loading
ጋዜጠኞችን የደበደቡ የዩጋንዳ ወታደሮች የእስር ትእዛዝ ወጣባቸው፡፡

የሀገሪቱ ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ዴቪድ ሙሁዚ ጸጥታ የማስከበር ስራን ሽፋን አድርገው ጋዜጠኞችን በጭካኔ የደበደቡ ወታደሮች ላይ ከባድ ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ጠበቅ ያለ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ የኬንያው ደይሊ ኔሽን ጋዜጣ እንደዘገበው ጋዜጠኞቹ ባለፈው ሰኞ በዩጋንዳ ፖለቲከኞች ይፈቱ የሚል አመጽ ባሰነሱ ሰልፈኞች ላይ የጸጥታ ሀይሎች የሚወስዱትን ርምጃ ሲዘግቡ ነው ድብደባው የደረሰባቸው፡፡ የዩጋንዳ መከላከያ ተቋም ይህን ትእዛዝ ያስተላለፈው በሀገር ውስጥና […]

በመሬት፣ በቀበሌ ቤቶች፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በህንፃዎች ላይ የኦዲት ሥራ በመስራት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት በከተማ አስተዳደሩ እስካሁን የነበሩ ተግባራትን ቆም ብሎ በማየት ሀገራዊ ለዉጡን ለማስቀጠል በመሬት፣ በቀበሌ ቤቶች፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በህንፃዎች ላይ የኦዲት ሥራ እየተሰራ ነዉ፡፡ ምክትል ከንቲባዋ ˝የአዲስ ተስፋ ቀመር˝ በሚል መሪ ቃል አዲሱን ዓመት ለማክበር ጥላቻን በመቀነስ (-)፣ ያለንን በማካፈል (÷)፣ […]

ኢትዮ ቴሌኮም የታሪፍ ቅናሽ አደረገ፡፡ 

በዚህም መሰረት የስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የ43 ከመቶ፣ የብሮድባንድ ኢንተርኔት ላይ የ54 ከመቶ፣ የስልክ ድምፅ ላይ የ40 ከመቶ እንዲሁም የሞባይል የፅሁፍ መልዕክት (SMS) ላይ የ43 ከመቶ ቅናሽ ማድረጉን ሰምተናል፡፡ መረጃውን ሸገር የሰማሁት ከኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ነው ብሎ በድረ ገፁ አስነብቧል።

ከኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ከነሀሴ 14 እስከ 16/2010 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የጥልቅ ተሃድሶውን አፈፃፀምና ያስገኘውን ውጤት በተለመደው ድርጅታዊ ባህል፣ ዴሞክራሲያዊነትን በተላበሰ እና በሰከነ አግባብ በጥልቀት ገምግሟል፡፡ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የጥልቅ ተሃድሶውን ተከትሎ የተወሰዱ የለውጥ እርምጃዎች የአመራር ፈጠራ ታክሎባቸው የለውጡ ቱርፋት የሆኑ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን አረጋግጧል፡፡ ከአሁን በፊት ውሳኔዎች እየተወሰኑ እና አቅጣጫዎች እየተቀመጡ በአፈፃፀም ድክመት ይታይባቸው […]

የዘንድሮው የአሸንዳ በአል በመቀሌ ከተማ ስታዲየም “አሸንዳ ለሰላም እና አንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል፡፡

በክብረ በዓሉ የመንግስተ አመራሮች፣ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸአው ታዳሚዎች ተገኘተውበታል፡ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ወ/ሮ ሶፊያ አሚን የህዝቦች አንድነት፣መፈቃቀር፣አብሮ የመኖር ትስስርን ከሚያጠናክሩ ጠቃሚ እሴቶች እና ክብረ በአላት መሃከል አሸንዳ አንዱ እንደሆነ ገልፀው እነዚህ እሴቶች የሰላም እና አንድነት ማገር ሆነው ከትውልድ ትውልድ ይተላለፉ ዘንድ ጠንክረን መስራት አለብን ብለዋል፡፡ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደ/ር […]

የአፍሪካና የቻይና ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡

ሮይተርስ እንዘገበው በቻይናና በአፍሪካ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን እስካለፈው ዓመት ድረስ 170 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ደርሷል፡፡ በመጭው መስከረም ወር ላይ  የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም  ቻይና ውስጥ ይካዳል፡፡ ፎረሙም በቻይናና በአፍሪካ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ቻይና ለአፍሪካ ሀገራት ለአቅም ግንባታ የሚውል 10 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ገንዘብ መድባለች፡፡ ገንዘቡ […]

ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ እና ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ በላሊላ አሸንድዬ ካባ ተደረበላቸው።

አሸንድዬ፣አሸንዳ ፣ሶለል እና ሻደይ የዓለም ሀብት የሚሆኑት በባለቤትነት ስንጠብቃቸው ነው ብለዋል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን። የአሸንድዬ የሴቶች በዓል “አሸንድዬ ለሰላምና አንድነት በፍቅር ለመደመር” በሚል መሪ ቃል በላሊበላ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። በበዓሉ ላይ ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ ወጣቶች ለሰላም ስሩ ሲሉ ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ደግሞ ባህል የሚታወቀው አገር ሲኖር ነው ብለዋል ። አርትስ ቲቪ […]

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በኮየ ፈጬ ሳይት የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገኙበትን ደረጃ ጎበኙ

በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተመራውና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልኡካን በ11ኛው ዙር የተላለፉ የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን አነጋግረዋል። ነዋሪዎች የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ባለማሟላቱ ቅሬታቸውን ገልጸውላቸዋል በተለይም የውሃ፣ የመብራት  እና የባለድርሻ አካላት በቅንጅት ተናበው አለመስራት በኑሮአቸው ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረ ነው የገለጹት፡፡ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለም የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች የህብረተሰቡን ቅሬታ ወስደው […]