loading
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሀገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሀገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳ፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ እንዲነሳ ወስኗል፡፡ ይህን ውሳኔ ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ […]

በክልሉ ሰላምን ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የሶማሌ ክልል አስታወቀ

በክልሉ ሰላምን ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የሶማሌ ክልል አስታወቀ፡፤ የሶማሌ ክልል መንግሥት ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በመሆን የክልሉን ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁንየክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል። በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በክልሉ ረብሻ፣ አለመረጋጋትና መንግስታዊ የኃላፊነት ቦታዎችን በኃይል ለመያዝ የተደረገ ሙከራ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑንም […]

የሕወሓት ቡድን በአማራ ክልል ከተሞች አሰቃቂ ግፍና ወንጀሎችን መፈፀሙን አመንስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 የሕወሓት ቡድን በአማራ ክልል ከተሞች አሰቃቂ ግፍና ወንጀሎችን መፈፀሙን አመንስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ አደረገ፡፡ተቋሙ ዛሬ ባወጣው ሪፖርቱ የቡድኑ አባላት በአማራ ክልል ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች ሆን ብለው በርካታ ንጹሃንን መግደላቸውን፣ ሴቶችን በቡድን መድፈራቸውን እንዲሁም ከፍተኛ የግልና የመንግስትን ሃብት መዝረፋቸውን ተናግሯል፡፡ በተለይ ቆቦ እና ጭና በተባሉ ሁለት አካባቢዎች በነሃሴ መጨረሻና መስከረም መባቻ ላይ […]

በአዲስ አበባ በትናትናው እለት በተከሰተው የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2014 በአዲስ አበባ በትናትናው እለት በተከሰተው የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡ አዲስ አበባ አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደተናገሩት ÷ በመዲናዋ በትናንትናው ዕለት ሁለት የእሳት አደጋዎች ደርሰዋል፡፡አንዱ የእሳት አደጋ ትናንት 11 ሰዓት ከ50 ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በመኖሪያ ቤት ላይ […]

የጀጎል ግንብ ከንፅህና ጉድለት ጋር በተያያዘ ምክንያት ችግሮች እየገጠሙት እንደሆነ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 የጀጎል ግንብ ከንፅህና ጉድለት ጋር በተያያዘ ምክንያት ችግሮች እየገጠሙት እንደሆነ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ በአሁኑ ወቅትም በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የጀጎል ግንብ ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የማስዋብ ስራ እየተካሄደ ነው ተብሏል፡፡ “ጀጎልን ጽዱ እና ውብ እናድርጋት”  በሚል መሪ ሀሳብ በጀጎል የሚገኙ አሚር ኑር እና አባድር ወረዳዎችን በማስተባበር እና የህዝብ ንቅናቄ […]

ከ90 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪ እያስመዘገበ ያለው ውጤት አነስተኛ መሆኑ ተገለጸ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 ከ90 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪ እያስመዘገበ ያለው ውጤት አነስተኛ መሆኑ ተገለጸ። ኢትዮጵያ በእንስሳት ሃብቷ ከአፍሪካ ቀዳሚ ብትሆንም ያላትን ሃብት በአግባቡ መጠቀም ባለመቻሏ ውጤታማ እንዳልሆነችና በርካታ የቆዳ ውጤቶችን ከውጭ እንደምታስገባ ተነግሯል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኮቪድ-19 ወረርሽኝና ሌሎች ችግሮች ለኢንዱስትሪው የገበያ መቀዛቀዝ ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት […]

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ ምክክሩን በሃላፊነት የሚመሩትን የ11 እጩ ኮሚሽነሮችን ሹመት አጸደቀ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 ምክር ቤቱ በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባት ለመፈጠር ያስችላል የተባለው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265 /2014 ማጽደቁ ይታወሳል። በዚህም መሰረት አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን የሚመሩት 11 ኮሚሽነሮች ለመለየት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ የጥቆማ ዘዴዎች ከ600 በላይ ሰዎች ተጠቁመዋል። ከተጠቆሙት ግለሰቦች መካከል 42ቱ አዋጁን መሰረት ተደርጎ መለየታቸውና […]

የግል ባንኮች ለቀጣዩ ፉክክር ራሳችሁን አዘጋጁ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2014 በኢትዮጵያ የሚገኙ የግል ባንኮች ራሳቸውን ለውድድር እንዲያዘጋጁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ወቅት በሰጡት ማብራሪያ የግል ባንኮች በዘርፉ እድገት ያስመዘገቡ ቢሆንም አሁንም ብዙ ስራዎች እንደሚጠብቃቸው ገልጸዋል፡፡ በተለይ እስካሁን የግል ባንኮች የውጭ ሀገራት የፋይናንስ ተቋማት ፈቃድ […]

አሜሪካ የትግራይ ታጣቂዎች በአማራ ክልል የፈጸሟቸው ዘግናኝ ድርጊቶች በእጅጉ አሳስበውኛል ስትል ገለጸች፡፡

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 አሜሪካ የትግራይ ታጣቂዎች በአማራ ክልል የፈጸሟቸው ዘግናኝ ድርጊቶች በእጅጉ አሳስበውኛል ስትል ገለጸች፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአመንስቲ አንተርናሽናልን ሪፖርትን መነሻ አድርጎ ባወጣው መግለጫ በክልሉ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ የተፈጸሙ በርካታ ወንጀሎች አሳሳቢ ናቸው ብሏል፡፡መግለጫው አክሎም በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው አሰቃቂ ግፍና ወንጀል በሚገባ ተጣርቶ የድርጊቱፈጸሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥር አቅርቧል፡፡ የትኛውም የታጠቀ […]

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለመሥጠት እየሰራሁ ነው አለ፡፡

አዲስ አበበ፣ የካቲት 16፣ 2014 ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለመሥጠት እየሰራሁ ነው አለ፡፡ ኩባንያው ይህን የገለጸው በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያስገነባቸውን መሰረተ ልማቶችና የዳታ ቤዝ ማእከሉን ለጋዜጠኞች ባስጎበኘበት ወቅት ነው፡፡ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለመሥጠት እየሰራ መሆኑን የኩባንያው የውጭ ጉዳይና የቁጥጥር ኦፊሰር ማቴ ሃሪሰን ሃርቬይ ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ጨረታውን ማሸነፉን […]