loading
የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣን የሚያስረክብበትን ቀነ ገደብ አራዘመ፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣን የሚያስረክብበትን ቀነ ገደብ አራዘመ፡፡ የአፍሪካ መሪዎች በሱዳን እና በሊቢያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ካይሮ  ላይ በተገናኙበት ወቅት ነው ውሳኔው የተላለፈው፡፡ ህብረቱ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ ወታደራዊ ምክር ቤቱ በ15 ቀናት ውስጥ ስልጣኑን ለሲቪል የሽግግር መንግስት እንዲያስረክብ ይህ ባይሆን ግን ሱዳን ከህብረቱ እንደምትባረር አስጠንቅቆ ነበር፡፡ የግብፁ የዜና ወኪል ሜና […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የልዑካን ቡድናቸው ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ጋር ከቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ በፊት የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ የጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድን አመራርና ያለፈውን አንድ ዓመት የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት እንደሚያደንቁ የገለጹት ፕሬዚዳንት ዥንፒንግ ቻይና ለኢትዮጵያን ዕድገት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች ብለዋል:: በውይይቱ ወቅትም እስከ የፈረንጆች 2018 ዓ.ም መጨረሻ የተጠራቀመ የብድር ወለድን ሙሉ በሙሉ እንደተሠረዘ አስታውቀዋል:: ከዚሁም […]

ልጣን ላይ ያሉትና የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎች ለ8ኛዉ የጣና ከፍተኛ የደኅንነት ፎረም ባህር ዳር ከተማ ሊገናኙ ነው

በስልጣን ላይ ያሉትና የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎች ለ8ኛዉ የጣና ከፍተኛ የደኅንነት ፎረም ባህር ዳር ከተማ ሊገናኙ ነው። መሪዎቹ ባህር ዳር የሚገናኙት በአፍሪካ ቀንድ ሁኔታዎች ላይ ለመምከር ነው። ”የፖለቲካ ተለዋዋጭነት በአፍሪካ ቀንድ እና የታዩ የሠላም ጅማሮዎችን ማጎልበት” በሚል መሪ መልክዕት የሚካሄደው ይኸው ፎረም ከሚያዚያ 26-27 ድረስ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ነው ማወቅ የተቻለው። የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር […]

የሶማሊያው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ስልጣን በቃኝ አሉ፡፡

የሶማሊያው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ስልጣን በቃኝ አሉ፡፡

የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ ዳሂር ሞሀመድ ጊሌ ሀላፊነታቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁት ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ፋርማጆ በሚመሩት የፌደራል አስተዳደር  የሀሳብ ልዩነት ስላላቸው ነው ተብሏል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የጊሌ የመልቀቂያ ደብዳቤ እንደደረሰው እና ጥያቄቸውን መቀበሉን ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡

ዳሂር ሞሀመድ ጊሌ ከ11 ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ሀሰን ካይር ነበር የሶማሊያ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት፡፡

የጊሌን ከሀላፊነታቸው መልቀቅ ተከትሎ የንግድ ሚኒስትሩ አብዲ ሃይር ማሪየ በቦታቸው የተተኩ ሲሆን የሳቸውን ቦታ ደግሞ አብዱላሂ አሊ ሀሰን እንዲይዙት ተደርጓል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

የሶማሊያው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ስልጣን በቃኝ አሉ፡፡

ዳሂር ሞሀመድ ጊሌ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ጋር አልተስማሙም፡፡

ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አደነቁ፡፡ ፕሬዝዳንቱ  የዓለም ባንክ  ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ትብብር  አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት አደነቁ፡፡ ፕሬዝዳንቱ  የዓለም ባንክ  ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ትብብር  አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡