loading
በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ምክክር መጀመሩ ተነገረ

በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ምክክር መጀመሩ ተነገረ፡፡  በጉባኤው የተገኙት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለችግሮች የሚመጥን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲኖር ለማስቻል ምክክሩ ለቀጣይ ስምሪቶች ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች እና አጎራባች ስፍራዎች  የሕግ የበላይነት እንዲከበር እና ሕዝቡ የሚፈልገውን ሰላም ለማረጋገጥ የፌዴራል እና […]

በቅርቡ የተቋቋመው  የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ለግጭቶች ዋነኛ መንስኤዎችን በማጥናት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እሰራለሁ አለ

በቅርቡ የተቋቋመው  የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ለግጭቶች ዋነኛ መንስኤዎችን በማጥናት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እሰራለሁ አለ ፡፡ ኮሚሽኑ በቀጣይ ጊዜያት እውነትና ፍትህ ላይ መሰረት ያደረገ እርቅ ለማውረድ እንደሚሰራም ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ወደ ስራ የገባው በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ምክንያት በህዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶችን ለማከም እውነተኛና ፍትህን መሰረት ያደረገ እርቅ ማውረድ አስፈለጊ መሆኑን አምኖ […]

የ አይኤስ አይኤስ መሪው አልባግዳዲ አልሞትኩም እያለ ነው

ለአምስት አመታት ከእይታ ተሰውሮ የቆየውና በብዙዎች ዘንድ ሞቷል ተብሎ የታመነው የኢስላማዊ ታጣቂ (አይ ኤስ) ቡድን መሪ አቡ ባክር አልባግዳዲ በቅርቡ በለቀቀው  ተንቀሳቃሽ ምስል እንዳልሞተ አረጋግጧል። ከሁለት ሳምንት በፊት በስሪላንካ የፋሲካ በዓል ዕለት ለደረሰው የቦምብ ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዷል። የኢስላማዊ ታጣቂ (አይ ኤስ) ቡድን መሪ አቡ ባክር አልባግዳዲ ድምጹን ካጠፋ ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ በተንቀሳቃሽ […]

በቡሪኪናፋሶ በቤተ ክርሰቲያን ላይ በተፈፀመ ጥቃት 5 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል

በቡሪኪናፋሶ በቤተ ክርሰቲያን ላይ በተፈፀመ ጥቃት 5 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል አልጀዚራ እንደዘገበው ጥቃቱ ከትላንት በስቲያ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ዲጂቦ አቅራቢያ በምገትኘው ሲልጋ ዲጂ ከተማ ነው የተፈፀመው፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመውም በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ላይ ሲሆን፣ በቤተክርስቲያኑ ላይ በተፈጸመው ጥቃት አገልግሎት ላይ የነበረን አንድ ፓስተርን ጨምሮ በቤተ ክርስሰቲያን ውስጥ በፀሎትላይ የነበሩ 5 ምዕመናን ህይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በዚሁ ጥቃት ህይወታቸው ካለፈው አምስት ሰዎች በተጨማሪ ይህ ዘገባ እስከተሰራበት ጊዜ ድረስ ሁለት ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀም ተገልፃል፡፡ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡርኪነፋሶ የሽብር ጥቃት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በቤተ ክርሰቲያን ላይ ጥቃቱ ሲፈፀም ይህ የመጀመሪያው ነው፣ የታጣቂዎች ማንነትም እስካሁን እንዳልታወቀ ነው አልጀዚራ በዘገባው ያሰፈረው፡፡