loading
ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ ከተለያዩ ሀገራት የተጠሩ 60 የኢትዮጵያ አምባሳደሮችን ሊያወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ ከተለያዩ ሀገራት የተጠሩ 60 የኢትዮጵያ አምባሳደሮችን ሊያወያዩ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ውይይቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለተደረገው ሪፎርም ፣ ባለፉት 10 ወራት በተገኙ የዲፕሎማሲ ውጤቶች እና ቀጣይ የውጭ ጉዳይ ተልዕኮ ላይ የሚያተኩር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ይበልጥ ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ ፣ከዳያስፖራው […]

በግመል የኮንትሮባንድ ንግድ ሲካሄድ ተያዘ።

ግምታዊ ዋጋቸው 937ሺህ 912 የሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ለኮንትሮባንድ ክትትል ቡድን በደረሰ ጥቆማ መሠረት በዚህ ሳምንት መያዛቸውን በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡ አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች እንዲሁም ሲጋራዎች በግመል ተጓጉዘው ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጀርባ በተለምዶ መርመርሳ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በተራገፈበት በጉምሩክ ሠራተኞች፣ በፌደራል እና በድሬዳዋ አድማ ብተና ፖሊሶች አማካኝነት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የቅ/ጽ/ቤቱ […]

አቡነ መርቆሬዎስ ጎንደር ላይ ሊቃውንት በተገኙበት አቀባበል ተደረገላቸው፡፡

ጎንደርን ከ10 ዓመታት በላይ በጵጵስና ያገለገሉትና ከመንበረ ጵጵስናቸው ተነስተው በግዞት ቆይተው የተመለሱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዛሬ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ሊቃውንት እና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ አቡነ መርቆሬዎስ ከ1971 እስከ 1980 ዓ.ም በጎንደር ሀገረ ስብከት በሊቀጵጵስና ቆይታቸው ዘመን ተሻጋር ስራዎች እንደሰሩ ይነገራል፡፡ የ አማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደዘገበው […]

የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ሙዚየም ዛሬ ተመረቀ።

የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ሙዚየም ዛሬ ተመረቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምህረት አንድነት ገዳም ሙዚየምን ዛሬ አስመረቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅርሶችን ጠብቃና ተንከባክባ እዚህ አድርሳለች ብለዋል። አሁን ያለው […]

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰላም በሚል መሪ ቃል ኮንፈረንስ ተካሄደ።

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰላም በሚል መሪ ቃል ኮንፈረንስ ተካሄደ። በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመጀመሪያው የሰላም ኮንፈረንስ ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተካሂዷል። ”ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሰላም” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ኮንፍረንስ ላይ ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተወከሉ የአስተዳደር አካላትና ተማሪዎች ተሳትፈዋል። የሰላም ሚኒስትር ዴእታ ወይዘሮ አልማዝ መኮነን በኮንፈረንሱ ላይ፥ ሀገራችን ከበርካታ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ውህደት የተገነባች በመሆኗ አንዳችን ላንዳችን […]