እጅ ንክኪ ነፃና ለአጠቃቀም ቀላል የእጅ ማስታጠቢያ የፈጠራ ውድድር ምዝገባ ተጀመረ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ08፣ 2012 ከእጅ ንክኪ ነፃና ለአጠቃቀም ቀላል የእጅ ማስታጠቢያ የፈጠራ ውድድር ምዝገባ ተጀመረ::ውድድር በዩ. ኤስ. ኤድ ትራንስፎርም ዋሽ እና ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ትብብር ነዉ የተዘጋጀዉ፡፡ የውድድሩ አዘጋጆች በሰጡት መግለጫ ማንኛውም በቴክኒክና ሞያ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችም ይሁኑ በቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ የሚሰሩ ግለሰቦች መወዳደር ይችላሉ፡፡በሚኒስቴሩ የጤና አጠባበቅ ምክትል ዳይሬክተር አቶ አሽረፈዲን ዮያ እንደተናገሩት ህብረተሰቡ በንክኪ የሚተላለፉ […]

ሶማሊያ ሞቃዲሾ ከተማ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 17 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 11፣ 2012 ሶማሊያ ሞቃዲሾ ከተማ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 17 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል:: የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ኢስማኤል ሙክታር ኦማር እንዳሉት ጉዳቱ የደረሰው የአልሸባብ ታጣቂዎች በአንድ ሆቴል በከፈቱት ጥቃት ነው፡፡ ቃል አቀባዩ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ጥቃቱን ያደረሱት አራቱም የአልሸባብ ታጣቂዎች በተኩስ ልውውጡ ወቅት በመንግስት የፀጥታ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ከሶስት ሰዓታት በላይ በፈጀው የተኩስ […]

ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ አቋርጠውት የነበረውን ድርድር ለመጀመር ተስማሙ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 11፣ 2012ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ አቋርጠውት የነበረውን ድርድር ለመጀመር ተስማሙ:: የሱዳን የውሃ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ረዘም ካለ ውይይት በኋላ ሶስቱም ሀገራት በየራሳቸው ያዘጋጇቸውን የውይይት ሀሳቦች በማስታረቅ ከማክሰኞ ጀምሮ ለመደራደር ተስማምተዋል ብሏል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በሳምንቱ መጨረሻ ካርቱም ላይ ተገናኝተው የተዋያዩት የግብፅ እና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቀጣዩ የሶስቱ ሀገራት ድርድር ፍሬያማ እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ ሁለቱ […]

የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀደማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ አሜሪካን ከችግር የመታደግ አቅም የላቸውም አሉ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀደማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ አሜሪካን ከችግር የመታደግ አቅም የላቸውም አሉ:: ቀዳማዊት እመቤቷ ፕሬዚዳንቱ ውጤት ያለው ስራ ሰርቶ ለማሳየት ከበቂ በላይ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል ግን አንድም ፍርያማ ተግባር አላከናወኑም ብለዋል፡፡ ትራምፕ ለሀገራችን ትክክለኛው መሪ አይደሉም ያሉት ሚሼል አንድ ቀላል ምሳሌ ብናነሳ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በአሜሪካ የተከሰተውን ሁኔታ ማረጋጋት አልቻሉም […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ:- – ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስትር – ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ – ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር – ታከለ ኡማ፤ የማዐድንና ነዳጅ ሚኒስትር – ተስፋዬ ዳባ፤ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ – ዮሐንስ ቧያለው፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግነኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት […]

በሊባኖስ የሚኖሩ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ፈቃድ አገኙ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 በሊባኖስ የሚኖሩ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ፈቃድ አገኙ:: በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ቆንላ ጀነራል ተመስገን ዑመር ጽሕፈት ቤቱ በሊባኖስ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ዜጎች መረጃዎች ለአገሪቱ ኢምግሬሽን ጉዳዮች መሥሪያ ቤት አስገብቶ እንደነበር ለኢዜአ ገልጸዋል። በዚሁ መሠረት የኢሚግሬሽን ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ፈቃድ […]