loading
በትግራይ ጉዳይ የፀጥታው ምክር ቤት መግለጫ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አሳስቦኛል አለ፡፡ምክር ቤቱ ሁኔታውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በተለይ በሴቶች ላይ ተፈጸመ የተባለው የመደፈር ጥቃት በእጅጉ አሳሳቢ ነው ብሏል፡፡ በክልሉ በተፈጠረው ግጭት ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ሁኔታዎች አስቸጋሪ ናቸው ያለው ምክር ቤቱ ሁኔታው በፍጥነት መስተካከል አለበት ሲል አሳስቧል፡፡ ኢትዮጵያ […]

ያልተሳካው የህወሃት ቡድን ከሀገር የመውጣት ሙከራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013  የህወሃት አባላት ከሃገር ለመውጣት ያደረጉት ጥረት በመከላከያ ሰራዊት ከሽፏል ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ተናገሩ ሌተናል ጄኔራሉ ደበሌ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ፥ ከሃገር ለመውጣት ከሞከሩት የቡድኑ አባላት መካከል አብዛኛዎቹ መደምሰሳቸውን እና የተወሰኑት ወደኋላ ተመልሰው ሸለቆ ውስጥ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ ከሃገር ለመውጣትም መታወቂያ በማዘጋጀትና ስማቸውን በሌላ ማንነት በመቀየር በሱዳንና በአማራ ክልል አቋርጠው […]

የህንጻ ግንባታ ሳይት አፈር ተደርምሶ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 በአዲስ አበባ ከተማ ካዛንችዝ አከባቢ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አቅራቢያ በሚገኝ የህንጻ ግንባታ ሳይት አፈር ተደርምሶ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ ከደቂቃዎች በፊት በደረሰው የመደርመስ አደጋ በርካታ ሰዎች የተጎዱ ሲሆን ምናልባትም የሞቱ ሰዎች ሳይኖሩ እንደማይቀር ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ስለሁኔታው ዝርዝር መረጃ ሲደርሰን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡