Africa

ግብፅ በሁለት ሳምንታት ውስጥ 35 ዶክተሮቿን በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ማጣቷን የሀገሪቱ የህክምና ማህበር ገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 ግብፅ በሁለት ሳምንታት ውስጥ 35 ዶክተሮቿን በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ማጣቷን የሀገሪቱ የህክምና ማህበር ገለጸ::
ባለፈው ማክሰኞ ዶክተር ዋስፊ የተባሉ የቆዳ ስፔሻሊስት ሀኪም በሳዳር አል አባሲያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ መሞታቸው የተሰማ ሲሆን በሰዓታት ልዩነት የህፃናት ሃኪም የሆኑት ዶክተር ራኒያ ፉአድ አልሰይድ ህልፈት ተሰምቷል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር የህክምና ማህበሩን ጠቅሶ እንደዘገበው ግብፅ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ወደ 500 የሚጠጉ ዶክተሮቿ በኮቪድ-19 ምክንያት ሞተውባታል፡፡ በግብፅ በኮሮናቫይረስ የሚሞቱ ሃኪሞች ቁጥር ከአሜሪካ ጋር ሲነፃፀር በ6 እጥፍ እንደሚበልጥም ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡
ወረርሽኙ በሀገሪቱ መስፋፋት ከጀመረ አንስቶ ሀኪሞቹ በሽታው እንዳይጋባባቸው የሚከላከሉባቸው መሳሪያዎች እጥረት እንዳለባቸው ለመንግስት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ጥሩ ምለሽ አላገኙም ተብሏል፡፡

በሀገሪቱ የታማሚዎችም ይሁን የሟቾች ቁጥር በይፋ ከሚነገረው ይበልጣል የሚል ትቸት የሚነሳ ሲሆን ይህን በግልፅ የሚናገሩ የህክምና ባለሙያዎች እስከመታሰር ደርሰዋል ነው የሚባለው፡፡ግብፅ እስካሁን በኮሮናቫይረስ የተያዙባት ዜጎቿ ቁጥር ከ249 ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን ከነዚህ
መካከል 14 ሺህ 498 የሚሆኑት ህይዎታቸው ማለፉ ተረጋግጧል፡፡ ባለፉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ብቻ 9 ሺህ 111 ግብፃዊያን በቫይረሱ ሲያዙ 407 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button