loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ለፍልስጤማዊው ወጣት ሞት ይቅርታ ጠየቁ ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ለፍልስጤማዊው ወጣት ሞት ይቅርታ ጠየቁ :: የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታያሁ ለወጣቱ እናት የይቅርታ መልእክታቸውን ያተላለፉት ከተገደለ አንድ ሳምንት ካለፈው በኋላ ነው፡፡ እየሩሳሌም ውስጥ በእስራኤል ፖሊሶች የተገደለው የ32 ዓመቱ ወጣት ኢያድ ሀላክ ከልጅነቱ ጀምሮ የኦቲዝም ታማሚ ነበር ተብሏል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ኔታኒያሁ በሰጡት መግለጫ […]

ብራዚል በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሟች ዜጎቿ ቁጥር በዓለም ሁለተኛ ደረጃ እንድትቀመጥ አድርጓታል

አዲስ አበባ፣ሰኔ 7፣2012 ብራዚል በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የሟች ዜጎቿ ቁጥር በዓለም ሁለተኛ ደረጃ እንድትቀመጥ አድርጓታል:: ደቡብ አሜሪካዊቷ ሃገር ብራዚል ዓርብ ዕለት በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎች ቁጥርን ከፍ በከፍተኛ መጠን የመዘገበች መሆኑን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃን ከአውሮፓዊቷ እንግሊዝ ተረክባለች፡፡ ይሄንን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት የሀገሪቱ የጤና ስርዓት ትልቅ ጫና ውስጥ ይገኛል ብሏል፡፡የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ዓርብ ዕለት የ24 […]

የቱርክ ተዋጊ ጄቶች በሰሜናዊ ኢራቅ በሚገኘው የፒኬኬ የጦር ሰፈር ድብደባ ፈጸሙ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2012  የቱርክ ተዋጊ ጄቶች በሰሜናዊ ኢራቅ በሚገኘው የፒኬኬ የጦር ሰፈር ድብደባ ፈጸሙ፡፡የጦር ጄቶቹ ከቱርክ የተለያዩ የአየር ሃይል ማረፊያዎች በመነሳት የፒኬኬ ዋነኛ የጦር ካምፕን ጨምሮ በሰሜናዊ ኢራቅ የሚገኙ በርካታ ስፍራዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል፡፡እንደ ሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ከሆነ የጦር ድብደባው በቱርክ የጦር ካምፕ ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው የተወሰደ የአፀፋ እርምጃ ነው፡፡የቱርክ መከላከያ […]

ብራዚል ኮሮናቫይረስ ከቁጥጥሬ ውጭ አይደለም ብትልም በቀን ውስጥ የሚመዘገበው የሟችና የታማሚ ቁጥር እያሻቀበ ነው::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  ብራዚል ኮሮናቫይረስ ከቁጥጥሬ ውጭ አይደለም ብትልም በቀን ውስጥ የሚመዘገበው የሟችና የታማሚ ቁጥር እያሻቀበ ነው:: የፕሬዚዳት ዣየር ቦልሶናሮ የፅህፈት ቤት ሀላፊ ዋልተር ብራጋ ኔቶ በሰጡት መግለጫ በሀገራችን ኮቪድ 19 ቀውስ ፈጥሮብናል ግን ደግሞ ከቁጥጥራችን አልወጣም ማለታቸው ብዙዎቹን አስገርሟል ነው የተባለው፡፡ ምክንያቱም ሀላፊው ይህን አይነት መግለጫ የሰጡት በብራዚል በ24 በሰዓታት […]

በጋዛ የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ፍልስጤማዊያን ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 በጋዛ የሚገኙ አንድ ሚሊዮን ፍልስጤማዊያን ለከፋ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ተባለ፡፡ እስራኤል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለፍልስጤም ስደተኞች የሚልከውን ድጋፍ እንዳይደርስ በማገዷ በጋዛ የሚኖሩ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ፍልስጤማዊያን ለምግብ እጥረት መጋለጣቸው ነው የተነገረው፡፡ አሜሪካ ለፍልስጤም ስደተኞች የሚሆን በዓመት 360 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን እርዳታ ማቆሟ ደግሞ ጉዳቱን ያባባሰው ሌላኛው ጉዳይ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የምግብ […]

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመጭው ህዝበ ውሳኔ ድል ከቀናቸው ስልጣናቸውን እስከ 2036 የማራዘም እድል ይኖራቸዋል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመጭው ህዝበ ውሳኔ ድል ከቀናቸው ስልጣናቸውን እስከ 2036 የማራዘም እድል ይኖራቸዋል ተባለ::ሩሲያ በፈረንጆቹ ጁላይ 1 ላይ ህገ መንግስት ለማሻሻል የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ልታካሂድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡ በህዝበ ውሳኔው መሰረት ህገ መንግስቱ ይሻሻል የሚለው ድምፅ የሚያሸንፍ ከሆነ ፑቲን ተጨማሪ ሁለት የምርጫ ውድድሮችን ለማድረግ የሚያስችላቸው እድል ይፈጠርላቸዋል ተብሏል፡፡ በዚህም […]

ቻይና በ24 ሰዓታት ውስጥ ባደረገችው ምርመራ 14 ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙባት ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣2012 ቻይና በ24 ሰዓታት ውስጥ ባደረገችው ምርመራ 14 ሰዎች በኮሮናቫይረስ እንደተያዙባት ይፋ አደረገች:: ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል አስራ ሶስቱ ዋና ከተማዋ ቤጅንግ ውስጥ ሲሆኑ አንድ ሰው ደግሞ የቤጂንግ አጎራባች ከሆነችው የሄቢ ግዛት መሆኑ ታውቋል፡፡ የቻይና የጤና ኮሚሽን በሰጠው በግለጫ ሁሉም በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ከማህበረሱቡ ውስጥ ተጠርጥረው የተመረመሩ እና የጉዞ ታሪክ […]

ኢራቅ 13 ዶክተሮቿ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ማጣቷን ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 ኢራቅ 13 ዶክተሮቿ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ማጣቷን ይፋ አደረገች:: የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ካለፈው ፌብሯሪ ወር ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ 13 ዶክተሮቿ በኮቪድ 19 ሞተውባቸዋል፡፡ የኢራቅ የሀኪሞች ማህበር ሀላፊ አብዱል አላሚር አል ሺማሪ በመላ ሀገሪቱ ከ700 በላይ ዶክተሮች በበሽታው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ ሀኪሞቻችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለመርዳት የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው […]

ሰሞኑን ፈረንሳይ ውስጥ በተቀሰቀሰ የእሳት አደጋ ሁለት ህፀናትን ያዳኑ ሰዎች ከከንቲባቸው ጀግኖች የሚል ውዳሴ ተችሯቸዋል::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ16፣ 2012ሰሞኑን ፈረንሳይ ውስጥ በተቀሰቀሰ የእሳት አደጋ ሁለት ህፀናትን ያዳኑ ሰዎች ከከንቲባቸው ጀግኖች የሚል ውዳሴ ተችሯቸዋል::የሶስት እና የአስር ዓመት ያላቸው እመነዚህ ህፃና የሚኖሩበት አፓርታማ በእሳት ሲጋይ ከሶስተኛ ፎቅ መውጫ አጥተው ህዝቡ ከታች ከቦ ይመለከት ነበር፡፡ሰዎቹም ህፀናቱ በመስኮት እንዲዘሉ እና ጉዳት ሳይደርስደባቸው እንደሚቀበሏቸው በማበረታታት የህፀናቱን ህይዎት መታግ ችለዋል ነው የተባለው፡፡ህፀናቱም እሳቱ እየበረታ ሲመጣ ከንጻው ስር […]

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በርካታ የፌደራል ሀይሎችን አሰማራለሁ አሉ ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በርካታ የፌደራል ሀይሎችን አሰማራለሁ አሉ ::ፕሬዚዳንቱ ከፎክስ ኒውስ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እስከ 75 ሺህ ወታደሮችን በሁሉም የአሜሪካ ከተሞች ለማሰማራት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ይሁን እንጂ ይህን የምናደርገው ከየግዛቶቹ የድጋፍ ጥያቄ ከቀረበልን ነው ያሉት ትራምፕ አግዙን የሚሉን ከሆነ ያለማቅማማት እናደርገዋለን ብለዋል፡፡ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ […]