loading
አማርኛ ቋንቋን የአፍሪካ ኅብረት የስራ ቋንቋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 አማርኛ ቋንቋን የአፍሪካ ኅብረት የስራ ቋንቋ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ፤ በመዲናችን የተካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ስኬታማ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡ ኅብረቱ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከል ተቋምን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መወያየቱንም ተናግረዋል፡፡ የኮቪድ- 19 መፍትሄዎቸ፣ የሰላምና የጸጥታ ችግር፣ […]

የህዳሴ ግድቡ ሃይል ማመንጨት መጀመርና የግብጽ ቅሬታ…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 ኢትዮጵያበግድቡ ዙሪያ የተናጠል ውሳኔ በማሳለፍ መርህ የመጣስ ተግባሯን ቀጥላበታለች ስትል ግብጽ ቅሬታዋን አሰማች፡፡የግብፅ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የህዳሴ ግድቡን የመጀመሪያው ሃይል የማመንጨት ስራ ይፋ መሆን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን እርምጃ መርህን የሚጻረር ብሎታል፡፡ ከአሁን ቀደም የመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ሲከናወን ተመሳሳይ ተቃውሞ ያሰማችው ግብፅ ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ2015 […]

ዩጋንዳ የኮቪድ-19 መከላከያ ያልተከተቡ ሰዎችን በገንዘብና በእስራት መቅጣት የሚያስችል ህግ አረቀቀች::

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 ዩጋንዳ የኮቪድ-19 መከላከያ ያልተከተቡ ሰዎችን በገንዘብና በእስራት መቅጣት የሚያስችል ህግ አረቀቀች፡፡ ለሀገሪቱ ፓርላማ የቀረበው ይህ የህግ ረቂቅ ክትባት ለመውሰድ አሻፈረኝ በሚሉ ዜጎች ላይ 1 ሺህ 139 ዶላር ወይም 4 ሚሊዮን የሀገሪቱን ገንዘብ የሚያስቀጣ ሲሆን የሥድስት ወር እስራትንም ያካትታል፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ጄን ሩት አሴንግ ረቂቅ ህጉን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ዜጎችን […]

ቻይና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን የፀጥታ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚያደርጉትን ጥረት እንደምትደግፍ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 ቻይና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን የፀጥታ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚያደርጉትን ጥረት እንደምትደግፍገለጸች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአፍሪካ ቀንድ የቻይና ልዩ መልዕክተኛ ሚስተር ዙ ቢንግ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። በውይይታቸውም አቶ ደመቀ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት እና ቻይና ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ሁለገብ ድጋፍ አድንቀዋል።በዚህ ረገድ ቻይና […]

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሚገጥሟቸው ችግሮች …

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 በሱዳን የመኖሪያ እና ሥራ ፈቃድ ክፍያዎች ከኢትዮጵያዊያን የመክፈል አቅም በላይ በመሆቸው በርካቶች ሕጋዊ ሆኖ ለመኖር መቸገራቸው ተገለጸ፡፡ በሱዳን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር የሆኑት ይበልጣል አዕምሮ ችግሩን ለመቅረፍ በሱዳን በኩል ልዩ ድጋፍ እና ትብብር እንዲደረግ ጠይቀዋል። አምባሳደር ይበልጣል ጥያቄውን ያቀረቡት ከሱዳን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ተጠባባቂ ሚኒስትር ጋር በችግሩ ዙሪያ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ […]

የኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ኡሁሩ ኬንያታ ሀገሪቱን በተሳሳተ መንገድ እየመሯት ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 የኬንያው ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ኡሁሩ ኬንያታ ሀገሪቱን በተሳሳተ መንገድ እየመሯት ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡ኡሁሩ የአመራር ብቃት የላቸውም ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ለዚህ አንዱ ማሳያ እሳቸው ወደ ስልጣን ሲመጡ የነበረው የመንግስት የብድር መጠን ከ17 ቢሊዮን ወደ 63 ቢሊዮን ዶላር ማሻቀቡ ነው ብለዋል፡፡ የሁለቱ መሪዎች መቃቃር የተጀመረው ኡሁሩ ከቀድሞው ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋ ጋር […]

በሶማሊያ በተፈፀሙ ሁለት የሽብር ጥቃቶች የ48 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 በሶማሊያ በተፈፀሙ ሁለት የሽብር ጥቃቶች የ48 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ በማዕከላዊ ሶማሊያ በተፈፀሙት ጥቃቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 48 ከፍ ያለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የሂርሻቤል ግዛት አስተዳዳሪ የአልሸባብ አማፂያን ከምርጫው በፊት ፖለቲከኞች ላይ ማነጣጠራቸውንአስታውቀዋል። መጀመርያ በሂርሻቤል ቤልደዌን አውራጃ በተፈፀመው የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት አሚና መሀመድ አብዲን ጨምሮ ሁለት የአካባቢው ህግ አውጪዎች […]

የሱዳን የሽግግር መንግስት መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ በካይሮ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 የሱዳን የሽግግር መንግስት መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ በካይሮ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡አልቡራሃን ወደ ካይሮ በመጓዝ ከፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ ሀገራትመካከል ስላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በደህንነትና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ውይይትአድርገዋል፡፡በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ላይ የተቀመጡት ጄኔራል አልቡራሃን በሀገራቸው የተፈጠረውንአለመረጋጋት መልክ ለማስያዝ የግብፅን ድጋፍ ጠይቀዋል ነው የተባለው፡፡ፕሬዚዳንት አልሲሲ በበኩላቸው ግብፅና ሱዳን […]

ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ በኒው ጀርሲ ግዛት ተካሄደ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ በኒው ጀርሲ ግዛት ተካሄደ:: በትናትናው ዕለት በ “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕግ አርቃቂ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርሲ) ቢሮ ፊት ለፊት በተከናወነው ሰልፍ ላይ “ረቂቅ ሕጎቹ ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚጎዱ ናቸው”፣ ”ማዕቀብ ይገድላል ማዕቀብ ምንም አይጠቅምም”፣ “ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” […]

ለጋሽ አካላት በአፍሪካ ቀንድ ለምግብ እጥት ለተጋለጡ ወገኖች 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2014 ለጋሽ አካላት በአፍሪካ ቀንድ ለምግብ እጥት ለተጋለጡ ወገኖች 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ከ40 ዓመታት በላይ ታይቶ የማያውቅ የድርቅ አደጋ መከሰቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል፡፡ በዚህም የተነሳ ቁጥራቸው ከ15 ሚሊዮን የሚበልጥ ሰዎች ለከፋ የምግብ እጥረት አደጋ ተጋልጠዋል ነው የተባለው፡፡ […]