loading
ማላዊ በቮሮናቫይረስ ሳቢያ ሁለት የካቢኔ ሚኒስትሮቿን ማጣቷ በሀገሪቱ ትልቅ ሀዘን ፈጥሯል፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 05፣ 2013 ማላዊ በቮሮናቫይረስ ሳቢያ ሁለት የካቢኔ ሚኒስትሮቿን ማጣቷ በሀገሪቱ ትልቅ ሀዘን ፈጥሯል፡፡ የማላዊ ፕሬዳንት ላዛረስ ቺኩየራ የሚንስትሮቹን ሞት አስመልክተው ባደረጉት ንግግር የማይሰላ ኪሳራ ደርሶብናል ካሉ በኋላ በሀገሪቱ የሶስት ቀን ሀዘን መታወጁን ይፋ አድርገዋል በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ህይዎታቸው ያለፈው የትራንስፖርት ሚስትሩ ሲዲክ ሚያ እና የአካባቢ አስተዳደር ሚንስትሩ ሊንግሰን ብሬካኒያማ ናቸው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው […]

ዩዌሬ ሙሴቬኒ የምርጫው ቀን ከመድረሱ በፊት የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እንዲዘጉ አዘዙ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 05፣ 2013 ዩዌሬ ሙሴቬኒ የምርጫው ቀን ከመድረሱ በፊት የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እንዲዘጉ አዘዙ፡፡ ዩጋንዳ ጃኑዋሪ 14 ለምታካሂደው ምርጫ የተሳሳተ መረጃን በማሰራጨት ሁከት እንዲቀሰቀስ ያደርጋል በሚል ስጋት ከምርጫው ቀን አስቀድሞ ላሉት ሁለት ቀናት የበይነ መረብ አገልግሎት ዝግ ተደርጓል፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የሀገሪቱ የኮምኒኬሽን ቁጥጥር ባለስልጣናትም የሙሴቬኒን ትእዛዝ ተቀብለው የበይነ መረብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን […]

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ከ600 በላይ የልዩ ሀይል ፖሊሶችን እያስመረቀ ነው::

አዲስ አበባ፣ጥር 06፣ 2013 የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ከ600 በላይ የልዩ ሀይል ፖሊሶችን እያስመረቀ ነው:: የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ በዛሬው እለት ከ600 በላይ የልዩ ሀይል ፖሊሶችን እያስመረቀ ነው፡፡ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅን ጎብኝተዋል፡፡ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እና በእርሳቸው የተመራው ልዑክ የኮሌጁን ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡

የአርባምንጭ ከተማ የጤና መሰረተ ልማት ላይ ያለዉን የአገልግሎት ጥራት ችግር ለማቅለል በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013  የአርባምንጭ ከተማ የጤና መሰረተ ልማት ላይ ያለዉን የአገልግሎት ጥራት ችግር ለማቅለል በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ ፡፡በከተማዋ 3 የጤና ጣቢያዎችና 1 አጠቃላይ ሆስፒታል ያለ ሲሆን ከፍተኛ ህክምና የሚሹ የከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ሆስፒታሎችን ማስፋት ላይ በትኩረት እተሰራ እንደሆነ አርትስ ያነጋገራቸዉ የከተማ ጤና ፅ/ቤት ሀላፌ ገልፀዋል፡፡

ትራምፕ ነጩን ቤት ከመልቀቃቸው በፊት በቀረቻቸው ሽርፍራፊ ሰዓት አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው::

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 ትራምፕ ነጩን ቤት ከመልቀቃቸው በፊት በቀረቻቸው ሽርፍራፊ ሰዓት አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው:: የትራምፕ የቅርብ ሰዎች በተለይ ለስቲቭ ባኖን ይቀርታ እንዳያደርጉ ቢመክሯቸውም በምጫው ያነሱትን ቅሬታ በመደገፋቸው ነው ይቅርታው የተደረገላቸው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡

ቱኒዚያዊያን በመንግስት ላይ የጀመሩት ተቃውሞ ከአራት ቀናት በላይ አስቆጥሯል::

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 ቱኒዚያዊያን በመንግስት ላይ የጀመሩት ተቃውሞ ከአራት ቀናት በላይ አስቆጥሯል:: ተቃዋሚዎቹ ጎዳናዎችን በመዝጋትና ቁሳቁሶችን በእሳት በማቀጣጠል ቁጣቸው በአደባባይ ሲያሰሙ ታይተዋል፡፡ የተቃውሟቸው መነሻ በሀገሪቱ የተንሰራፋው ድህነትና የስራ አጥነት መባባስ መሆኑን ለተቃውሞ በወጡበት ወቅት ገልፀዋል፡፡ አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው ሰልፈኞቹ የተለያዩ ሱቆችንና የንግድ ተቋማትን በመዝረፍ ተግባር ላይ መሰማራታቸውም ተሰምቷል፡፡ ይህን ተከትሎም የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰይድ […]

ኢራን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ወታራዊ ልምምዶችን ማድረጓ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 ኢራን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ወታራዊ ልምምዶችን ማድረጓ ተሰማ፡፡ የአሜሪካ ቢ 52 ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች በመካከለኛው ምስራቅ መብረራቸውን ተከትሎ ቴህራን በሀገሪቱ ደቡባዊ ጠረፍ አካባቢ ከባድ ልምምዶችን አድርጋለች ነው የተባለው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ባለፈው ጃኑዋሪ 3 በጄኔራል ቃሲም ሰይማኒ ላይ ግድያ ከተፈፀመ ወዲህ የአሜሪካ ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች በአካባው ሲበሩ የመጀመሪያቸው ነው፡፡ ኢራን በሁለት […]

ግብፅ በመላ ሀገሪቱ ጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአስራአምስተኛ ጊዜ አራዘመች::

አዲስ አበባ፣ጥር 16፣ 2013  ግብፅ በመላ ሀገሪቱ ጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአስራአምስተኛ ጊዜ አራዘመች:: በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ተግባዋ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አቃጅ ዳግም የታደሰው በፓርላመው ውሳኔና በፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ይሁንታ ነው፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ግብፅ የመጀመሪያውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጣለቸው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2017 ነበር፡፡ በወቅቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገው የሽበርተኝነትን አደጋ ለመከላከል በሚል […]

የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች ስምምነት

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣ 2013  የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች ቁልፍ የመንግስት ተቋማትን የሚመሩ እጩዎችን ለመምረጥ ተስማሙ ::የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ሞሮኮ ላይ ባደረጉት አዲስ ውይይት የእጩዎቹ የምልመላ ሂደት ከማክሰኞ ጀምሮ እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡ ተፋላሚ ሃይሎቹ የደረሱበት ስምምነት በሀገሪቱ ለአስር ዓመታት የተካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት እንዲያበቃ ለማድረግ ሁነኛ መፍትሄ መሆኑ ነው የተመገረለት፡፡ ሂደቱ እስከመጭው ፌብሩዋሪ 2 ቀን ድረስ የሚጠናቀቅ ሲሆን […]

በሩሲያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ::

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣ 2013 በሩሲያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ:: የሩሲያ የፀጥታ ሃይሎች ከ3 ሺህ በላይ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ማሰራቸው ተሰማ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት በቅርቡ ከህመም ያገገሙት የተቃዋሚ መሪው አሌክስ ናቫልኒ ከእስር ይፈቱልን የሚል ጥያቄ ይዘው ነው፡፡