loading
6 ሰዓታትን የፈጀ ስኬታማ ቀዶ ህክምና-በኢትዮጵያ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 የልብ የደም ስር ነቅሎ መትከል እና የልብ በር ቀዶ ህክምና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ መካሄዱን የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሐኪም ገለጹ፡፡ ቀዶ ህክምናው 6 ሰዓታትን የፈጀ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ቀዶ ህክምናውን ለየት የሚያደርገው የልብ የደም ስር ነቅሎ መትከል እና የልብን በር ቀዶ ህክምና በአንድ ላይ መደረጉ መሆኑን በጥቁር አንበሳ የልብ ማዕከል የልብ […]

በኒውዚላንድ አንድ የኮቪድ-19 ተጠቂ መገኘቱን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዕቀባ ተጣለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 12፣2013 በኒውዚላንድ አንድ የኮቪድ-19 ተጠቂ መገኘቱን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ ገደብ መጣሉ ተነገረ፡፡በኒው ዚላንድ በስድስት ወር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ ኦክላንድ ውስጥ አንድ ሰው የኮቪድ-19 ተህዋሲ ተጠቂ መሆኑን ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ ከሶስት ቀን እስከ ሳምንት የሚደርስ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ታውቋል። በተህዋሲው የተያዘው ሰው የተጎበኘችው የባህር ዳርቻዋ ከተማ ኮሮማንዴል እንደ ኦክላንድ ሁሉ ለሰባት ቀናት […]

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣2013 በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት 2 ሺህ 95 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ10 ሺህ 804 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 2 ሺህ 95 ሰዎች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል።13 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን፤ 532 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህክምና […]

አሁንም ትኩረት የሚያሻው የኮቪድ-19 ስርጭት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ በመግለጫው እንዳለው ምርመራ ከተደረገላቸው 13 ሺህ 280 ሰዎች መካከል 5 ሺህ 185 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።ይህም እስካሁን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 405 ሺህ 745 ከፍ እንዳደረገው ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡ በሌላ […]

በአንድ ሳምንት ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 በአንድ ሳምንት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር ተመዘገበ ከዲሴምበር 22 እስከ 28 ባለው ጊዜ በየቀኑ በአማካይ 935 ሺህ ገደማ ሰዎች በቫይረሱ ይያዙ እንደነበር አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ በዓለማቸው በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ይህም በሽታው ከተከሰተ ወዲህ ትልቁ ቁጥር ነው ተብሏል፡፡ መረጃዎች […]

ህብረተሰቡ ሁለተኛውን ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ወደ ክትባት መስጫ ጣቢያዎች በመቅረብ እንዲከተብ ጥሪ ቀረበ

የሁለተኛዉ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ዘመቻ እድሚያቸው 12 አመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሁሉ በመንግስት ጤና ተቋማትና በጊዚያዊ ክትባት መስጫ ጣቢያዎች ከየካቲት 7 እስከ 16/2014 ዓ.ም መስጠት ተጀምሯል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶር ዮሃንስ ጫላ በሰጡት መግለጫ እንዳሳዎቁት፤እስካሁን ሰባት ሺህ 426 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በወረርሽኙ ህይወታቸው አልፏል። ክትባቱን ተደራሽ ከማድረግ አንጻርም፤ እስካሁን […]

በሴት የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የቀዶ ሕክምና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 በሴት የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የቀዶ ሕክምና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ:: ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በሴት የሕክምና ባለሙያዎች ብቻ የተመራ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ሰጠ፡፡ ሆስፒታሉ በሴት ሐኪሞች ብቻ በሚመራው በዚህ መርሀ ግብሩ ለ23 ያህል ሕሙማን ቀዶ ሕክምና እሰጣለሁ ብሏል፡፡ የሴቶች ሕክምና ቡድኑን የሚመሩት ዶ/ር መሰረት ሕይወቴ የቀዶ ሕክምና […]

የወባ በሽታን ከሀገሪቱ ለማጥፋት ህብረተሰቡ የወባ ማስወገድ አፈጻጸም መመሪያዎችንና መከላከያ ዘዴዎችን በአግባቡ ሊተገብር እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 የወባ በሽታን ከሀገሪቱ ለማጥፋት ህብረተሰቡ የወባ ማስወገድ አፈጻጸም መመሪያዎችንና መከላከያ ዘዴዎችን በአግባቡ ሊተገብር እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡ የወባ ቀንን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ 75 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ መልክዐ ምድር ለወባ በሽታ ስርጭት አመቺ መሆኑን ጠቅሰዋል። 52 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ ህዝብ በእነዚህ አካባቢዎች እንደሚኖር ተናግረዋል። በወባ […]

ሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ከግንቦት ወር መጨረሻ ሳምንት ጀምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች መሰጠት ሊጀምር ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 ሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ከግንቦት ወር መጨረሻ ሳምንት ጀምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች መሰጠት ሊጀምር ነው፡፡ በሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከ25 ሚሊዮን ዶዝ በላይ ለመከተብ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታው ዶክተር ደረጀ ድጉማ በተለይ ሁለተኛው ዙር የኮቪድ-19 ዘመቻ እንደ ሀገር በርካታ ጠንካራ […]

አንዲት በጎ አድራጊ ግለሰብ ለዘውዲቱ ሆስፒታል ዘመናዊ የአምቡላንስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 አንዲት በጎ አድራጊ ግለሰብ ለዘውዲቱ ሆስፒታል ዘመናዊ የአምቡላንስ ድጋፍ አደረጉ፡፡ የዘውዲቱ ሆስፒታል ፋርማሲስት የሆኑት ወይዘሮ ሃና ልካስ ለሆስፒታሉ ያደረጉት የአምቡላንሶ ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ሲሆን፥ በተለይ በእርግዝና ላይ ያሉ እናቶች አስፈላጊውን የህክምና ድጋፍ እያገኙ ወደ ሆስፒታል እንዲደርሱ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡ አምቡላንሱ ዘመናዊ የመተንፈሻ ቬንትሌተር የተገጠመለት ሲሆን፤በተለይ እናቶች […]