loading
በትግራይ ኤርትራዊያን ስደተኞች ደህንነታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 በትግራይ ኤርትራዊያን ስደተኞች ደህንነታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ:: አሸባሪው ህወሓት ስደተኞች በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ጥቃቶች መክፈቱን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ኤጀንሲው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባለከው መግለጫ እንደገለጸው፤ ህወሓት የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ውድቅ አድርጎ ስደተኞች ላይ ጥቃት እየፈጸመ ነው። በዚህ የህወሓት ጥቃት ምክንያት በማይ-ዓይኒ እና በአዲ-ሐሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች […]

የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን አግቶ የወሰደዉ ግለሰብ ተያዘ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን አግቶ የወሰደዉ ግለሰብ ተያዘ:: የ4ዓመት ከ9ወር ዕድሜ ያላትን ህጻን ከትምህርት ቤት አግቶ በመውሰድ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ ከአዲስ አበባ ውጪ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ የእገታ ወንጀሉ የተፈፀመው ሰኔ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 10 ሰዓት ተኩል ገደማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ […]

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ተረከበች::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 አሜሪካ ለኢትዮጵያ የለገሰችውን 453 ሺህ 600 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ጤና ሚኒስቴር ተረከበ:: በአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የተደረገው ድጋፍ  ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተባለው  ክትባት ሲሆን ቃል ከገባችው 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶዝ 453 ሺህ 600 ዶዙ አዲስ አበባ  ገብቷል። ድጋፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት […]

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቀቀ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቀቀ::ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ መጀመሩ ተነግሯል ዛሬ ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ መጀመሩን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው ላይ ውሃው በግድቡ […]

ኢትዮጵያ በጽናት ትገሰግሳለች-ጠ/ሚ ዐቢይ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013  ጠ/ሚ ዐቢይ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን አስመልክተው በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ በጽናት ትገሰግሳለች ብለዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ÷የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት መርሃግብር […]

በጣና ሀይቅ በተሰወረችው ጀልባ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስክሬን ተገኘ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 በጣና ሀይቅ በተሰወረችው ጀልባ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች አስክሬን ተገኘ:: በጣና ሀይቅ በተሰወረችው ጀልባ ህይወታቸው ያለፈ የ7 ሰዎች አስክሬን ተገኘ በማእከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በጣና ሀይቅ 13 ሰዎችን አሳፍራ በጉዞ ላይ እንዳለች በተሰወረችው አነስተኛ ጀልባ ህይወታቸው ያለፈ የሰባት ሰዎች አስክሬን መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ […]

የሕወሃት ትንኮሳ በሰብዓዊ ድጋፍ ስርጭት ላይ የፈጠረው ጫና…

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16፣ 2013 አሸባሪው ህወሓት ትንኮሳውን ወደሌሎች ክልሎች በማስፋቱ የእርዳታ እህል ለማጓጓዝ መቸገሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ:: መንግስት ለሰብአዊ ድጋፍ ሲል ያሳለፈውን የተናጠል ተኩሱ አቁም አሸባሪው ህወሓት ወደ ጎን በመተው ትንኮሳውን ወደ አማራ እና አፋር ክልል ማስፋቱ ይታወቃል። በዚህ ግጭት ምክንያትም የእርዳታ እህል እና መሰል ድጋፎችን ወደ ትግራይ ክልል ለማስገባት መቸገሩን የተባበሩት […]

በማይካድራ በርካታ የጅምላ መቃብሮች ተገኝተዋል-ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16፣ 2013  የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 30 በማይካድራ በተፈጸመው ጭፍጨፋ ከ1 ሺህ 600 በላይ ሰዎች ሰለባ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በማይካድራው በደረሰው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ላይ ስድስት ወራት የፈጀ ጥናት ሠርቻለሁ ብሏል፡፡ የጥናቱ ዓላማ ድርጊቱን ለዓለም አቀፍ ማኀበረሰብ ማሳወቅ፣ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተጎዱ ወገኖች እንዲካሱ ማድረግ ነው ተብሏል። በጥናቱ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ለዓመታት […]

በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ሁከት ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ከ3 መቶ በላይ መድረሱ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16፣ 2013 በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ሁከት ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ከ3 መቶ በላይ መድረሱ ተሰማ፡፡ ለአንድ ወር ያህል በዘለቀው የደቡብ አፍሪካ ብጥብጥ እስካሁን የ 347 ዜጎችን ህይወት መቅጠፉን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 79 የሚሆኑ ሰዎች በጋውንቴንግ ግዛት 276 ዜጎች ደግሞ ክዋዙሉ-ናታል ግዛት መሞታቸውን ከፕሬዝዳንቱ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ ሁከቱ በየዕለቱ እየጨመረ የመጣ ሲሆን […]

ለሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በሙኒክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በሙኒክ ተካሄደ፡፡ በጀርመን ሙኒክ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ አዘጋጅነት በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል። በተለያዩ ዘርፎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር “ደግሞ ለዓባይ” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይ ኢትዮጵያዊያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ በቦንድ […]