loading
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዘዳንት ማይክ ፔንስ ጋር በሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዘዳንት ማይክ ፔንስ ጋር በሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል ::

በገበሬዎችና በእንስሳት አርቢዎች መካከል ነፍስ መጠፋፋት ለናይጀሪያ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል፡፡

በገበሬዎችና በእንስሳት አርቢዎች መካከል ነፍስ መጠፋፋት ለናይጀሪያ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል፡፡ ፕሬዝዳንት ማማዱ ቡሀሪ ሀገራቸውን ሰላም ከነሳት ነገር የመጀመሪያው የቦኮሀራም ጥቃት ነው ይባላል፡፡ ነገር ግን ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በተደረገ ጥናት ሌላ አስደንጋጭ ክስተት መፈጠሩን የሚያሳይ መረጃ ይፋ ሆኗል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በዚህ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በከብት አርቢዎችና በአርሶ አደሮች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ከ1ሽህ […]

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካን ምክትል ፕሬዝዳንት ያነጋግራሉ::

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ እንዳስታወቀው የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ጋር በሁለቱ አገሮች ግንኙነት እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው ዕለት ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር አብይ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከት ከሚያራምዱ ኢትዮጵያውያን የፓርቲ መሪዎች ጋር የሚነጋገሩ መሆኑ ታውቋል። በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአሜሪካ […]

በአሜሪካ የሚገኙ ስደተኛች ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር መቀላቀል ጀመሩ፡፡

የፕሬዝዳን ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ባወጣው ህግ ሰነድ አልባ ስደተኞች በማቆያ ስፍራ ሲቀመጡ ህጻናቱ ለብቻቸው እንዲኖሩ ተገደው ነበር፡፡ አሁን ግን የአሜሪካ ፍርድ ቤት በወሰነው መሰረት እድሜያቸው ከ5-17 ያሉ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር መቀላቀል ጀምረዋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው እስካሁን 1ሺህ 800 ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር የመቀላቀል ዕድል አግኝተዋል፡፡ 2ሺህ 500 ህጻናት ወላጆቻቸው ህገ ወጥ ናችሁ ተብለው በስደተኞች ማቆያ ስፍራ ሲቀመጡ […]

የኢንጀነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነ – ሥርዓትን እሁድ ሀምሌ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ይፈጸማል

የኢንጀነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነ – ሥርዓትን እሁድ ሀምሌ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ይፈጸማል ፡፡ ብሔራዊ የቀብር አስፈሚ ዐብይ ኮሚቴ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ የቀብር ሥነ-ስርአቱ ዕሁድ ሐምሌ 22 ቀን 2010. ከቀኑ 7፡00 ሰአት በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ በሚገኘው በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸው፣ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ የሥራ ባልደረቦች እና መላው ህዝብ በተገኙበት […]

ዛሬ በልደታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ የአራት ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡

ዛሬ በልደታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ የአራት ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን በመደገፍ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ የተደረገው ሰልፍ ላይ ከፈነዳው ቦምብ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ላይ ፍ/ቤቱ የተጠየቀውን ጊዜ ቀጠሮ ተቀብሏል፡፡

መሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ን የምትደብቁ ተጠንቀቁ ተብላችኋል፡፡

መሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ን የምትደብቁ ተጠንቀቁ ተብላችኋል፡፡ ይህንን ያላችሁ የኢፌድሪ የንግድ ሚኒስቴር ነዉ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በላከልን መግለጫ ስንዴ ፣ስኳርና ፓልም ዘይት በመንግስት ድጎማ ወደሀገር ዉስጥ እየገባ ቢሆንም ፤ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባደረገዉ አሰሳና በህዝብ ጥቆማ መሰረታዊ ሸቀጦቹ እየተደበቁ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡ ሚኒስቴሩም መሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ህገወጥ ድርጊቶችን የምትፈጽሙ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ ካልሆነ የሸማቹን […]