loading
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ግንቡን እናፍርስ ድልድዩንም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በአሜሪካ በሚያደርጉት ቆይታ ከ40 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተባለ፡፡ በዋሽንግተንዲሲ፣ በሎሳንጀለስና በሚኔሶታ በሚካሄዱ የድጋፍ ሰልፎችም የተለያዩ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገዉ የድጋፍ ሰልፍ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ የሚሳተፍበት ሲሆን ፤በሎሳንጀለስ ደግሞ የጥያቄና መለስ የዉይይት መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡ በሚኔሶታ በሚደረገዉ ሶስተኛዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቆይታ የተለያዩ ፖለቲካዊ […]

መንግስት ባወጣው የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ ለመሆን ከታራሚዎች ምን ይጠበቃል?

መንግስት ባወጣው የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ ለመሆን ከታራሚዎች ምን ይጠበቃል? መንግስት ያወጣው የምህረት አዋጅ ከወጣበት ሐምሌ13ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡ የምህረት አሰጣጡ ለሚቀጥሉት 6 ወራት ስራ ላይ የሚውል ሲሆን፤ የምህረቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ታራሚዎች የተጠየቁበት ወንጀል እስከ ግንቦት 30 የተፈጸመ ከሆነ ብቻ ነዉ ተብሏል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በእነዚህ […]

አዋሽ ባንክ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን የሚቀንስ ዲጂታል የገንዘብ ማስተላልፊያ አገልግሎት መስጠት ጀምሬያለሁ አለ፡፡

አዋሽ ባንክ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን የሚቀንስ ዲጂታል የገንዘብ ማስተላልፊያ አገልግሎት መስጠት ጀምሬያለሁ አለ፡፡ ባንኩ ና ወርልድሪሚት ገንዘብ በዲጂታል ማስተላለፍን በጋራ ለመስራት መፈራረማቸውን ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ወርልድ ሪሚት የገንዘብ ማስተላለፊያ ከ 50 በላይ ሀገራትና ከ145 በላይ መዳረሻዎች ላይ እየሰራ መሆኑን እና በ ኢትዮጲያ ውስጥ በወርልድ ሪሚት የተደረገ የገንዘብ ልውውጥ ከ160 በመቶ በላይ እንዳደገ በምስራቅ እና […]

አሜሪካ ለገበሬዎቿ ካሳ ልትከፍል ነው

ዋሽንግተን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በቀሰቀሰው የንግድ ጦርነት ኪሳራ ለደረሰባቸው ገበሬዎች 12 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል መወሰኗ ተሰምቷል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በግብርና የሚተዳደሩ አሜሪካውያን ምርታቸውን ወደ ውጭ ሀገር ልከው እንዳይሸጡ አዲሱ የንግድ እሰጣ ገባ እንቅፋት ሆኖባቸዋል፡፡ በተለይ የአሜሪካን የግብርና ምርቶች ወደ ሀገሯ ታስገባ የነበረቸው ቻይና፤ ትራ ምፕን ለመበቀል የጣለችው ታሪፍ በገበሬዎቹ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮባቸዋል፡፡ የታሪፍ […]

በግብጽ እስር ቤቶች በጤና ችግር ሳቢያ የሚሞቱ እስረኞች ቁጥር እየጨመረ ነዉ

ምክንያቱ ደግሞ ያልተገባ አያያዝ፣ የህክምናና የመድሀኒት እጥረት መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተናግረዋል፡፡ የእስረኞቹ ጠበቆችም የደንበኞቻቸውን የጤና ሁኔታ ተከታትለው እንዳይመዘግቡና መረጃ እንዳያገኙ እየተደረጉ ነው ይላል የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ፡፡ በግብጽ የአንድ ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ መሪ የነበሩት አብደል ሞኔም አቡል ፎቱህን የጤና ሁኔታ በማሳያነት ያነሳሉ የመብት ተሟጋቾቹ፡፡ ግለሰቡ በፌስ ቡክ ገጻቸው የእስር ቤቱ አስተዳዳሪዎች ሆስፒታል ሄጄ እንዳልታከም […]

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ነገ ወደ አሜሪካ ይሄዳሉ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩንም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚያደርጉት ጉዞ በአጠቃላይ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፥ በሀገራቸው እየተካሄደ ላለው ሁለንተናዊ ለውጥ አካል ሆነው ለሀገሪቱ ልማትና እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ያለመ ነው ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሎስ አንጀለስ እና በዋሽንግተን ዲ ሲ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ሐምሌ 24 ቀን ድረስ ነው በአሜሪካ ቆይታ የሚያደርጉት። የኢፌዴሪ […]

ቡናችን በዓለም ገበያ የሚፈለገዉን ያህል አልተዋወቀም ተባለ

ይህ የተባለዉ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንና ከቡና ላኪዎች ማህበር ጋር በጋራ ባዘጋጁት ቡናን በአለም ማስተዋወቅ ላይ ባተኮረ የዉይይት መድረክ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ የቡናና ሻይ ባለስልጣን የገበያ ልማት ቁጥጥርና የግብይት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር በሀገራችን ከ25 ሚሊየን በላይ ህዝብ ኑሮዉ በቡና ምርት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የምናመርተዉ ቡና ግን ጥራቱን የጠበቀ ባለመሆኑ አምራቹን መጥቀም አልተቻለም […]

ሺ ጂፒንግ ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ለብሪክስ ስብሰባ ነው ደቡብ አፍሪካ የተገኙት፡፡ ፕሬዝዳንቱ በመካከለኛው ምስራቅና በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ጉብኝታቸውን የጀመሩ ሲሆን ከነገ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ በሚካሄደው 10ኛው የብሪክስ ጉባዔ ይሳተፋሉ፡፡ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይናና ደቡብ አፍሪካ በጋራ ያቋቋሙት የትብብር ተቋም በዋናነት በሀገራቱ መካከል ያሉትን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ታስቦ ነው የተመሰረተው፡፡ ፕሬዝዳንት ሺ ጆሀንስበርግ በምታስተናግደው በዚህ ጉባዔ […]