loading
በሰሜን አሜሪካ በአዉሮፓ በአዉስትራሊያ እና በአፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች ኢትዮጵያን የሚያፈርሱ አካሄዶችን እንደሚቃወሙ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2013 በሰሜን አሜሪካ በአዉሮፓ በአዉስትራሊያ እና በአፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች ኢትዮጵያን የሚያፈርሱ አካሄዶችን እንደሚቃወሙ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች ወቅታዊ የሀገራቸዉን ሁኔታ በተመለከተ ባወጡት የጋራ መግለጫ ፤ አደገኛ የዉስጥ ግጭት እና የዉጭ ከበባና ዛቻ ባለበት በዚህ የታሪክ ወቅት ልዩነታችን ላይ እያተኮርን የምንበታተንብት ጊዜ ሳይሆን፤ የተነሳብንን አደጋ በጥልቀትና አርቆ በማሰብ መርምረን በምን መልኩ […]

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቅሬታ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቅሬታውን ገለፀ ፡፡ የኢ/ያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 19 ባደረገው 7ኛ መደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚሳተፉ የማራቶን ተወዳዳሪ አትሌቶች በኑከራ ውድድር መምረጥ አስፈላጊ በመሆኑና በፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ኮሚቴ፣ በአሰልጣኞችና በአትሌቶቹም ጭምር በጋራ በተደረገ በመሆኑ እንድትሳተፉ ሲል በወንዶች የ12 እንዲሁም በሴቶች የ8 […]

የአብን ማሳሰቢያ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 የአገራችንን ምኅዳር ለአንድ ወገን ዘረኛና ያልተገራ ሽምጥ ግልቢያ የሚያመቻቹ ኃይሎች ከወዲሁ ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ሲል አብን አሳሰበ፡፡ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ባወጣዉ መግለጫ፤ የአማራ ሕዝብ በአገዛዙ ላይ የቀረውን ተስፋና በጎ ግምት ሁሉ አስተባብሎ መጨረሱን እና በየቦታው በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ጭፍጨፋና ፖለቲካዊ አሻጥር በማያሻማ ሁኔታ በአገር ቤትና በውጭ አገር […]

የፖሊስ ልዩ የበዓል ዝግጅት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 የስቅለት እና የትንሳኤ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ወቅቱን ያገናዘበ የፀጥታ ዕቅድ አውጥቶ ወደ ተግባር መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡በበዓላት መዳረሻ ወቅቶች ከወትሮው በተለየ ጨምሮ የሚታየውን የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተከትሎ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት እና በተለይም በግብይት፣ በመዝናኛ ሰፍራዎች እና በዕምነት ተቋማት አካባቢ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ከወትሮው የተለየ ዝግጅት በማድረግ የፀጥታ […]

ለህግ ታራሚዎች የተደረገ ይቅርታ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22 ፣ 2013የአማራ ክልል ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን ገለጸ የአማራ ክልላዊ መንግስት ለ2ሺህ 705 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡ የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አለምሸት ምህረቴ ለኢዜአ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ለታራሚዎቹ ይቅርታ ያደረገው በይቅርታ ቦርዱ ተመርምሮ መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው ነው። የይቅርታው […]

ህዝቡ በዓብይ ፆሙ ለሀገር ሠላም ተግቶ ሲፀልይ የነበረውን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22 ፣ 2013የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው ህዝቡ በፆም ወቅት ያሳየውን መተዛዘን፣ መከባበርና ለሀገር ሠላምና ደህንነት ተግቶ ሲፀልይ የነበረውን በጎ ተግባር ከፆሙፍቺ በኋላም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። በክልሉ የትንስዔ በዓልን በማስመልከት ለ970 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታና የእስራት ቅነሳ መደረጉን የገለፁት አቶ ርስቱ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል። ምክትል […]

የአሚሶም ሽልማት ለኢትዮጵያ ወታደሮች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 አሚሶም ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት አስተዋጽኦ ላበረከቱ የኢትዮጵያ ወታደሮች የክብር ሜዳልያ ሸለመ:: በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) ስር የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኑ፡፡ ሽልማቱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች በሶማሊያ በነበራቸው የአንድ አመት ከስድስት ወር ቆይታ በሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት ላደረጉት […]

በአዲስ አበባ አንድ ግለሰብ ስጋ አንቆት ሕይወቱ አለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 በአዲስ አበባ አንድ ግለሰብ ስጋ አንቆት ሕይወቱ አለፈ፡፡ በፋሲካ በአል ቀን ስጋ እየተመገበ የነበረው ወጣት ስጋው አንቆት ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ ድንገተኛ የሞት አደጋው የደረሰው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ካዲስኮ አካባቢ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጻል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት የሚዲያ ሀላፊ ዋና […]

በኢትዮጵያ የሚከበረው የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 የአለም የፕሬስ ነፃነት ቀን መረጃ ለህዝብ ጥቅም በሚል መሪ ሀሳብ ነው ለ30ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው። ከ 30 አመት በፊት በናሚቢያ መከበር የጀመረው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ መንግስታት የፕሬስ ነፃነትን እንዲያከብሩ መነሻ ሆኗል። በኢትዮጵያ የሚከበረውን አለምአቀፉ የፕሬስ ቀን በማስመልከት አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ በሀገራችን የፕሬ […]

በአዲስ አበባ በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013  በአዲስ አበባ ከተማ በደረሱ ሁለት ድንገተኛ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አያት ጤና ጣቢያ ጀርባ ትናንት ምሽት 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ በግንባታ ስራ ላይ የነበረ የ35 […]