loading
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሁለት ፓርቲዎችን ፈቃድ ሰረዘ፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 20፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሁለት ፓርቲዎችን ፈቃድ ሰረዘ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሰረት ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እንዲያሟሉ ከተጠየቁት መካከል አራት ፓርቲዎች መስፈርቱን ያሟሉ ሲሆን ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ ባለሟሟላታቸው መሰረዛቸውን ገልጿል፡፡ የተጠየቀውን መስፈርት ያሟሉ ፓርቲዎች ፤የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/- የአፋር ሕዝብ ፓርቲ /አሕፓ/፤ የጋሞ […]

በዳያስፖራው የተፈጠረው መነሳሳትና የአንድነት ስሜት ቀጣይነት እንዲኖረው ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 20፣ 2013 በዳያስፖራው የተፈጠረው መነሳሳትና የአንድነት ስሜት ቀጣይነት እንዲኖረው ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ:: የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ እንዳስታወቀዉ የዳያስፖራዉ ማህበረሰብ በሀገር ልማትና ዕድገት ለማሳተፍ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሆነ ገልጿል፡፡ የዳያስፖራ የምክክር መድረክ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደበት ወቅት የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠላማዊት ዳዊት እንዳሉት ዳያስፖራው አባላት በንግድና ኢንስትመንት፣ በዕውቀት ሽግግር፣ በሬሚታንስና በሌሎች ወሳኝ የሀገር ልማት […]

በ2ኛው የዓለም ጦርነት የተሳተፉ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች ከ75 ዓመት በኋላ ውቅና አገኙ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 20፣ 2013 በ2ኛው የዓለም ጦርነት የተሳተፉ የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች ከ75 ዓመት በኋላ ውቅና አገኙ:: ወደ 80,000 የሚሆኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪቃውያን እንደ የወታደራዊ ጓድ አካል ሆነው በጦርነቱ ቢሳተፉም ከነጭ ወታደሮች ያነሱ ተደርገው የእነሱ አስተዋፅዖ ሳይነገር ተዳፍኖ ቀርቶ ነበር፡፡ አሁን ግን በኮመንዌልዝ በኩል በተቋቋመው ኮሚሽን በወቅቱ ለተዋጉትና ለሞቱት እንዲሁም አሁንም በህይዎት ለሚገኙ ወታደሮች የመታሰቢያ ሂደት […]

በማዕከላዊ አፍሪካ ምርጫ በተከሰተ ብጥብጥ 800 የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 20፣ 2013 በማዕከላዊ አፍሪካ ምርጫ በተከሰተ ብጥብጥ 800 የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን የሀገሪቱ የምጫ ኮሚሽን አስታወቀ:: የታጠቁ ሃይሎች ምርጫው በኪካሄድበት ወቅት ባደረሱት ጥቃት 14 በመቶ የሚሆኑት የምርጫ ጣቢያዎችን ለመዝጋት መገደዱን ነው ኮሚሽኑ የገለፀው፡፡ ታጣቂዎቹ በመራጮችና በምርጫ ሰራተኞች ላይ ጥቃት በመሰንዘር፣ እንዲሁም የምርጫ ኮሚሽኑ ስራውን እንዳያከናውን በማገድ ነው ሂደቱን ያደናቀፉት ተብሏል፡፡ የታጠቁ ሃይሎች በመራጮች ከማዋከብ […]

የተማሪዎችን የፈጠራ ውጤቶች በአግባቡ መምራት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 የተማሪዎችን የፈጠራ ውጤቶች በአግባቡ መምራት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ:: የትምህርት ሚኒስቴር በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና፣ በጥበብና ሂሳብ ዘርፍ የሚቀርቡ የተማሪዎችን የፈጠራ ስራዎች ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ መመሪያው ተወዳዳሪዎች በተቀመጠላቸው መስፈርት መሰረት የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡና አሸናፊዎች በማያሻማ መልኩ ተለይተው ተገቢውን ማበረታቻ እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑ ነው […]

በጋምቤላ ክልል በሰለጠነ ባለሙያ የወለዱ እናቶች ሽፋን 40 በመቶ መሆኑ ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 በጋምቤላ ክልል በሰለጠነ ባለሙያ የወለዱ እናቶች ሽፋን 40 በመቶ መሆኑ ተገለፀ:: በክልሉ የእናቶችና ጨቅላ ህፃናትን ጤናና የስርዓተ ምግብ ሁኔታን ለማሻሻል ያለመ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ወቅት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት በክልሉ በሰለጠነ ባለሙያ የሚወልዱ እናቶች ሽፋን 40 በመቶ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ሚኒስትሯ የህጻናት ክትባት መሻሻል ቢታይበትም አሁንም ዝቅተኛ ሽፋን እንዳለው […]

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተ የፀጥታ መደፍረስ 123 ሰዎች ሲገደሉ 500 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በተከሰተ የፀጥታ መደፍረስ 123 ሰዎች ሲገደሉ 500 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ:: የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የምርመራውን ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ወቅት በወንጀሉ የተሳተፉ ሰዎች ያደረሱት ጥቃት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ባሕርያትን የሚያሟሉ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

እስራኤል በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 በጋዛ ሰርጥ 300 ጥቃቶችን መፈፀሟን ይፋአደረገች::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 እስራኤል በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 በጋዛ ሰርጥ 300 ጥቃቶችን መፈፀሟን ይፋአደረገች:: የሀገሪቱ መከላከለያ ተቋም ባወጣው መግለጫ በአካባቢው በተመረጡ 300 ኢላማዎችላይ ጥቃት ማድረሱንና 38 የጥቃት ሙከራዎችን ማክሸፉን ተናግሯል፡: ከጋዛ በኩል 176 ሮኬቶች ተተኩሰውብን ነበር ያለው የእስራኤል ጦር ሃይል ከነዚህ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ባዶ ሜዳ ላይ ነው ያረፉት ብሏል፡፡ በሪፖርቱ እንደተገለፀው የእስራኤል ተዋጊ […]

አፍሪካ ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እየታገለች ነው ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣ 2013 አፍሪካ ሁለተኛው ዙር የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እየታገለች ነው ::ከቀሪው ዓለም ጋር ሲነፃፀር የበሽታው ስርጭት በአፍሪካ አነስተኛ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አሁን ላይ በ47 የአፍሪካ ሀገራት በበሽታው የተያዙባቸው ዜጎች ሳምንታዊ አማካይ ቁጥር 73 ሺህ መድረሱ ታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪካ አህጉር የበሽታውን የስርጭት መጠን […]

ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የጤና ኤክስቴንሽን ወሳኝ ሚና እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 26፣ 2013 ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የጤና ኤክስቴንሽን ወሳኝ ሚና እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ:: የግልና አካባቢ ንጽህናን በአግባቡ በመጠበቅ የተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመቀነስ ለጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም የተሰጠው ትኩረት ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የግልና የአካባቢ ንጽህናን ጨምሮ 19ኙ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ ያደረጉ ከ900 የሚበልጡ ግንባር ቀደም ቤተሰቦች ትናንት በባሌ ጎባ ተመርቀዋል። በግንባር ቀደም ቤተሰቦች ምረቃ […]