loading
ሞሮኮ በማረሚያ ቤቶቿ ባደረገችው ምርመራ ከ300 በላይ ታራሚዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን አረጋገጠች::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 ሞሮኮ በማረሚያ ቤቶቿ ባደረገችው ምርመራ ከ300 በላይ ታራሚዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን አረጋገጠች:: ይሄ ቁጥር የተገኘው በሶስት እስር ቤቶች በሚገኙ 1 ሺህ 736 እስረኞች ላይ በተደረገ ምርመራ መሆኑን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ከነዚህ ሶስት እስር ቤቶች መካከል ደግሞ 303 በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች የተገኙት በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በሚገኝ ኦዋራዛቴ […]

ሚኒስቴሩ በሃብት ማሰባሰብ ስትራቴጂ ካሰባሰበዉ ሀብት ዉስጥ 15 ሚሊዮን ብሩን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ ተቋማት አስረከበ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 ሚኒስቴሩ በሃብት ማሰባሰብ ስትራቴጂ ካሰባሰበዉ ሀብት ዉስጥ 15 ሚሊዮን ብሩን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ ተቋማት አስረከበ፡፡የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ፤ ሚኒስቴሩ ባካሄደዉ የርክክብ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ህይወት ኃይሉ ባስተላለፉት መልዕክት ቫይረሱ በፍጥነት የሚዛመት በመሆኑ የቆየንበት  የመጠጋጋት፣ የመጨባበጥና የመሳሳም ልማድን መተዉ አለብን ብለዋል፡፡ ሚኒስትር ዲኤታዋ […]

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 66 ደረሰ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 66 ደረሰ:: በ24 ሰዓታት ውስጥ በ912 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ ሁለት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 7 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል፡፡የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133 ደርሷል፡፡ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ በበሽታው ተይዘው እንክብካቤ ሲደረግላቸው ከነበሩት መካከል 66 […]

ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆነ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆነ:: በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆኗል።በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የለይቶ ሕክምና ማእከል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት ከምትገኝ የ34 ዓመት እናት ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም የተወለደው ሕፃን 3.1 ኪ.ግ. ክብደት ያለው ወንድ ልጅ መሆኑም ታውቋል።ከሕፃኑ በተወሰደው ናሙና ላይ በተካሔደው […]

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ህፃን በማገት 600 ሺህ ብር የጠየቀቺው ተጠርጣሪ ተያዘች:: የአማራ ፖሊስ ከሚሽን እንዳስታወቀዉ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ የሁለት ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን ይዛ በመሰወር የማስለቀቂያ 600 ሺህ ብር የጠየቀችው ተጠርጣሪ መያዟን የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ግለሰቧ በሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት ከግብረአበሯ ጋር በመሆን ህፃኑን ይዛ በመሰወር ለህፃኑ […]