loading
የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ለህክምና ወደ አቡዳቢ መጓዛቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2012 የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ለህክምና ወደ አቡዳቢ መጓዛቸው ተሰማ:: በቅርቡ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የተባረሩት ኬታ ህክምናቸውን ለመከታተል ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች መጓዛቸውን የቀድሞው የጦር አዛዣቸው ማማዱ ካማራ ተናግረዋል፡፡ ለአስር ቀናት ያህል በወታራዊ ጁንታው ቁጥጥር ስር የነበሩት ኬታ ባማኮ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል የህክምና ተቋም የጤናቸውን ሁኔታ ሲከታተሉ […]

ህንድ በኮቪድ 19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብራዚልን በመቅደም ሁለተኛዋ የዓለም ሀገር ሆነች፡፡

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2012 ህንድ በኮቪድ 19 በተያዙ ሰዎች ቁጥር ብራዚልን በመቅደም ሁለተኛዋ የዓለም ሀገር ሆነች፡፡ ህንድ በአንድ ቀን ብቻ ከ90 ሺህ በላይ አዲስ በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎችን በማስመዝገብ ብራዚልን ቀድማና አሜሪካንን ተከትላ ሁለተኛ ሀገር ሆናለች፡፡ አሁን ላይ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙባት ሁለተኛዋ ሀገር ስትሆን፤ በሟቾች […]

በሱዳን አሁንም የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ ተሰግቷል::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2012  በሱዳን አሁንም የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ ተሰግቷል:: በሱዳን የሚዘንበው ከባድ ዝናብ የራይል ወንዝ በ17.5 ሜትር ከፍ እንዲል በማድረጉ ከባድ ጥፋት እያስከተለ ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ሱዳን በታሪኳ ከ100 ዓመት ወዲህ እንዲህ የወንዝ ሙላት ገጥሟት አያውቅም፡፡ በዚህም ምክንያት በሱዳን ካለፈው በፈረንጆቹ ኦገስት መጨረሻ 100 ሺህ ቤቶች ሲወድሙ ወደ ከአንድ […]

የፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ልጅ የሞተው በገዳይ ንጥረ ነገር መሆኑን የቤተሰቡ ጠበቆች ተናገሩ ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2012 የፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ልጅ የሞተው በገዳይ ንጥረ ነገር መሆኑን የቤተሰቡ ጠበቆች ተናገሩ ::የቀድሞው የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ልጅ የሞተው በልብ ህመም ሳይሆን በአደገኛ ንጥረ ነገር ተመርዞ ስለመሆኑ መረጃ ደርሶናል ብለዋል ጠበቆቹ፡፡ የ25 ዓመቱ አብደላ ሙርሲ ከአንድ ዓመት በፊት መኪና በሚያሽከረክርበት ወቅት በድንገት የጡንቻ አለመታዘዝ እና መኮማተር ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም […]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን የአንድ ዓመት ወጪ ለመሸፈን ቃል ገባ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4፣ 2012 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን የአንድ ዓመት ወጪ ለመሸፈን ቃል ገባ:: ለ2013 ዓ.ም የሚሆን ስጦታ በሚል በመንግስት ሆስፒታሎች የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ህሙማን በሙሉ የአንድ ዓመት የህክምና ወጪ እንደሚሸፍን የከተማ አስተዳደሩ ቃል ገብቷል፡፡ ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን የምስጋና ቀን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ […]

አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ 551 ለሚሆኑ የፌዴራል ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4፣ 2012 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ 551 ለሚሆኑ የፌዴራል ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ:: የ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በፌዴራል፣ በክልልና በመከላከያ ወታደራዊ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ የፌዴራል ታራሚዎች በተለያዩ መስፈርቶች መነሻ ለ551 ታራሚዎ ይቅርታ ተደረገ ። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የይቅርታና ምህረት ቦርድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘለቀ ዳላሎ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ […]

የዳሽን ባንክ የጤና ሚኒስቴርን አመሰገነ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4፣ 2012 የዳሽን ባንክ የጤና ሚኒስቴርን አመሰገነ::ዳሽን ባንክ ኮሮናቫይረስን በመከላከል ረገድ የጤና ባለሙያዎችንና የጤና ሚኒስቴር እየከፈሉት ላሉት መስዕዋትነት ለማመስገን ለጤና ሚኒስቴር አበባ አበረከተ፡፡ ባንኩ ጳግሜ 4 የምስጋና ቀን እንደመሆኑ በዚህ ወቅት እጅግ በሚባል ሁኔታ መስዋትነት እየከፈሉ በኮቪድ 19 የተያዙ ህሙማኖችን እያከሙ ያሉ ጤና ባለሙያዎችን ለማመስገን አበባ ለጤና ሚኒስቴር እንዳበረከተ ገልጿል:: የጤና ባለሙያዎች […]

በሶማሊያ ሞቃዲሾ በደረሰ የሽብር ጥቃት በርካቶች መሞታቸው ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2012 በሶማሊያ ሞቃዲሾ በደረሰ የሽብር ጥቃት በርካቶች መሞታቸው ተነገረ፡፡ በሞቃዲሺ በሚገኝ አንድ ሬስቶራንት በደረሰ የቦንብ ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ 3 ሰዎች ህይወታቸው ወዲያው ሲያልፍ 7 ሰዎች መቁሰላቸውን የመንግስት ቃል አቀባይ ተናግሯል፡፡ የሀገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ሙክታር እንደገለጹት ጥቃቱን ያደረሰው አጥፍቶ ጠፊ ሞቃዲሾ ብሄራዊ ቲያትር ቤት አጠገብ ወደሚገኘው ሬስቶራንት በመግባት የያዘውን ቦንብ […]

ትራምፕ ኮሮረናቫይረስ አሜሪካዉያንን እንደጎዳ አመኑ::

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 5፣ 2012 ትራምፕ ኮሮረናቫይረስ አሜሪካዉያንን እንደጎዳ አመኑ::ሲ ኤን ኤን እንደዘገበዉ ትራምፕ ኮሮና ቫይረስ በአሜሪካ እነደተገኘ በመጀመሪያዎቹ ሳመንታት ቫይረሱ አደገኛ እንደሆነ ያዉቁ እንደነበር ተናግረዋል ብሏል፡፡ትራምፕ ከታዋቂዉ ጋዜጠኛ ቦብ ዉድዋር ጋር ባደረጉት የድምጽ ቅጂ ቃለ ምልልስ ፤ ኮሮና ቫይረስ በጣም አደገኛ በትንፋሽ የሚተላለፍ ፤በፍጥነት የሚዛመት ከዚህ በፊት ከነበሩ ጎንፋኖች በጣም ገዳይ መሆኑን ያዉቁ እንደነበር […]

የማሊ ወታደራዊ አዛዦች ከ18 ወራት በኋላ የሲቪል አስተዳደር ለማቋቋም ወሳኔ አሳለፉ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 የማሊ ወታደራዊ አዛዦች ከ18 ወራት በኋላ የሲቪል አስተዳደር ለማቋቋም ወሳኔ አሳለፉ:: ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታን በመፈንቅለ መንግስተር ከስልጣን አውርዶ ሀገሪቱን እየመራ ያለው የማሊ ወታደራዊ ጁንታ የሲቪል መንገስት ለመመስረት የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሏል፡፡ የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ማሊ ወደ ሲቪል አስተዳደር መመለስ አለባት ቢልም […]