loading

በእጅ የሚገፋ ማረሻ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የአፈርን አሲዳማነት የሚያክምና አፈርን የሚያዳብሩ ሁለት የምርምር ውጤቶች በሙከራ ላይ መሆናቸውንም ገልጿል ፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር እንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ባለፉት አመታት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በዘርፉ ለሀገሪቱ መሰረት የሚሆኑ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በግብርናዉ  ዘርፍ በእጅ የሚገፋ ማረሻ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ፤ የአፈርን አሲዳማነት […]

ስድስት የዕሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖችን ከደቡብ አፍሪካ ሊመጡ ነው።

ስድስት የዕሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖችን ከደቡብ አፍሪካ ሊመጡ ነው።   የኬንያ መንግስት የተጠየቀውን የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ አውሮፕላኖች ድጋፍ ማድረግ ያልቻለው በኬኒያ ፓርኮች ላይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በመነሳቱ መሆኑን አስታውቃል።   በሰሜን ተራሮች ላይ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ሳቢያ የኢትዮጵያ መንግስት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የደቡብ አፍሪካ መንግስት 6 የዕሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖችን ለመላክ መስማማቱ ተነግሯል።   […]

ፌዴራል ፖሊስ በሙስናና በኢኮኖሚ አሻጥር ወንጀሎች  የጠረጠራቸውን 61 የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር አዋለ

ፌዴራል ፖሊስ በሙስናና በኢኮኖሚ አሻጥር ወንጀሎች  የጠረጠራቸውን 61 የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር አዋለ። ከታሳሪዎቹ መካከል የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደርና አወጋገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባ ይገኙበታል ተብሏል። አዲስ ፎርቹን ድረገጽ እንደዘገበው ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን  በቁጥጥር ስር ያዋለው ከትናንት ማለዳ ጀምሮ ባካሄደው ዘመቻ ነው። በቁጥጥር ሰር ከዋሉት ባለስልጣናት ውስጥ የቀደመው የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ የግዢና ንብረት […]

ኮካ ኮላ ከምርት ሽያጩ ያሰባሰበውን ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች መለገሱን አስታወቀ

ኮካ ኮላ ከምርት ሽያጩ ያሰባሰበውን ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች መለገሱን አስታወቀ ኩባንያው ይህንን ያስታወቀው በቅርቡ ተካሂዶ የነበረውን የኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ ሙዚቃ ፕሮግራም ይፋዊ መዝጊያ ስነስርዓት ባካሄደበት ወቅት ነው። ሃሙስ ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው በዚሁ ስነስርዓት ላይ እንደተገለጸው ኩባንያው የገንዘብ ድጋፉን ያደረገው የሴቶችና ህጻናት ልማት ድርጅት፣ ታለንት የወጣቶች ማህበር እና የሴቶች […]

ኢትዮጵያ የቡድን 77 እና ቻይና ሊመንበርነቷን በስኬት ማጠናቀቋ ተገለጸ

ለአንድ ዓመት የዘለቀውን የቡድን 77 እና ቻይና የናይሮቢ ቻፕተር ሊቀመንበርነቷን በስኬት ማጠናቀቋን አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው ኢትዮጵያ ለዚህ ተቋም ስኬት ጠንክራ እንደምትሰራ ቃል ገብታለች። የቡድን 77 እና ቻይና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 134 የአፍሪካ፣ ኤዥያ እና ላቲን አሜሪካ አገራትን ያጠቃለለ ጠንካራው ስብሰባው ነው። ቡድኑ በዓለም አቀፍ መድረኮች ለታዳጊ አገሮች […]

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በመጋቢት ወር የ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የግብርና ምርቶችን አገበያየ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በመጋቢት ወር 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው 84 ሺህ ቶን የግብርና ምርቶችን ማገበያየቱን አስታወቀ። አንድ የመገበያያ ወንበር በ3.5 ሚሊዮን ብር ሸጧል። በቅርቡ ወደ ዘመናዊ የግብይት ስርዓት የተቀላቀለው አኩሪ አተር ግብይት በመጋቢት ወር ብቻ የ47 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ ምርት ገበያው ለአርትስ ቲቪ በላከው  መግለጫ እንዳስታወቀው በመጋቢት ወር 21 ሺህ ቶን አኩሪ አተር […]

108 ሰዓሊያን ከ2ሺህ በላይ ስራዎቻቸውን ለሽያጭ ያቀርባሉ

ከሚገኘው ገቢ አቅም የሌላቸውን ታማሚዎችን ለመደገፍ ቃል የተገባበት  የስዕል አውደ ርዕይ እየተዘጋጀ ነው በአውደርዕዩ 108 ሰዓሊያን ከ2ሺህ በላይ ስራዎቻቸውን ለሽያጭ ያቀርባሉ ዋትስ አውት ሚድያ ከሄልተን ሆቴል ጋር በጋራ በመሆን The Big Art Sale  የተሰኘ የስዕል አውደ ርዕይ ሚያዚያ 12 ቀን   በሂልተን  ሆቴል  ግቢ ሊያዘጋጅ ማቀዱን  በሰጠው ጋዜጣዊ  መግለጫ አስታውቋል ፡፡ የዚህ አውደ ርዕይ ዋና አላማ  […]