loading
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የተጓዙት ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የተጓዙት ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው፡፡ 465 ቱን የዛሬዎቹን ተጓዦች ለመቀበል የአስመራ ጎዳና በነዋሪዎቿ ደምቃለች፡፡

ዲያስፖራ ኖት?

ዲያስፖራ ኖት? እንግዲያዉስ የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ይፋ ሆኗልና እንንገርዎ። ይህም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በሚል ስም ሲሆን ሂሳቡ የተከፈተዉ፤የሂሳብ ቁጥሩም 1000255726725 ነዉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በውጭ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በየቀኑ ቢያንስ አንድ ዶላር ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ለተለያዩ የልማት ስራዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀው ነበር። ለዚህም […]

የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የዕርቀ ሰላም ልዑኳን ወደ አሜሪካ ሸኘች፡፡

የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የዕርቀ ሰላም ልዑኳን ወደ አሜሪካ ሸኘች፡፡ በውጭ አገር ከሚኖሩ ብፁዓን አባቶች ጋር እየተደረገ ባለው የዕርቀ ሰላም ሂደት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ለዕርቀ ሰላም ልዑካን አባላት የሽኝት መርሐ-ግብር ተደርጎላቸዋል፡፡ አቡነ ማትያስ በሽኝት ስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ዕርቀ ሰላም ሂደት የበኩሏን ጥረት ስታደርግ መቆየቷን […]

የአሰብ ወደብ በአፋጣኝ ስራ እንዲጀምር የኤርትራና የኢትዮጲያ መንግስታት መመሪያ ሰጡ፡፡

የአሰብ ወደብ በአፋጣኝ ስራ እንዲጀምር የኤርትራና የኢትዮጲያ መንግስታት መመሪያ ሰጡ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ከትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ማሪታይም አገልግሎት ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትናሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ አካላት ያሉበት ግብረ ሀይል የአሰብን ወደብ ስራ ቶሎ ለማስጀመር ተቋቁሟል። የአሰብ ወደብን ለመጠቀም በአሁኑ ወቅት የመንገድ ጥገና […]