loading
የኤፍ ኤ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ ይከናወናሉ

የ2018/19 የኤፍ ኤ ኤመሬትስ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያዎች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት፤ ቡድኖች ወደ ፍፃሜ ዋንጫ ለማለፍ እያለሙ ይጫወታሉ፡፡ በነገው ዕለት የአራትዮሽ ዋንጫ ግስጋሴው ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ከብራይተን ኤንድ ሆቭ አልቢዮን ጋር በግዙፉ ዌምብሌይ ይጫወታል፡፡ ከአራቱ ዋንጫዎች የካራባዎ ዋንጫ ጉዞን በድል የፈፀመው የፔፕ ጓርዲዮላው ቡድን፤ ከክሪስ ሁተኑ ክለብ በኩል ጠንከር ያለ አጨዋወት ሊጠብቀው እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ […]

በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በኢትዮጵያውያን የተመዘገቡ የሩጫ ውጤቶች

በኔዘርላንድስ ሮተርዳም ማራቶን በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አሼቴ በከሬ በ2፡22፡55 ስታሸንፍ፤ ኬንያዊቷ ስቴላ ባሮሲዮ 2፡23፡36 ሁለተኛ እንዲሁም ሌላኛዋ ኬንያዊ አትሌት አሊፍን ቱሊያሙክ በ2፡26፡50 ሶስተኛ አትሌት ቤተልሔም ሞገስ አራተኛ ደረጃ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡ በወንዶች ኬንየዊው ማሪዩስ ኪፕሴሬም ፤ ቱርካዊው ካን ኦዝቢሌን እና ኢማኑኤል ሳይና ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ ኬንያዊያን የበላይነት በነራቸው የሚላን ማራቶን በሴቶች ቪቪያን ኪፕላጋት […]

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ወጣቶች አትሌቲክስ ቡድን ሽልማት ተበረከተለት

በምስራቅ አፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀዉና በሩዋንዳ ኪጋሊ አስተናጋጅነት በ5 የስፖርት አይነቶች ማለትም በአትሌቲክስ፣ ብስክሌት፣ ቴኳንዶ፣ የዉሃ ዳር መረብ ኳስ እና ቅርጫት ኳስ ስፖርቶች ከመጋቢት 24 እስከ 28 በሩዋንዳ በተካሄደው፤ የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች የዞን 5 ሀገሮች የወጣቶች ጨዋታ በአትሌቲክስ ስፖርት ተሳትፎ ትልቅ ውጤት ይዞ የተመለሰው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ወጣት አትሌቶች ልኡክ፤ የእውቅና እና ሽልማት […]

የአውሮ ቻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይከናወናሉ

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ግጥሚያዎች ዛሬ ይጀመራሉ፡፡ ዛሬ ምሽት 4፡ 00 ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ሁለት ጨዋታዎች ሲከናወኑ፤ ሶስት የእንግሊዝ ክለቦች ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ የፖርቱጋሉ ክለብ ፖርቶ ወደ እንግሊዝ ምድር ተጉዞ በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ከሊቨርፑል ጋር ይፋጠጣል፡፡ በጥሎ ማለፉ ውድድር ቀያዮቹ ባየርን ሙኒክን እንዲሁም ፖርቶ የጣሊያኑን ሮማ በመጣል ነው ለዚህ ዙር መብቃት የቻሉት፡፡ በምሽቱ ጨዋታ […]