loading
ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት እርዳታ ተስተጓጉሏል

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት እርዳታ ተስተጓጉሏል አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ መቀሌ ሲጓዙ የነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደኋላ ለመመለስ መገደዳቸው ተገለፀ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ህወሓት በአፋር በኩል እየፈፀመ ባለው ትንኮሳ እና ወደ መኖሪያ አካባቢዎች […]

የወይብላን ጉዳይ ለማጣረት በግብርኃይል እየተመረመረ ነው- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን የተፈጸመውን ድርጊት ግብርኃይል ተቋቁሞ እየመረመረ እንደሚገኝ መንግሥት አስታወቀ፡፡የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ ግብርኃይሉ ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጣ እንደሆነ ገልጸው ውጤቱ ሲደርስ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡ ሌሎች […]

አሸባሪው ህወሓት እንደ አዲስ ከወረራቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጣና በቀጠናው የከፈተውን ጦርነት እንዲያቆም የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሳሰበ።

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 አሸባሪው ህወሓት እንደ አዲስ ከወረራቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጣና በቀጠናው የከፈተውን ጦርነት እንዲያቆም የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሳሰበ።የክልሉ መንግስት በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ ከሰሞኑ አሸባሪው ቡድን በተደራጀ መልኩ በአብአላ፣ በመጋሌና ኤረብቲ ወረዳዎችን በመቆጣጠር እና በራህሌ ወረዳንም ከፊል ቀበሌዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት ከባድ ጥቃት ከፍቶ ንፁሀንን በመግደል እና በማሳደድ ወረዳዎቹን እያወደመ እንደሚገኝና […]

በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የሕክምና ድጋፎች ለመስጠት አንድ መቶ በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ወደ አማራ ክልል አቀኑ።

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የሕክምና ድጋፎች ለመስጠት አንድ መቶ በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ወደ አማራ ክልል አቀኑ። የሕክምና ባለሙያዎቹ ከጥር 22 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል የሕክምና ምርመራ፣ ሕክምናና የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፤ መድኃኒትም ያቀርባሉ ተብሏል። በጎ ፍቃደኞቹ የሕክምና ድጋፋቸውን የሚሰጡባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ሸዋሮቢት፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ […]

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ።

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የ2014 በጀት ዓመት የተቋሙን የ6 የስራ አፈፃፀም በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በ6 ወራት ብቻ ከቴሌኮም አገልግሎት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል።ተቋሙ በስድስት ወራት ካገኘው ገቢ መካከል 50 ነጥብ 4 በመቶው ከድምጽ እንዲሁም 28 ነጥብ 8 በመቶው ከኢንተርኔት አገልገሎት የተገኘ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ […]

በአንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ ያደረሰው ጉዳት ወደ ሰው እንዳይሸጋገር እየተሰራ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከአጋር አካላት ጋር በመሆንድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ በሶማሌ ክልል 9 ዞኖችበተከሰተው የድርቅ አደጋ 960 ሺህ በላይ ዜጎች ተጎጂ በመሆናቸው የእለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ በክልሉ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች የእለት ደራሽ ድጋፍ ይፈልጋሉ […]

እያንዳንዳቸው 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ቅጣት የተወሰነባቸው የንግድ ተቋማት…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 ግብይት ሳይኖር የደረሰኝ ሽያጭ ሲፈፅሙ የነበሩ 2 ድርጅቶችና 3 ግለሰቦች ከባድ የቅጣት ዉሳኔእደተላለፈባቸው ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ቅጣቱ የተወሰነባቸው አባቢን ኮንስትራክሽን እና ማሽነሪ ኪራይ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እናዲን ጀነራል ትሬዲንግ የተባሉ ድርጅቶች መሆናቸውን ሚስቴሩ ገልጿል፡፡ ከንግድ ተቋማቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 3 ግለሰቦችም የገንዘብና የእስር ቅጣትተወስኖባቸዋል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡ አቶ ቢኒያም […]

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከአቶ ሙስጠፌ ሞሐመድ እና ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ተወያዩ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከአቶ ሙስጠፌ ሞሐመድ እና ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር በአካባቢውበተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ተወያዩ። ፕሬዚዳንቷ ከ.ተ.መ.ድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ሞሐመድና የልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆንበሶማሌ ክልል ጉብኝት አድርገዋል። በቀብሪ በያ ባደረጉት የመስክ ጉብኝት በድርቁ የተነሳ ከተፈናቀሉት ወገኖች ጋር ተገናኝተዋል። የአካባቢው ሕዝብ ለተጎዱት ወገኖቹ የመጀመርያ ደራሽ በመሆን ላሳየው ታላቅነት እንዲሁም […]

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀገራችን ተቋማትን መገንባትና ለትውልድ ማሸገጋር እንደምትችል ማሳያ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀገራችን ተቋማትን መገንባትና ለትውልድ ማሸገጋር እንደምትችል ማሳያ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የባንኩን የ80ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓልና ያስገነባውን ዘመናዊ ህንፃ ማስመረቁን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ነው፡፡ ባንኩ ያስገነባውን ባለ 53 ወለል ህንፃ በሚያስመርቅበት ወቅት ተገኝተው ባደረጉት ንግግርም […]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ ከ96 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙ ከ96 በመቶ በላይ መድረሱን አስታወቀ፡፡ኤጀንሲው መረጃውን ይፋ ያደረገው የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ኤጀንሲው የሳይበር ጥቃቶችን ቅድመ መከላከል፣ ጥቃት የደረሰባቸውን መልሶ ወደ ነበሩበት ስራ የመመለስ አቅሙ አድጓል ብለዋል። ባለፉት ስድስት ወራት ከሶስት ሺ […]