loading
ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ ሰባት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በግንባር ለመስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ። ሰነዱን የተፈራረሙት የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት (ኢዴህ)፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ)፣ የአፋር ህዝቦች ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአፋር ህዝቦች ነፃነት ፓርቲ እና የኦሮሞ ህዝቦች ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ […]

የትራምፕ እና ኪም ድርድር ያለስምምነት ተቋጨ፡፡

የትራምፕ እና ኪም ድርድር ያለስምምነት ተቋጨ፡፡ የዓለምን ህዝብ ትኩረት ስቦ የነበረው የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ሁለተኛ ዙር ውይይት ያለውጤት ለመበተኑ ምክንያት የኪም ማእቀብ ይነሳልኝ ጥያቄ መልስ በማለማግኘቱ መሆኑን ሲ ኤን ኤን ከስፍራው ዘግቧል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ግን ሁሌም እንደምለው መቻኮል አያስፈልግም ዋናው ነገር ብዙ ጠቃሚ ሀሳቦችን ተለዋውጠናል በማለት ነገሩን ለማለዘብ ሞክረዋል፡፡ ከአሁኑ ስብሰባ ብዙ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስዊዲን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስዊዲን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ተወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስዊዲን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ማርጎት ቫለርስትሮም ጋር ዛሬ ጠዋት ተገናኝተው ተወያይተዋል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ዘግቧል፡፡ ሁለቱ ወገኖች በኢትዮ ስዊዲን ትብብር ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን ቫለርስትሮም ስዊዲን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል በድጋሜ አረጋግጠዋል ተብሏል።

ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከዛሬ  በኢትዮጵያ ጉብኝት ላይ ናቸው

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከዛሬ  ጀምሮ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት  ጉብኝት ያደርጋሉ የኬንያው ፕሬዝዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ ከዛሬ  ጀምሮ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት  የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በሁለቱ አገሮች መካከል ለዘመናት የቆየውንና በሁኔታዎች የማይለዋወጠውን ታሪካዊ ግንኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ተብሏል። ኡሁሩ ኬንያታ የአፍሪካ አባት በመባል የሚታወቁት የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት  ጄሞ ኬንያታ […]