loading
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ምርመራ 1 መቶ 42 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸዉ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ምርመራ 1 መቶ 42 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸዉ፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት ባለፉት 24 ሰዓታት ዉስጥ በተደረገዉ የ4 ሺህ 1መቶ 20 የላብራቶሪ ምርመራ 1 መቶ 42 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 4 መቶ 86 ደርሷል፡፡ቫይረሱ […]

ፔፕሲኮ ኢትዮጵያ “ ምግብ ይለግሱ -ተስፋን ይቀጥሉ “የሚል ፕሮግራም ይፋ አደረገ ፡፡

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27፣ 2012 ፔፕሲኮ ኢትዮጵያ “ ምግብ ይለግሱ -ተስፋን ይቀጥሉ “የሚል ፕሮግራም ይፋ አደረገ ፡፡በፕሮግራሙም 2 ሺህ ሰዎችን ለሶስት ወራት ምሳና እራት እንዲመገቡ ይደረጋል፡፡ድርጅቱ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንደስታወቀዉ ፤ ድጋፉ በኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ስርጭት ምክንያት ለተጎዱና ጫና ለደረሰባቸዉ አካላት የሚዉል ሲሆን 8ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡ድርጅቱ ድጋፉን ከሜቅዶንያ በጎ አድራጎት ተቋም ጋር […]

ብራዚል በ24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ ተባለውን የኮሮናቫይረስ ሞት አስመዘገበች፡፡

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27፣ 2012 ብራዚል በ24 ሰዓታት ውስጥ ከፍተኛ ተባለውን የኮሮናቫይረስ ሞት አስመዘገበች፡፡ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ለማንሳት እየተንቀሳቀሰች ያለችው ብራዚል ለሁለት ተከታታይ ቀናት በርካታ ዜጎቿ እንደሞቱባት ተገልጿል፡፡ አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው በብራዚል በአንድ ቀን ብቻ 1 ሺህ 349 ሰዎች በኮቪድ 19 ምክንያት ህይዎታቸው ማለፉ ተረጋግጧል፡፡ ብራዚል እስካሁን ከ32 ሺህ 500 በላይ ዜጎቿ የሞቱባት ሲሆን በበሽታው የተያዙት […]

ትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ከመደበችው በጀት 40 በመቶውን ለክትባት ታውላለች አሉ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 ኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ከመደበችው በጀት 40 በመቶውን ለክትባት ታውላለች አሉ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፡፡ ፕሬዝደንቷ ይህን ያሉት የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በጠሩት ዓለም አቀፍ የክትባት ጉባኤ ላይ ላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ ከመደበችው በጀት መካከል በዚህ መጠን ለማዋል መነሳቷ መንግስት ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት መስጠቱን እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡ የበርካታ ሀገራትና መንግሥታት […]

ይህን ክፉ ጊዜ ያለው ለሌለው በማጋራት በመተጋገዝ ልናልፈው ይገባል-አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2012 ይህን ክፉ ጊዜ ያለው ለሌለው በማጋራት በመተጋገዝ ልናልፈው ይገባል-አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፡፡ ይህን ክፉ ጊዜ ለማለፍ እርሾ ለሚያጥራቸው ጎረቤቶች ያለው ለሌለው በማጋራት ማለፍ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ጥሪ አቅርበዋል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመኖሪያ አካካቢያቸው ለሚገኙ ከ114 በላይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የተለያዩ ምግብ ነክ ድጋፎችን አበርክተዋል።  አቶ […]

ኒው ዚላንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ አለማስመዝገቧን ተከትሎ ክልከላዎችን በሙሉ ልታነሳ ነው ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 ኒው ዚላንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ አለማስመዝገቧን ተከትሎ ክልከላዎችን በሙሉ ልታነሳ ነው ::የኒው ዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን በሀገራቸው ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች እንዴሌሉ ተናግረው ከእንግዲህ አካላዊ መራራቅን እንጅ እንቅስቃሴን አንገድብም ብለዋል፡፡ ይሁን እንጅ ከውጭ የሚገቡ ዜጎቻችን ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ማድረግ የግድ ይላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሯ ለተገኘው ውጤት ሁሉንም ዜጎቻቸውን […]

ግብፅ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 47 ዶክተሮቿን በሞት ማጣቷ ትልቅ ስጋት ሆኖባታል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2 ፣ 2012 ግብፅ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 47 ዶክተሮቿን በሞት ማጣቷ ትልቅ ስጋት ሆኖባታል ተባለ::የብግብፅ የህክምና ማህበር በሰጠው መግለጫ የሀገሪቱ የጤና አጠባበቅ ስርዓት በፍጥነት ካልተስተካከለና ለሀኪሞች ልዩ እንክብካቤ ካልተደረገላቸው የበለጠ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ብቻ በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሰባት ዶክተሮች መሞታቸው ሁኔታው ምን ያህል አደገኛ እየሆነ መምጣቱን ያሳያል ነው የተባለው፡፡ ከሁለት […]

ኬንያዊያን ፖሊስ በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን ግድያ ያቁም የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ነው::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2 ፣ 2012 ኬንያዊያን ፖሊስ በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚፈፅመውን ግድያ ያቁም የሚል ተቃውሞ እያሰሙ ነው:: በኬንያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የተጣለውን የእንቅስቃሴ እገዳ ተከትሎ ፖሊስ ህግ በማስከበር ሰበብ በርካታ የሰብዓዊ መብቶችን እየጣሰ እንደሆነ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ሰዎች ተናግረዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው መንግስት እገዳውን ከጣለ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በፖሊስና በነዋሪዎች መካከል በተከሰቱ ግጭቶች ከ15 ያላነሱ […]

የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በልብ ህመም በድገንገት ህይዎታቸው አለፈ ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3 ፣ 2012የብሩንዲው ፕሬዚዳንት ፒዬር ንኩሩንዚዛ በልብ ህመም በድገንገት ህይዎታቸው አለፈ ::የብሩንዲ መንግስት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ፕሬዚዳንቱ በልብ ህመም መሞታቸው ተረጋግጧል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ቅዳሜ በአንድ የቮሊቦል ጨዋታ ውድድር ላይ ታድመው የነበረ ሲሆን በዚያው ምሽት ታመው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ የጤናቸው ሁኔታ መሻሻል አሳይቶ የነበረ ቢሆንም ሰኞ እለት በተደረገላቸው […]

የኮሮና ቫይረስ  በ164 ሰዎች ላይ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012  የኮሮና ቫይረስ  በ164 ሰዎች ላይ ሲገኝባቸው፤ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 630 የላብራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 670 መድረሱንም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት አመላክተዋል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው […]