loading
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ13 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ በተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ተመርምሮ፣ በየኮሌጆቹ አካዳሚክ ጉባኤዎች ተፈትሾና በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ ይሁንታ ያገኘውን መረጃ ተመልክቶ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡ በዚህም መሠረት፡-ፕሮፌሰር ተሾመ ሶሮመሳ፣ፕሮፌሰር አሰፋ ወልደማርያም፣ፕሮፌሰር ወርቅነህ ቀልቤሳ፣ፕሮፌሰር በቀለ አበበ፣ፕሮፌሰር ዳንኤል አሥራት፣ፕሮፌሰር ንጉሴ መገርሳ፣ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ለማ፣ፕሮፌሰር ጥላሁን ተክለኃይማኖት፣ፕሮፌሰር አበበ በቀለ፣ፕሮፌሰር ኃይሉ ወርቁ፣ፕሮፌሰር ሽመልስ አድማሴ፣ፕሮፌሰር ላይከማርያም አስፋውና ፕሮፌሰር አባተ ባኔ የሙሉ […]

ሩስያ በሺዎች ሚቆጠሩ የሰሜን ኮሪያ ዜጎች በሀገሯ ገብተዉ እንዲቀጠሩ ፈቀደች፡፡

ሞስኮ ታይምስ ከመቀመጫዉ ከሞስኮ እንደዘገበዉ በሩሰያ ከ10 ሺ በላይ ሰሜን ኮርያዉያን የስራ ፍቃደ ማግኘታቸዉን አረጋግጠዋል፡፡ ሩስያ የወሰደችዉ እርምጃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፒዮንግያንግ ዜጎች ላይ ከሀገር ወጥተዉ እንዳይሰሩ የተጣለባቸዉን ማእቀብ የጣሰ ነዉ ተብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ጉዳዩን እያጣራሁ ነዉ ብሏል፡፡ ሩስያ ግን ስለጉዳዩ ለማንም ምላሽ አልሰጠችም፡፡ እስካሁን ሩስያ ዉስጥ የሚኖሩ ሰሜን ኮርያዉያን ወደሀገራቸዉ በየአመቱ እስከ 300 […]

በሰኔ 16 የቦምብ ፍንዳታ ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው::

ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ድጋፍ ለመስጠት ሰኔ 16 ቀን 2010 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማፈንዳት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል በአምስቱ ላይ ክስ ሊመሰረት ነው። መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ያሰረከበባቸው ተጠርጣሪዎች አብዲሳ ቀነኔ፣ ደሳለኝ ተስፋዬ፣ ጌቱ ግርማ፣ ህይወት ገዳ እና ባህሩ ቶላ ናቸው። የፌደራል ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች […]

ኢትዮጵያ ለሽምግልና ልትቀመጥ ነዉ፡፡

ኢትዮጵያ የምትሸመግለዉ ኤርትራንና ጅቡቲን ነዉ፡፡ የዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት መሀከል ያለዉ ችግር ተቀርፎ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲሰፍን ኢትዮጵያ ለጅቡቲዉ ፕሬዝዳንት መልክት ልካለች ብለዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራትም ለሽምግለና ለመቀመጥ መልካም ፍላጎትን አሳይተዋል ተብሏል፡፡

ለህፃናት ሞት መቀነስ ዋና መፍትሄ ጡት ማጥባት ነው ተባለ ፡፡

ይህ የተባለው አለም አቀፍ ጡት የማጥባት ሳምንትን በተመለከተ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ላይ ነው፡፡ አለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት በኢትዮጲያ ሲከበር ለ10ኛ ጊዜ ሲሆን “ጡት ማጥባት የሕይወት መሰረት ነው” በሚልመሪ ቃል እስከ ነሃሴ 1ቀን 2010 ዓ.ም ይከበራል ፡፡ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶች እና ህፃናት ዳይሪክቶሬት የስርአዓተ ምግብ አማካሪ ወ/ሮ በላይነሽ ይፍሩ ህፃናት ከወሊድ […]