loading
በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013 በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም:: በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮቪድ -19 ምክንያት የሞት መጠን አልተመዘገበም ተባለ፡፡ የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓትን ሪፖርት ባወጣዉ መረጃ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከረጅም ግዜ በኋላ በኮቪድ- 19 ምክንያት ሞት ያልተመዘገበበት ቀን ሆኗዋል፡፡ በ24 ሰዓቱ በተደረገ 4 ሺህ 974 የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች […]

እስካሁን የምርጫ ውጤት ተጠቃልሎ አልደረሰኝም-ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013  በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን የሁሉንም ምርጫ ክልሎች ውጤት ይፋ ማድረግ አለመቻሉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ። እስካሁን ባለው ሂደት ምርጫ ከተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች የ26ቱ ውጤት አለመድረሱን ቦርዱ አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ፤ በድምር መዘግየት፣ በትራንስፖርት ችግር እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ምክንያት የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ማዕከል ተጠቃሎ አልደረሰም ብለዋል። […]

ህንድ በ39 ቀናት 100 ሺህ ዜጎቿን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ አጣች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013  በህንድ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ400 ሺህ በላይ ሲያሻቅብ ከዚህም ግማሽ ያህሉ ሞት በሁለተኛው ዙር ወረርሽኝ የተከሰተ ነው ተባለ፡፡ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተመታችው ህንድ እስካሁን ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ መጠቃታቸውን ይፋ አድርጋለች፡፡ በህንድ 400 ሺህ 312 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ህይዎታቸውን ሲያጡ ከነዚህ መካከል 100 ሺህ የሚሆኑት የሞቱት በ39 ቀናት […]

የቻይና መንግስት ህገ ወጥ አዘዋዋሪ ነው- አንቶኒ ብሊንከን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013 አሜሪካ ቻይናና ሩሲያን ጨምሮ ከ10 በላይ ሀገሮችን በህገ ወጥ ሰዎች ዝውውርና በግዳጅ የጉልበት ብዝበዛ ከሰሰች፡፡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰጡት መግለጫ ከሩሲያና ቻይና በተጨማሪ ማይናማር እና ቱርክ በዚሁ ተግባር ይሳተፋሉ የሚል ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ ብሊንከን በተለይ ሺንጂያንግ ግዛት አካሂዶታል ያሉትን የጅምላ እስር እና ተያያዥ ተግባራትን በመጥቀሽ የቻይና መንግስት […]

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ነው::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ነው እያካሄደ የሚገኘው፡፡ ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው የፌዴራል መንግስትን የ2014 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡ በምክር ቤቱ ስብሰባ መክፈቻ ላይ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላበረከተው አስተዋፅኦ የምክር ቤቱ አባላት አድናቆታቸውን በጭብጨባ ገልፀዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መሰብሰቢያ […]

የሰኔ ወር ዋጋ ግሽበት 24 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሪ አሳየ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ ሁኔታ የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ካለው ጋር ሲነጻጸር በ24 ነጥብ 5 ከመቶ ጭማሬ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡ የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ28 ነጥብ 7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በዳቦና እህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው […]

ካይሮ የግድቡ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት መጀመሩን የሚገልፅ ደብዳቤ ከአዲስ አበባ ደርሶኛል አለች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29፣ 2013 ካይሮ የግድቡ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት መጀመሩን የሚገልፅ ደብዳቤ ከአዲስ አበባ ደርሶኛል አለች፡፡ የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ሞሀመድ አብደል አቲ የኢትዮጵያው የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ኢንጂኔር ስለሺ በቀለ በላኩልኝ ይፋዊ ደብዳቤ ሀገራቸው በተናጠል ውሳኔዋ ፀንታ ሁለተኛውን ዙር ሙሌት መጀመሯን አረጋግጠውልኛል ብለዋል፡፡ አብደል አቲ ለኢንጂኔር ስለሺ በጻፉት የመልስ ደብዳቤ ግብፅ የኢትዮጵያን […]

የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና የቀብር ስነ-ስርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29፣ 2013 በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል፡፡ አፍሪካዊቷ ማዘር ቴሬዛ በመባል የሚታወቁት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ከሀገር ባለውለታነት አልፈው ለሰው ልጆች ትልቅ […]

የፀጥታው ምክር ቤት በህዳሴው ግድብ ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነት የለውም-የናይል ተፋሰስ ሀገራት

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013  የፀጥታው ምክር ቤት በህዳሴው ግድብ ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነት የለውም-የናይል ተፋሰስ ሀገራት የናይል ተፋሰስ ሀገራት በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት የሚደረገው የግድቡ ድርድር ሂደት ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ትክከለኛው መንገድ መሆኑን ገለጹ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ድርድሩ ያለበትን ደረጃ በሚመለከት በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተፋሰሱ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ገለፃ አድርገዋል፡፡ […]

ልጆቿን የምታስርብ ሃገር ልትለማ አትችልም-ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 በህፃናት ምገባ ላይ ትኩረቱን ያደረገው ስኩል ሚል ኢኒሸቲቭ የተማሪዎችን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ የድርሻችንን እንወጣ ሲል ጥሪ አቀረበ፡፡ ድርጅቱ ይህን ያለው በተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የተሰሩትን ሥራዎች ማሳያና የምስጋና መርሐ ግብር ባካሄደበት ወቅት ነው። የስኩል ሚል ኢኒሸቲቭ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው ሃገር የምትለማው ዜጎቿን ስትንከባከብ ነው ብለዋል። ልጆች ባሉበት ሁሉ […]