loading
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ የተከሰተውን ቃጠሎ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር አይገናኝም አሉ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2013 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ የተከሰተውን ቃጠሎ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር አይገናኝም አሉ:: በካፎርኒያ፣ኦሬጎን እና ዋሽንግተን የተከሰተው ሰደድ እሳት ያደረሰውን ውድመት የጎበኙት ትራምፕ የደን አጠባበቅ ችግር እንጂ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ብለዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ተርራምፕ በጉብኛታቸው ወቅት ከአካባቢው ባለ ስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይት ጉዳዩን ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር […]

ኢራን የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶችና ባህሬን ከእስራኤል ጋር ያደረጉትን የዲፕሎማሲ ስምምነት አወገዘች::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 ኢራን የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶችና ባህሬን ከእስራኤል ጋር ያደረጉትን የዲፕሎማሲ ስምምነት አወገዘች:: ፕሬዚዳንት ሀሰን ሩሃኒ እነዚህ ከጠላታችን እስራኤል ጋር ስምምነት የደረጉ ሁለት የአረብ ሀገራት ወደፊት እስራኤል በገልፉ አካባቢ ለምታደርስው ማነኛውም ጉዳት ተጠያቂ ይሆናሉ ብለዋል፡፡ እስራኤል በፍልስጤማዊያን ወገኖቻችን ላይ በየቀኑ ወንጀል እየፈፀመች ሳለ ከሷ ጋር መተባበርና በቀጠናው የጦር ሰፈር እንድትነባ ለመፍቀድ መዘጋጀት […]

በአውሮፓ የኮሮናቫይረስ ስርጭት መጨመሩ እንዳሳሰበው የዓለም ጤና ድርጅት ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013  በአውሮፓ የኮሮናቫይረስ ስርጭት መጨመሩ እንዳሳሰበው የዓለም ጤና ድርጅት ገለፀ:: ድርጅቱ በሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው በአውሮፓ በሳምንት ውስጥ የበሽታው ስርጭት በማርች ወር ከተመዘገበው ከፍተኛ ቁጥር የበለጠ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት የአውሮፓ አህጉር ሪጂናልን ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ሃንስ ክሉግ አሁን ላይ በአህጉሩ እየታየ ያለው የቫይረሱ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ብለዋል፡፡ በአወሮፓ […]

በእንግሊዝ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሀገሪቱ የጤና ሃላፊ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 በእንግሊዝ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሀገሪቱ የጤና ሃላፊ አስታወቁ፡፡የእንግሊዝ ጤና ሃላፊ ማት ሃንኮክ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ ጫፍ ላይ መድረሱን የተናገሩ ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ተጨማሪ ክልከላዎች ሊተገበሩ ይገባል ብለዋል፡፡አሁን ላይ ያለን ምርጫ ክልከላዎችን በማያከብሩ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመር አለብን ብለዋል ዋና ፀሐፊው፡፡ በመንግስት በኩል የተቀመጡ የጥንቃቄ እርምጃዎችንና ክልከላዎችን […]

የኢራን ፕሬዚዳንት አሜሪካ በምታደርገው ምርጫ ሀገራቸው መደራደሪያ ሆና አትቀርብም አሉ ፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 የኢራን ፕሬዚዳንት አሜሪካ በምታደርገው ምርጫ ሀገራቸው መደራደሪያ ሆና አትቀርብም አሉ ፡፡የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮሃኒ በቨርቹዋል በተካሄደው 75ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ኢራን በአሜሪካ ምርጫም ሆነ በውስጥ ጉዳይ ላይ በጭራሽ መደራደሪያ ሆና አትቀርብም ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው የሀገራችን ክብርና ብልጽግና ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊያችን ነው ያሉ ሲሆን […]

ደቡብ ኮሪያ የተሰወሩብኝ ባለሰልጣን በጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለውብኛል ስልት ከሰሰች::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 ደቡብ ኮሪያ የተሰወሩብኝ ባለሰልጣን በጎረቤት ሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለውብኛል ስልት ከሰሰች:: በዓሳ ሀብት ልማት ተቋም ውስጥ ይሰሩ የነበሩት ግለሰብ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ደብዛቸው ጠፍቶ እንደነበር የገለፀችው ሴኡል በመጨረሻ በሰሜን ኮሪያ የባህር ጠረፍ አስከሬናቸው መገኘቱን አረጋግጣለች፡፡ የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ሰውየውን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተኩሰው ገድለው ሲያበቁ በጭካኔ አስከሬናቸው […]

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በሶስት የምስራቅ እስያ ሀገራት ጉብኝት ሊያደርጉ ነው::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2013 የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በሶስት የምስራቅ እስያ ሀገራት ጉብኝት ሊያደርጉ ነው:: ፖምፒዮ ከመጭው ኦክቶበር 4 ጀምሮ ለጉብኝት የመረጧቸው ሀገራት ጃፓን ደቡብ ኮሪያ እና ሞንጎሊያ ናቸው፡፡ በነዚህ ሀገራት ጉብኝታቸውም በዋናነት የሰሜን ኮሪያና የቻይናን ጉዳይ አንስተው ከሀገራቱ ጋር ይመክራሉ ነው የተባለው፡፡ ፖምፒዮ ኦክቶበር 6 ላይ አሜሪካ፣ ጃፓን፣ አውስትራሊያ እና ህንድ […]

የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ወደ ጨረቃ ጉዞ በማድረግ የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር ልትሆን ተዘጋጅታለች ተባለ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013  የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ወደ ጨረቃ ጉዞ በማድረግ የመጀመሪያዋ የአረብ ሀገር ልትሆን ተዘጋጅታለች ተባለ::ጠቅላይ ሚስትርና የአቡዳቢ አስተዳዳሪ የሆኑት ሼክ ሞሃመድ ቢን ራሽድ አል መክቱም በቱይተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ሀገራቸው የጠፈር መንኮራኩር ወደ ጨረቃ ለመላክ መዘጋጀቷን ይፋ አድርገዋል፡፡ አቡዳቢ በቅርቡ ወደ ማርስ ሳተላይት ያመጠቀች ሲሆን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2024 መንኮራኩር ጨረቃ […]

ፈረንሳይ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱ ግለሰብ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው እንዲሰጡ ወሰነች::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 ፈረንሳይ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱ ግለሰብ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው እንዲሰጡ ወሰነች:: የፈረንሳይ ከፍተኛ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፌሊሲን ካቡጋ የተባሉ በዘር ጭፍጨፋው ወቅት ጥቃት አድራሾቹን በመሳሪያ እና በሌሎች ቁሳቁሶች ይደግፉ እንደነበር በማረጋገጡ ነው ተላልፈው እንዲሰጡ የወሰነው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አቃቤ ህግ ሰውየውን የከሰሳቸው ዘር […]

በፓሪስ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በድጋሚ ማገርሸቱ ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 በፓሪስ የኮሮናቫይረስ ስርጭት በድጋሚ ማገርሸቱ ተሰማ::በፈረንሳይ ዋና ከተማና ፓሪስና ማርሴል የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በድጋሚ በማገርሸቱ ምክንያት በርካታ ተቋማት ለአገልግሎት ዝግ ሆነው እንዲቆዩ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡ በሀገሪቱ ባገረሸው የኮቪድ 19 ስርጭት ምክንያት በዋና ከተማዋ ፓሪስ የሚገኙ የምሽት መዝናኛዎችና ሬስቶራንቶች ከማክሰኞ ጀምሮ ዝግ ሆነው እንዲቆዩ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ማዘዛቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ትላንት በወጣው የሀገሪቱ ሪፖርት […]