loading
የመስቀል አደባባይና የባህረ ጥምቀት ቦታዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸዉ ሲኖዶሱ አሳሰበ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23፣ 2013 የመስቀል አደባባይና የባህረ ጥምቀት ቦታዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸዉ ሲኖዶሱ አሳሰበ:: ከሰኔ 14 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 4 ቀን የሚቆይ የምህላ ፀሎት እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ አወጀ፡፡ መጪው ሀገራዊ ምርጫ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት በአንድነትና በሰላም እንዲጠናቀቅ በመላ ኢትዮጵያ ፀሎተ ምህላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ባሳለፈው ወሳኔ አስታውቋል ገዢው ፓርቲም ሆነ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝቡ የሚጠቅመውን […]

ቻይና በቤተሰብ ምጣኔ ላይ ትተገብረው የነበረውን የሁለት ልጅ ፖሊሲ ልታሻሽል ነው፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23፣ 2013 ቻይና በቤተሰብ ምጣኔ ላይ ትተገብረው የነበረውን የሁለት ልጅ ፖሊሲ ልታሻሽል ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናትን ዋቢ ያደረገው የሺንዋ ዘገባ መንግስት ጥንዶች ሶስት ልጆችን እንዲወልዱ ሊፈቅድ መሆኑን ያመለክታል፡፡መንግስት ከዚህ በፊት ጥንዶች ሁለት ልጆች ብቻ እንዲኖራቸው የሚያስገድድውን ፖሊሲ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አሁን ላይም ይህን ፖሊሲ በመቀየር ጥንዶች ሶስት ልጆችን እንዲወልዱ የሚፈቅደው የውሳኔ ሃሳብ […]

ቦርዱ በሰኔ 14 በተለያዩ ምክንያቶች ድምጽ የማይሰጥባቸውን  አካባቢዎች ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 ቦርዱ በሰኔ 14 በተለያዩ ምክንያቶች ድምጽ የማይሰጥባቸውን  አካባቢዎች ይፋ አደረገ:: የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሰኔ 14 በተለያዩ ምክንያቶች የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ የማይከናወንባቸውን  የተወሰኑ አካባቢዎች ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድምጽ መስጫ ቀን መሆኑን አሳውቆ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል፣ ከዚህም መካከል በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ የድምጽ […]

በኢትዮጵያ 37 ሺህ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 በኢትዮጵያ 37 ሺህ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ:: በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ 37 ሺህ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል፡፡ ተቋሙ ባወጣው መረጃ “ሳይበር ሆርስ ግሩፕ” የተሰኘ የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች […]

በመዲናዋ በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 በመዲናዋ በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ:: በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ አመት ውስጥ 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ፕሮፐርቲ 2000 ደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ተወካይ ተፈራርመውታል፡፡ ለግንባታው 4 ነጥብ 2 ቢሊየን […]

በአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 በአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው ::በአዲስ አበባ የሚገኙ 2 ሺህ አካል ጉዳተኞች ለአንድ አመት ያህል ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ሊያገኙ መሆኑን የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አካል ጉዳተኞች የእውቅና መርሃ ግብር […]

ከአሜሪካ ጋር ያጋጠመንን ጉዳይ በወዳጆቻችን በኩል ለመፍታት እየሰራን ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013  ከአሜሪካ ጋር ያጋጠመንን ጉዳይ በወዳጆቻችን በኩል ለመፍታት እየሰራን ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ:: የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ አቋሟን ትቀይራለች ብሎ እንደሚያምንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ ገልጸዋል:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት ጋዜያዊ መግለጫ የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ፣ ከአሜሪካ ጋር የተፈጠረው አለመግባባት የመግለጫቸው ዋነኛ […]

ኢሚግሬሽን “ለትግራይ ተወላጆች አገልግሎት መስጠት አቁሟል” መባሉን “ውሸት ነው” አለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ለትግራይ ተወላጆች የሚሰጠውን አገልግሎት አቁሟል በሚል በማህበራዊ ሚድያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ “ፍጹም ሀሰት” እንደሆነ የተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዪኒኬሽን ዳይሬክተር ደሳለኝ ተሬሳ ተናገሩ፡፡ አቶ ደሳለኝ ለአል-ዐይን እንደተናገሩት በክልሉ ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት “ትግራይ” የሚለው ስም ከኤጀንሲው የአገልግሎት ማመልከቻ ድረገጽ ወጥቷል፡፡ በዚህ ምክንያት ለትግራይ ተወላጆች […]

የባልደራስ እና የምርጫ ቦርድ የችሎት ክርክር::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013 ምርጫ ቦርድ ሰበር ችሎት ለባልደራስ የወሰነውን ለምን እንዳልፈጸመ ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እነ አቶ እስክንድር ነጋ (3 አባላት) በዕጩነት እንዲመዘገቡ የሰጠውን ውሳኔ ለምን መፈጸም እንዳልቻለ የሚያስረዳዉም ሐሙስ ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ነዉ፡፡ ፍርድ ቤቱ ለቦርዱ ትዕዛዙን ያስተላለፈው […]

የሴናተር ጂም ኢንሆፍ ጉብኝት ለኢትዮ-አሜሪካ ዲፕሎማሲ ያለዉ ፋይዳ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013  የሴናተር ጂም ኢንሆፍ ጉብኝት ወቅታዊውን የኢትዮ-አሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሊያለዝበው ይችላል ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር በዕውቀቱ ድረሰ ተናገሩ፡፡ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሀገራት ላይ የጉዞ እገዳ መጣሉን ባስታወቀ ማግስት ድርጊቱን የኦክላሃማው ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አጥብቀው ተቃውመዋል፡፡ ሴናተሩ በሀገራቸው ሳሉ ከሚያሳዩት የኢትዮጵያ አጋርነት ሌላ ከሰሞኑ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አዲስ አበባ መግባታቸዉ […]