loading
የዐረብ ሊግ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈረም ለመንግስታቱ ድርጅት ጥያቄ አቀረበ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11፣ 2013  የዐረብ ሊግ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈረም ለመንግስታቱ ድርጅት ጥያቄ አቀረበ፡፡በጋዛ የተቀሰቀሰው ግጭት እንዲቆም እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ድርድሩ ሂደት ዳግም እንዲጀመር ነው ሊጉ ጥሪ ያቀረበው፡፡ የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በፈረንጆቹ ግንቦት 20 በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ዙሪያ ለመምከር ቀጠሮ መያዙን በድርጅቱ የአረብ ሊግ ተወካይ መጅድ አብደልፈታህ ተናግረዋል፡፡ ተወካዩ አህራም […]

በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮሮናቫይረስ ሞት ተመዘገበ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11፣ 2013 በህንድ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮሮናቫይረስ ሞት ተመዘገበ በህንድ እየተባባሰ የመጣውን የኮሮናባይረስ ወረርሽኝ መቆጣጠር ያቃታቸው ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በህዝባቸው ዘንድ የነበራቸውን አመኔታ ዝቅ እንዲል አድርጎባቸዋል፡፡ በ24 ሰዓታት ውስጥ 4 ሽህ 529 ዜጎቿን በቫይረሱ የተነጠቀቸው ህንድ አሁንም በወረርሽኙ ጠንካራ ክንድ እየተደቆሰች ትገኛለች፡፡በየቀኑ በአማካይ ከ250 ሺህ በላይ ሰዎች […]

የቴክኖው CAMON 17 ሰልፊ ላይ ባውጠነጠነ አስገራሚ ዘጋቢ ፊልም በመታገዝ ወደገበያ ገብቱዋል::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 የቴክኖው CAMON 17 ሰልፊ ላይ ባውጠነጠነ አስገራሚ ዘጋቢ ፊልም በመታገዝ ወደገበያ ገብቱዋል::ይህ ፈጠራ የታከለበት በፊልም የታገዘው የቴክኖ የማስመረቂያ ፕሮግራም ድርጅቱ ምርቱን ከማስተዋወቅ ባለፈ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና በሰብዓዊነት ላይ የበለጠ ጥረት ለማድረግ ያለውን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው:: ይህ ደግሞ ድርጅቱ በአለማችን ላይ በዘርፉ ቁንጮ እየሆነ መምጣቱን ይጠቁማል:: በአዲሱ ትውልድ በአለም አቀፍ ደረጃ […]

በአዲስ አበባ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ላይ የተወሰደዉ እርምጃ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች በታየባቸው ክፍተት የስራ ውል እንዲያቋርጡ ተደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 በአዲስ አበባ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ላይ የተወሰደዉ እርምጃ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች በታየባቸው ክፍተት የስራ ውል እንዲያቋርጡ ተደረገ:: ከ 60 እስከ 70 የሚጠጉ ድጋፍ ሰጪ አውቶቢሶች ባሳዩት ክፍተት ውላቸው ተቋርጦ በሌሎች የመተካት ስራ እየሰራ እንደሆነ የ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖረት ቢሮ ምክትል […]

ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት ተከትበዋል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት ተከትበዋል ተባለ:: የጤና ሚኒስቴር በየ24 ሰዓቱ በሚያወጣው የኮቪድ 19 ወቅታዊ መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 ክትባት መከተባቸውን ገልጿል፡፡ በተጨማሪም 2 መቶ22 ሺ 5 መቶ 60 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ሪፖርቱ አትቷል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ […]

የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዞር የተደረገ ምክክር::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013  ጠ/ሚ ዐቢይ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዞር ከተቋቋመው አማካሪ ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለት የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ፈቃድ ለመስጠት እየተሰራ ባለው ስራ ዙሪያ ከአማካሪ ምክር ቤት አባላት ጋር መከሩ።ውይይቱ አዲስ የቴሌኮም ፈቃድ በመስጠት ሂደቱ ዙሪያ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ በከፊል ወደ ግል ለማዞር ከተቋቋመው […]

19 ክትባት ለሚከተቡ ሰዎች የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 የኮቪድ ኦሃዮ በተሰኘችው አሜሪካዋ ክፍለ ሃገር የኮቪድ 19 ክትባት ለሚከተቡ ሰዎች አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝ የሎተሪ ቁጥር እንደሚሰጣቸው ከተገለፀ በኋላ የተከታቢዎች ቁጥር በእጅጉ መጨመሩ ተገለፀ:: የኦሃዮ ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ ማይክ ዲዋይን በክትባቱ ላይ ጥርጣሬ ያላቸውን ሰዎች ለማበረታታትና የሚከተቡ ሰዎችን ቁጥር ለመጨመር ለእያንዳንዱ ክትባቱን የተከተበ ሰው አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝ […]

ግብፅ በሁለት ሳምንታት ውስጥ 35 ዶክተሮቿን በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ማጣቷን የሀገሪቱ የህክምና ማህበር ገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 ግብፅ በሁለት ሳምንታት ውስጥ 35 ዶክተሮቿን በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ማጣቷን የሀገሪቱ የህክምና ማህበር ገለጸ:: ባለፈው ማክሰኞ ዶክተር ዋስፊ የተባሉ የቆዳ ስፔሻሊስት ሀኪም በሳዳር አል አባሲያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ መሞታቸው የተሰማ ሲሆን በሰዓታት ልዩነት የህፃናት ሃኪም የሆኑት ዶክተር ራኒያ ፉአድ አልሰይድ ህልፈት ተሰምቷል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር የህክምና ማህበሩን ጠቅሶ እንደዘገበው […]

በቱኒዚያ የተጀመረው እስራኤልን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013  በርካታ ቱኒዚያዊያን እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈፅመውን ጥቃት በማውገዝ የአደባባይ ሰልፍ አካሄዱ ሰልፈኞቹ በዋና ከተማዋ ቱኒዝ ሞሃመድ 5ኛ ብሎ በሚጠራው ጎዳና ተሰባስበው ከፍልስጤም ጎን መሆናቸውን በመግለጽ እስራኤልን የሚያወግዙ መፈክሮችን ሲያሰሙ ታይተዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩት ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ በቅርቡ በቱኒዚያና በእስራኤል መካከል የተጀመረውን መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከወንጀል ትርታ በመመደብ እንዲሰርዝ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ […]

የህዳሴው ግድብ የሰላም ፕሮጀክት ነው” ደቡብ-ሱዳን

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሶስትዮሽ ድርድሩ ህብረቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተስፋ አለን አሉ፡፡ አቶ ደመቀ “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” መርህ መሰረት የሶስትዮሽ ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ሚናው አጠናክሮ እደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።አቶ ደመቀ የግድቡ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሊት በተያዘለት ጊዜ እንደኪካሄድም አብራርተዋል፡፡ አቶ ደመቀ […]