loading
በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ሁከት ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ከ3 መቶ በላይ መድረሱ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 16፣ 2013 በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ሁከት ሳቢያ የሟቾች ቁጥር ከ3 መቶ በላይ መድረሱ ተሰማ፡፡ ለአንድ ወር ያህል በዘለቀው የደቡብ አፍሪካ ብጥብጥ እስካሁን የ 347 ዜጎችን ህይወት መቅጠፉን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ 79 የሚሆኑ ሰዎች በጋውንቴንግ ግዛት 276 ዜጎች ደግሞ ክዋዙሉ-ናታል ግዛት መሞታቸውን ከፕሬዝዳንቱ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ ሁከቱ በየዕለቱ እየጨመረ የመጣ ሲሆን […]

የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰይድ የሀገሪቱን ፓርላማ በተኑ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰይድ የሀገሪቱን ፓርላማ በተኑ፡፡ ፕሬዚዳንቱ የቱኒዚያዉን ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ከስልጣናቸ አባረዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱ ተግባር መፈንቅለ መንግስት ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች ገልጸውታል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበዉ ፕሬዚዳንቱ በኮቪድ-19 ሳቢያ በሀገሪቱ የተከሰተውን አመጽ ተከትሎ ነው እርምጃውን የወሰዱት ተብሏል፡፡ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ቱኒዚያዊያን የሀገሪቱ መንግስት ኮቪድ -19ን የያዘበት መንገድ አግባብ አይደለም በሚል ለተቃውሞ ወጥተዉ ነበር፡፡ በከተማዋ ቱኒዝ እና በሌሎች ከተሞችም ለተቃውሞ […]

ስምንት የግብጽ ወታደሮች በፀረ ሽብርተኝነት ተልዕኮ ላይ ሳሉ መገደላቸው ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 26፣ 2013 ስምንት የግብጽ ወታደሮች በፀረ ሽብርተኝነት ተልዕኮ ላይ ሳሉ መገደላቸው ተገለፀ፡፡ ስምንቱ ግብጻውያን ወታደሮች በጸረ ሽብርተኝነት ተልዕኮ በነበሩበት መገደላቸውን የጦሩ ቃል አቀባይ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ እንደ ወታደራዊ ሃይሉ መግለጫ በአብዛኛው ውጊያው እየተካሄደ የነበረው የታጠቁ የዳኢሽ ቡድኖች በሚንቀሳቀሱበት ሰሜናዊ ሲናይ በረሃ ላይ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ወታደሮቹ በሙሉ እዚያ ይሁን በሌላ ስፍራ ስለመሞታቸው ግን […]

በኬኒያ የኮቪድ-19 ክትባት የማይከተቡ የመንግስት ሰራተኞች ቅጣት ይጠብቃቸዋል::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013  በኬንያ የመንግሥት ሠራተኞች በሙሉ የኮቪድ-19 ክትባት እንዲከተቡ የ13 ቀናት ጊዜ ተሰጣቸው ፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ የማይከተቡ የመንግሥት ሠራተኞች የዲሲፕሊን እርምጃ ይጠብቃቸዋል መባሉን አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ የመንግሥት ሠራተኞች ሃላፊው ጆሴፍ ኪንዩዋ አንዳሉት ከሆነ ውሳኔው የተላለፈው በተለይ በመምህራንና በፀጥታ ዘርፍ ውስጥ ባሉ የመንግሥት ሠራተኞች አካባቢ የኮቪድ-19 ክትባት የመከተብ ዝንባሌ ዝቅተኛ በመሆኑ […]

በትግራይ ክልል ያለው ችግር የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነው – የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣2013  በትግራይ ክልል ያለው ችግር የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ መንግሥታቸው ጣልቃ የመግባት አጀንዳን እንደማይደግፍ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ገለጹ፡፡ በደበብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንትና የአገልግሎት ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ ከሆኑት ሁሴን አብዱል ባጊ አኮል ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ዙሪያ መክረዋል። አምባሳደር ነቢል የሁለቱ […]

በደቡብ አፍሪካ የሥራ አጦች ቁጥር ከዓለም ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣2013 በደቡብ አፍሪካ የሥራ አጦች ቁጥር ከዓለም ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡በብሉምበርግ ቁጥጥር በሚደረግባቸው የ82 ሃገራት ዝርዝር ውስጥ በደቡብ አፍሪካ የሥራ አጦች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሆኑን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡ የሥራ አጥነት መጠኑ በሁለተኛው ሩብ ዓመት ከ32.6 በመቶ እስከ መጋቢት ባሉት ሦስት ወራት ድረስ ወደ 34.4 በመቶ ከፍ ማለቱን በፕሪቶሪያ የሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ሰታትስቲክስ የመረጃ […]

ፈረንሳይ 10 ሚሊዮን የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን ለአፍሪካ ልትሰጥ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 የፈረንሳይ መንግስት በሰጠው መግለጫ ክትባቱ በአፍሪካ ህብረት የክትባት ማግኛ ትረስት በኩል ለህብረቱ አባል ሀገራት ይከፋልል ብሏል፡፡ እስከ መጭው መስከረም ወር 2022 ድረስ 400 ሚሊዮን አፍሪካዊያንን ተጠቃሚ የሚያደርግ የክትባት መጠን ግዥ መፈጸሙን የፕሬዚደንት ማክሮን ጽህፈት ቤት ይፋ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት በርሊን ላይ በተካሄደ ኮንፈረንስ የአፍሪካ መሪዎች ለአህጉሩ በቂ የክትባት መጠን እንዲሰጥ […]

አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ ተካተቱ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ ተካተቱ::አራት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ስም ዝርዝር ዉስጥ መካተታቸው ተገለፀ፡፡ በየዓመቱ 100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶችን ስም ዝርዝር የሚያወጣው አቫንስ ሚዲያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ 4 ኢትዮጵያዊያን በስኬታማና ተፅዕኖ ፈጣሪ 100 አፍሪካዊያን ሴቶች መዝገብ ውስጥ አካቷቸዋል። ከፕሬዚዳንቷ […]

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት ናት – የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣2013 ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት ናት ሲሉ የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፁ አምባሳደር አለምፀሃይ መሰረት ከኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ ጋር በሁለትዮሽ፣ አካባቢያዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል። በወቅቱም የኡጋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄጄ ኦዶንጎ፥ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ምልክት […]

አልጄሪያ በሀገር ውስጥ የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት መጀመሯን ይፋ አደረገች፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 ክትባቱ በቻይናው ሲኖቫክ ኩባንያ የሚዘጋጅ ሲሆን በአንድ ወር ውስጥ እስከ ስምንት ሚሊየን ዶዝ የማምረት አቅም አለው ተብሏል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የምርት መጠኑን በእጥፍ ማሳደግ እንደሚቻልም የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ተናግረዋል፡፡ የአልጀሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር አይመን ቤን አብደራሀማን የምርት ሂደቱ በጀመረበተ ወቅት በስፍራው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ይህ ለሀገራችን ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል፡፡ ገና […]