loading
የሰዎች ያለአግባብ መታሰር አሳስቦኛል- ኢሰመጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ከህግ አግባብ ውጭ ዜጎችን ማሰር እንዲቆም ጠየቀ፡፡ ጉባኤው አስቸኳይ ባለው መግለጫው የብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ጠቅሶ የተያዙበት መንገድ ህጋዊ አለመሆኑንና ቤተሰቦቻቸውን ለእንግልት መዳረጉን አብራርቷል ጄኔራሉ ከሰው ጋር ቀጠሮ አለኝ ብለው ከቤታቸው እንደወጡ ሳይመለሱ መቅረታቸውንና ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ለማወቅ በርካታ ስፍራዎችን ማዳረሳቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ በመጨረሻም ባህርዳር ከተማ […]

ዳሸን ባንክ ሁለተኛውን ዙር የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ስልጠና ውድድር መርሃ ግብር በድሬዳዋ ከተማ ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 ዳሸን ባንክ ሁለተኛውን ዙር የዳሸን ከፍታ የስራ ፈጠራ ስልጠና ውድድር መርሃ ግብር በድሬዳዋ ከተማ ይፋ አደረገ:: ባንኩ ማኅበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ፕሮጀክቶችን ነድፎ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን በዚህም በርካቶች ተጠቃሚ ሆነዋል ተብሏል፡፡ የባንኩ የማርኬቲንግ ኮምዩኒኬሽን ከፍተኛ ስራ አስኪያጅ ስለሺ ይልማና የዳሸን ባንክ የድሬዳዋ ቀጠና ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ኑሪት መሀመድ […]

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቻይና በታይዋን ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ ሀገራቸው ጣልቃ እደምትገባ አስጠነቀቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቻይና በታይዋን ላይ ጥቃት የምትሰነዝር ከሆነ ሀገራቸው ጣልቃ እደምትገባ አስጠነቀቁ፡፡ ባይደን በእስያ ጉብኝታቸው ጃፓን ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቤጂንግ በታይዋን ላይ አንዳች ጥቃት ለማድረስ ከሞከረች ሀገራቸው የሃይል እርምጃ እንደምትወስድ ነው የተናገሩት፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ዋሽንግተን ታይዋንን ከቻይና ጥቃት የመጠበቅ ሀላፊነት አለባት ብለዋል፡፡ከጃፓኑ ጠቅላይ […]

በድብቅ ለህወሓትሊደርስ የነበርው ገንዘብ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 ለህወሓት ሊደርስ ነበር የተባለ 3 ሚሊዮን ብር በቆቦ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋለ:: በቆቦ ከተማ ለአሸባሪው ህወሓት ሊደርስ እንደነበር የተጠረጠረ 3 ሚሊዮን ብር በቆቦ ከተማ ህዝብ እና በከተማው ፓሊስ እና ሕዝባዊ ሚሊሻ ሰራዊት አማካይነት በትናንትናው እለት መያዙ ተነግሯል ተጠርጣሪዎቹ ገንዘቡን ደብቆ ለማሸጋገር የተጠቀሙበት መንገድ ያልተጠበቀ ቢሆንም፥ የቆቦ ከተማ ህዝብ እና የፀጥታ […]

የሶማሊያው አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን በይፋ ተረክበው ስራ ጀመሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 የሶማሊያው አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን በይፋ ተረክበው ስራ ጀመሩ፡፡ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ፋርማጆ በስልጣን ርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግግር አዲሱ መሪ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት ፈታኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዓመታት በአልቃኢዳ መራሹ አልሸባብ የምትታመሰው ሶማሊያ በቅርቡ ያጋጠማት የድርቅ አደጋ ሌላው ራስ ምታት ነው ብለዋል ፋርማጆ፡፡ እናም ይህን ሁኔታ ለማስተካከል ፕሬዚዳንት ሀሰን ሸይክ […]

አልሸባብ በአዲስ አበባ ሊፈጽም የነበረው የሽብር ተግባር መክሸፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 አልሸባብ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ ሊፈጽም የነበረው የሽብር ተግባር መክሸፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ አልሸባብ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ ሊፈጽም የነበረው የሽብር ተግባር መክሸፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ዘመቻ ነው የሽብር ቡድኑን ተግባርማክሸፍ የተቻለው ተብሏል። ጉዳዩን አስመልክቶ በጋራ በሰጡት መግለጫም ሸኔን ጨምሮ የህወሓት ተላላኪዎች በመዲናዋ […]

የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በተደረገው ጥረት መንግስት 124 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በተደረገው ጥረት መንግስት 124 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ። የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጀው የነዳጅ ግብይት ሪፎርም ትግበራ ማስተዋወቂያ መድረክ በሐዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ በመድረኩ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እንዲሁም የክልሉ […]

በሴኔጋል በአንድ ሆስፒታል በተከሰተ የእሳት አደጋ የ11 ህፃናት ህይወት ማለፉ በሀገሪቱ ከፍተኛ ሀዘን ፈጥሯል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 በሴኔጋል በአንድ ሆስፒታል በተከሰተ የእሳት አደጋ የ11 ህፃናት ህይወት ማለፉ በሀገሪቱ ከፍተኛ ሀዘን ፈጥሯል ተባለ፡፡የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በጨቅላ ህፃናቱ ላይ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ በሰማሁ ጊዜ ልቤ በሀዘን ተሰብሯል ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት መልእክትም ለህፃናቱ ወላጆችና ለመላው ቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ በማለት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡ የጤና ሚኒስትሩ አብዱላየ ዲዩፍ ሳር በበኩላቸው […]

በባንኮች ላይ እተፈጸመ ያለው የማጭበርበር ወንጀል አሳሳቢ ሆኗል-ፍትህ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 ፍትህ ሚኒስቴር በጥናት ደረስኩበት ያለውን በባንኮች ላይ የተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ይፋ አደረገ፡፡ ሚኒስቴሩ በጉዳዩ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት በባንኮች ላይ ከ370 ቢሊዮን ብር በላይ የማጭበርበር ወንጀል ሙከራ ተደርጓል ብሏል። በዚህም በተለያዩ ባንኮች ከ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ምዝበራ እንደተፈጸመባቸው ነው የተነገረው፡፡ […]

በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የተመረቀው ማዕከሉ ቀድሞ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ እንደሚያሳድገው ተነግሯል፡፡ ይህም ለኩላሊት ህመምተኞች እፎይታን ይሰጣል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕከሉን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ባዩት […]