በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ ያደረሰው ጉዳት ወደ ሰው እንዳይሸጋገር እየተሰራ ነው ተባለ፡፡
አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከአጋር አካላት ጋር በመሆንድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ በሶማሌ ክልል 9 ዞኖችበተከሰተው የድርቅ አደጋ 960 ሺህ በላይ ዜጎች ተጎጂ በመሆናቸው የእለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ በክልሉ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች የእለት ደራሽ ድጋፍ ይፈልጋሉ […]