loading
በወታደራዊ ስነ ምግባር ጥሰትና ኩብለላ ወንጀሎች ለተከሰሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ምህረት ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያጸደቀውን የምህረት አዋጅ መሰረት በማድረግ በወታደራዊ የስነ ምግባር ጥሰት ተከሰው በማረሚያ ቤት የሚገኙና ቀደም ሲል ከሃገር የኮበለሉ የሰራዊት አባላት ምህረት ተደርጎላቸዋል ብለዋል። የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ኪዱ አለሙ፥ ለኢዜአ እንደገለጹት መንግስት በሃገር አቀፍ ደረጃ የጀመራቸውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች ለማስቀጠል መከላከያ ሰራዊት ለውጡን በመደገፍ እየሰራ ነው። የምህረት አዋጁ […]

በብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የአየር ወለድ አሰልጣኝ የነበረችው መ/አለቃ አይዳ አሌሮ ተፈታች፡፡

ወደ መከላከያ ሠራዊት የተቀላቀለችው በ1997 ዓ.ም የሥልጠና ቦታው ብር ሸለቆ የምልምል ወታደሮች ማሠልጠኛ ነው፡፡ አይዳ በውትድርና ስልጠና ከፍተኛ ውጤት ያመጣች ተመራቂ ናት፡፡ በፓራሹት 27 ጊዜ በመዝለል የምትታወቀው አይዳ በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በ2009ዓ.ም ስትሰለጥን ከ1800 ሰልጣኞች አንደኛ መሆኗ ልዩ ያደርጋታል፡፡ በቅርቡ ከሽብር ቡድን ጋር ተገኛኝተሻል ተብላ ክስ ቀርቦባት ነበር፡፡ በተጨማሪም ውስጥ ለውስጥ ሠራዊቱን በማነሳሳት አገር በማስከዳት […]

የነልደቱ አያሌዉ ኢዴፓ ፈረሰ፡፡

የነልደቱ አያሌዉ ኢዴፓ ፈረሰ፡፡ ፓርቲዉ ከ1አመት ከ8 ወር በፊት በቀድሞ የኢዴፓ ፕሬዝደንት ዶክተር ጫኔ ከበደ በፓርቲዉ ላይ በከፈቱት ክስ ምክንያት ፤በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምስክርነት ፓርቲዉ በፍርድቤት እንዲፈርስ ተወስኖ እንደነበር አቶ ልደቱ አያሌዉ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡: ሆኖም እንደ አቶ ልደቱ ገለጻ ፍርድቤቱ ያሳለፈዉን ዉሳኔ ለማስቀልበስ አስከ ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ድረስ አቤቱታ ብናቀርብም ምላሽ […]

በሀዋሳ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቀያቸው ይመለሳሉ፡፡

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት በሀዋሳ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ከ 1 ወር በላይ የቆዩ ተፈናቃዮች ከዛሬ ጀምሮ ወደ የቀያቸዉ ይመለሳሉ ብለዋል፡፡ አቶ ሚሊዩን ተፈናቃዮቹ የሚመለሱባቸዉ መንደሮች የቀድሞ ሰላማቸዉን ማግኘታቸዉን ተናግረዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ እስኪቋቋሙ ድረስ ቤተሰብ ላላቸው በወር 4 ሺ ብር ፤ቤተሰብ ለሌላቸው ደግሞ በወር 2 ሺ […]

ናይጄሪያ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር ዘዴ አገኘሁ አለች፡፡

በናይጀሪያ የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር የተቋቋመ ኤጀንሲ አንድ ችግሩን ለመከላከል የሚያግዝ ቴክኖሎጂ ይፋ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡ ቴክኖሎጂው አይ ሪፖርት በመባል ይታወቃል፡፡ ሰዎች ባሉበት ሆነው ወንጀል ሲፈጸም ካዩ ለማዕከሉ ሪፖርት ማድረግ የሚያስችል በኢንተርኔት አማካይነት የሚሰራ መተግበሪያ ነው፡፡ እናም ማንኛውም ናይጄሪያዊ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ ግለሰቦችን በሚያይበት ወቅት ይሄን መተግበሪያ በመጠቀም ጉዳዩን ለሚመሩት ባለስልጣናት የማንቂያ መልእክት በመላክ […]

የጀዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ ኤም ኤን /OMN ) የአዲስ አበባ ቢሮ የፊታችን እሁድ በይፋ ይመረቃል፡፡

የጀዋር መሐመድ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ ኤም ኤን /OMN ) የአዲስ አበባ ቢሮ የፊታችን እሁድ በይፋ ይመረቃል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች እንዳስታወቀዉ በሚሊኒየም አዳራሽ የኦ ኤም ኤን ሥራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የሀገር ሽማግለዎችና ቄሮዎች በተገኙበት የቢሮ ምረቃና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳል ተብሏል፡፡

እንግሊዝ የዚምባቡዌ ነገር አሳስቦኛል ብላለች፡፡

አሁንም በአፍሪካ ምድር በምርጫ ማግስት ሰው ይገደላል፡፡ በዚምባቡዌ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤቱ ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡ የፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ዋነኛ ተፎካካሪ ሆነው በምርጫው የቀረቡት ኔልሰን ቻሚሳ የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ አሸናፊ ሆኗል መባሉን ባለመቀበላቸው ደጋፊዎቻቸው ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ ወጥተዋል፡፡ የምናንጋግዋ ወታደሮችም ሰልፈኞቹ ላይ ተኩሰዋል፡፡ እስካሁን 3 ሰዎች መገደላቸው ታወቋል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ መገናኛ ብዙሀን ቁጥሩን […]

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ13 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ በተለያዩ ትምህርት ክፍሎች ተመርምሮ፣ በየኮሌጆቹ አካዳሚክ ጉባኤዎች ተፈትሾና በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ ይሁንታ ያገኘውን መረጃ ተመልክቶ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡ በዚህም መሠረት፡-ፕሮፌሰር ተሾመ ሶሮመሳ፣ፕሮፌሰር አሰፋ ወልደማርያም፣ፕሮፌሰር ወርቅነህ ቀልቤሳ፣ፕሮፌሰር በቀለ አበበ፣ፕሮፌሰር ዳንኤል አሥራት፣ፕሮፌሰር ንጉሴ መገርሳ፣ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ለማ፣ፕሮፌሰር ጥላሁን ተክለኃይማኖት፣ፕሮፌሰር አበበ በቀለ፣ፕሮፌሰር ኃይሉ ወርቁ፣ፕሮፌሰር ሽመልስ አድማሴ፣ፕሮፌሰር ላይከማርያም አስፋውና ፕሮፌሰር አባተ ባኔ የሙሉ […]

ሩስያ በሺዎች ሚቆጠሩ የሰሜን ኮሪያ ዜጎች በሀገሯ ገብተዉ እንዲቀጠሩ ፈቀደች፡፡

ሞስኮ ታይምስ ከመቀመጫዉ ከሞስኮ እንደዘገበዉ በሩሰያ ከ10 ሺ በላይ ሰሜን ኮርያዉያን የስራ ፍቃደ ማግኘታቸዉን አረጋግጠዋል፡፡ ሩስያ የወሰደችዉ እርምጃ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፒዮንግያንግ ዜጎች ላይ ከሀገር ወጥተዉ እንዳይሰሩ የተጣለባቸዉን ማእቀብ የጣሰ ነዉ ተብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ጉዳዩን እያጣራሁ ነዉ ብሏል፡፡ ሩስያ ግን ስለጉዳዩ ለማንም ምላሽ አልሰጠችም፡፡ እስካሁን ሩስያ ዉስጥ የሚኖሩ ሰሜን ኮርያዉያን ወደሀገራቸዉ በየአመቱ እስከ 300 […]