loading
በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ኦዲት እና ምዝገባ ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።

አዲስ አበባ፣ሐምሌ30፣ 2012 በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ኦዲት እና ምዝገባ ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።ምዝገባው ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል ያለመ መሆኑንም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ክንቲባ ኢንጂር ታከለ ኡማ የምዝገባ እና ኦዲት ሂደቱን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል። ከነገ ጀምሮ መካሄድ የሚጀምረው የምዝገባ እና ኦዲት ሥራ ከመሃል ከተማ […]

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያገኙ እየሰራሁ ነው አለ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ1፣ 2012 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያገኙ እየሰራሁ ነው አለ:: በሊባኖስ በደረሰዉ ፍንዳታ የ1 ኢትዮጵያዊ ህይወት ማለፉንና 9 ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ቀላልና ከባድ አደጋ እንደደረሰባቸዉ የሚኒስሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲን ሙፍቲ ገልፀዋል፡፡ በቤይሩት በሚገኙት መጠለያዎች ዉስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ግን ጉዳት እንዳልደረሰባቸዉና በጥሩ ደህንነት እንደሚገኙ ነዉ የተነገረ ሲሆን ወደ ፌት ግን ቁጥሩ ሊጨምር […]

በሱዳን የተከሰተ የጎርፍ አደጋ 10 ሰዎችን ሲገድለ ከ3 ሺህ በላይ በሚሆኑ ቤቶች ላይ ጉት አድርሷል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ1፣ 2012 በሱዳን የተከሰተ የጎርፍ አደጋ 10 ሰዎችን ሲገድለ ከ3 ሺህ በላይ በሚሆኑ ቤቶች ላይ ጉት አድርሷል ተባለ:: አደጋው የደረሰው በደቡባዊ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ብሉ ናይል ግዛት ሲሆን በስፍራው የሚገኝ ግድብ በመደርመሱ ውሃው አካባቢውን በማጥለቅለቁ ነው ተብሏል፡፡ አፍሪካ ንውስ እንደዘገበው በውሃ ሙላቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ከ300 በላይ ቤቶች መካከል 1 ሺህ 800 የሚሆኑት ሙሉ […]

በሱዳን ዳግም ግጭት ማገርሸት በምስራቃዊ ሱዳን ዳግም ባገረሸው ግጭት የ4 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ4፣ 2012 በሱዳን ዳግም ግጭት ማገርሸት በምስራቃዊ ሱዳን ዳግም ባገረሸው ግጭት የ4 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተሰማ:: የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው በፖርት ሱዳን አካባቢ የሚኖሩ የቤኒ አሚር ጎሳዎች የኑባ ጎሳዎች ላይ ጥቃት በማድረሳቸው ነው ግጭቱ የተቀሰቀሰው፡፡ ለአሁኑ ግጭት መንስኤ ናቸው የተባሉት የቤኒአሚር ጎሳዎች መሆናቸውን ያመለከተው ዘገባው ኑባዎቹ ለግዛት አስተዳዳሪያቸው ባዘጋጁት መታሰቢያ ላይ ተሰባስበው […]

የህንድ የጎርፍ አደጋ ስጋት ህንድ ውስጥ የመሬት መንሸራተት ባስከተለው አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደረሰ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ4፣ 2012 የህንድ የጎርፍ አደጋ ስጋት ህንድ ውስጥ የመሬት መንሸራተት ባስከተለው አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደረሰ:: በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በአንድ የሻይ ማሳ ላይ በደረሰው በዚህ አደጋ እስካሁን የሟቾቹ ቁጥር 43 ደርሷል ነው የተባለው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የመሬት መንሸራተት አደጋው መንስኤ በሀገሪቱ እየዘነበ ያለው ከባድ ዝናብ ሲሆን በአደጋው ሳቢያ ከ24 ሰዎች በላይ የገቡበት አልታወቀም፡፡ የሀገሪቱ […]

አንድ ባለሀብት በብርጭቆ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኬሚካል እርጭት አካሄደ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ4፣ 2012 አንድ ባለሀብት በብርጭቆ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኬሚካል እርጭት አካሄደ፡፡ባለሀብቱ ኢንጂነር መኩሪያ በየነ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል  በማሰብ  የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን በኬሚካል ሲያስረጩ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በጋራ መኖሪያ መንደሩ  ከኬሚካል ርጭቱ ጎንለጎንም የችግኝ ተከላ የተካሄደ ሲሆን፤ለእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 140  ሰራተኞችም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር ባለሀብቱ ድጋፍ […]

ህበረት ለበጎ ከቄራና ጎፋ ወጣቶች ጋር በመተባበር ለ600 ሰዎች ድጋፍ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ4፣ 2012 ህበረት ለበጎ ከቄራና ጎፋ ወጣቶች ጋር በመተባበር ለ600 ሰዎች ድጋፍ አደረገ፡፡የማእድ መጋራት ፕሮግራሙ ብዙ ወገኖች በኮፊድ 19 ምክንያት ስራ መስራት ባለመቻላቸዉ ለችግር ለተዳረጉ ወገኖች ለመድረስ የተደረገ መሆኑን የህበረት ለበጎ መስራች አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ገልጿል፡፡ ድጋፉ ከጎፋ ቄራ ወጣቶች እንዲሁም በዉጭ ሀገር ከሚገኙ ወጣቶች በተሰበሰበ 1 ሚሊዮን 35 ሺህ ብር ወጪ ደረቅ ምግቦች […]

ሁለተኛው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተካለ መርሀ ግብር ከታሰበለት ጊዜ ቀድሞ መጠናቀቁ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 6፣ 2012በመላው ሀገሪቱ የተከናወነው የሁለተኛው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከታሰበለት ጊዜ አንድ ወር ቀድሞ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የመዝጊያ ስነ ስርዓት በባህር ዳርከተማ እየተከናወነ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም በባህር ዳር ከተማ ቤዛዊትቤተ-መንግስት እየተከናወነ ባለው የመዝጊያ ስነ ስርዓት ተገኝተዋል።በስነስርዓቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ […]

የህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያዊያን ሊረባረቡ ይገባል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ7፣ 2012  የህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያዊያን ሊረባረቡ ይገባል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩይን ያሉት ሁለተኛው ሃገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ በተገኙበት ወቅት መሆኑን ነው። በፕሮግራሙ ስነሰርዓት ችግኝ በመትከል የተሳተፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የለውጡ ኃይል ወደ ስልጣን ሲመጣ የገባውን ቃል ለመፈፀም ከፍተኛ ጥርት እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በሁለተኛው […]

የህዳሴ ግድቡ ሁሉም ሥራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት እየተከናወኑ መሆናቸው ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ7፣ 2012 የህዳሴ ግድቡ ሁሉም ሥራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት እየተከናወኑ መሆናቸው ተገለፀ:: የግድቡ አጠቃላይ የሲቪል ሥራ አፈጻጸም 88 ነጥብ 5 በመቶ፤ የግንባታ ፕሮጀክቱ ደግሞ 75 በመቶ መድረሱን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ገልጸዋል። ኢንጅነር ክፍሌ እንደገለጹት ከመጀመሪያው ዙር የግድቡ ውሃ ሙሌት በኋላም የግንባታ ሥራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት እየተከናወኑ ነው። […]