loading
የጎንደር ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል በ64 ሚሊዮን ብር የተቆፈሩ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 የጎንደር ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል በ64 ሚሊዮን ብር የተቆፈሩ:: ጥልቅ ጉድጓዶች በቅርቡ አገልግሎት እንደሚጀምሩ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ።   የአስተዳደሩ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይማኖት በለጠ ለኢዜአ እንደገለጹት የከተማውን የውሀ አቅርቦት ለማሻሻል በመካከለኛ ጊዜ እቅድ ከተያዙ አምስት ጥልቅ ጉድጓዶች የሁለቱ ቁፋሮ ተጠናቋል ። ጥልቅ ጉድጓዶቹ የሚያመነጩትን ውሀ ወደ […]

የሊቢያ የሰላም ጥሪ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 29፣ 2012 ግብፅ የሊቢያ የሰላም ጉዳይ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ አቀረበች:: የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ካይሮ የትኛውንም የተኩስ አቁም ስምምነትና የሰላም ድርድር ሂደት ለመደገፍ ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡ ሽኩሪ ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳዮች ፖሊሲ ከፍተኛ ልዑክ ጆሴፍ ቦሬል ጋር በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው ይህን ያሉት፡፡ በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰው […]

የመንግስታቱ ድርጅት ማሳሰቢያ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 29፣ 2012  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻይና በሆንግኮንግ ላይ ያወጣችውን የብሄራዊ ደህንነት ህግ አወገዘ::የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ኤክስፐርቶች ለቤጅንግ በፃፉት ባለ 14 ገፅ ደብዳቤ በሆንግኮንግ ላይ የተላለፈው እስረኞችን ለማእከላዊ ቻይና አሳልፎ የመስጠት ህግ ነፃነትን የሚጋፋ ነው ብለዋል፡፡ ቻይና ይህን ህግ ዳግም ካልፈተሸችው በስተቀረ አደጋ አለው ያሉት ባለ ሙያዎቹ ህጉ ከተላለፈ ጀምሮ የተቀሰቀሰው አመፅ አንዱ ማሳያ […]

አርትስ ቴሌቭዥን በአርትስ ቨርችዋል ባዛር ለሚሳተፉ ተመልካቾቹ የመኪና ሽልማት አዘጋጀ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 29፣ 2012 አርትስ ቴሌቭዥን በአርትስ ቨርችዋል ባዛር ለሚሳተፉ ተመልካቾቹ የመኪና ሽልማት አዘጋጀ፡፡አዲስ ሱዙኪ አልቶ 2020 ሞዴል መኪናም ለሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡አርትስ ቴሌቭዥን ባዘጋጀዉ የመጀመርያዉ ቨርችዋል ባዛር እየተካሄደ ሲሆን ለተመልካቾቹ እና ሸማቾችም በየቀኑ ከሞባይል አነስቶ ተለያዩ ሽልማቶችን በየቀኑ ይሸልማል፡፡ የአርትስ ቲቪ ስራ አስፈጻሚ አዜብ ወርቁ እንደገለጹት የመኪና ቶምቦላ ሽልማቱ ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፍቃድ ያገኘ ሲሆን ከዳሽን […]

የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ለህክምና ወደ አቡዳቢ መጓዛቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2012 የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ለህክምና ወደ አቡዳቢ መጓዛቸው ተሰማ:: በቅርቡ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተባረሩት ኬታ ህክምናቸውን ለመከታተል ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች መጓዛቸውን የቀድሞው የጦር አዛዣቸው ማማዱ ካማራ ተናግረዋል፡፡ ለአስር ቀናት ያህል በወታራዊ ጁንታው ቁጥጥር ስር የነበሩት ኬታ ባማኮ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል የህክምና ተቋም የጤናቸውን ሁኔታ ሲከታተሉ […]

ህንድ በኮቪድ 19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብራዚልን በመቅደም ሁለተኛዋ የዓለም ሀገር ሆነች፡፡

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2012 ህንድ በኮቪድ 19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብራዚልን በመቅደም ሁለተኛዋ የዓለም ሀገር ሆነች፡፡ ህንድ በአንድ ቀን ብቻ ከ90 ሺህ በላይ አዲስ በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ ብራዚልን ቀድማና አሜሪካንን ተከትላ ሁለተኛ ሀገር ሆናለች፡፡ አሁን ላይ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ሁለተኛዋ ሀገር ስትሆን፤ በሟቾች […]

በሱዳን አሁንም የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ ተሰግቷል::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2012  በሱዳን አሁንም የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ ተሰግቷል:: በሱዳን የሚዘንበው ከባድ ዝናብ የራይል ወንዝ በ17.5 ሜትር ከፍ እንዲል በማድረጉ ከባድ ጥፋት እያስከተለ ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ሱዳን በታሪኳ ከ100 ዓመት ወዲህ እንዲህ የወንዝ ሙላት ገጥሟት አያውቅም፡፡ በዚህም ምክንያት በሱዳን ካለፈው በፈረንጆቹ ኦገስት መጨረሻ 100 ሺህ ቤቶች ሲወድሙ ወደ ከአንድ […]

የፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ልጅ የሞተው በገዳይ ንጥረ ነገር መሆኑን የቤተሰቡ ጠበቆች ተናገሩ ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2012 የፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ልጅ የሞተው በገዳይ ንጥረ ነገር መሆኑን የቤተሰቡ ጠበቆች ተናገሩ ::የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ልጅ የሞተው በልብ ህመም ሳይሆን በአደገኛ ንጥረ ነገር ተመርዞ ስለመሆኑ መረጃ ደርሶናል ብለዋል ጠበቆቹ፡፡ የ25 ዓመቱ አብደላ ሙርሲ ከአንድ ዓመት በፊት መኪና በሚያሽከረክርበት ወቅት በድንገት የጡንቻ አለመታዘዝ እና መኮማተር ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም […]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን የአንድ ዓመት ወጪ ለመሸፈን ቃል ገባ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4፣ 2012 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን የአንድ ዓመት ወጪ ለመሸፈን ቃል ገባ:: ለ2013 ዓ.ም የሚሆን ስጦታ በሚል በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን በሙሉ የአንድ ዓመት የህክምና ወጪ እንደሚሸፍን የከተማ አስተዳደሩ ቃል ገብቷል፡፡ ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን የምስጋና ቀን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ […]

አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ 551 ለሚሆኑ የፌዴራል ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4፣ 2012 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ 551 ለሚሆኑ የፌዴራል ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ:: የ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በፌዴራል፣ በክልልና በመከላከያ ወታደራዊ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ የፌዴራል ታራሚዎች በተለያዩ መስፈርቶች መነሻ ለ551 ታራሚዎ ይቅርታ ተደረገ ። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የይቅርታና ምህረት ቦርድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዳላሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ […]