loading
የአዲስ አበባ የወሰን እና ማንነት ጉዳይ በተመለከት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዚማ) የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ (አነን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ለዲሞክራሲ ክርክር አድርገዋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 የአዲስ አበባ የወሰን እና ማንነት ጉዳይ በተመለከት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዚማ) የኦሮሞ ነፃነት ንቅናቄ (አነን) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ለዲሞክራሲ ክርክር አድርገዋል፡፡በአርተስ ቴሌቪዥን የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክር መድረክ  በመቅረብ ሀሳባቸውን የሰጡት ሶስቱ ፓርቲዎች አዲስ  አበባን  በተመለከተ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያሉባት ከተማ መሆኗን በመግለፅ በተለይም  ከመልካም አስተዳደር እና ከፍተኛ  የሆነ የስራ አጥ […]

ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረዉ ገጀራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013  ሀሰተኛ ሰነድን ተጠቅሞ ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረው የእጅ ገጀራ ተያዘ የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ ከ15 ቀን በፊት በአስመጪ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ አንድ መቶ 86 ሺህ 240 የሆነ የእጅ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ተጓጉዞ ከደረሰ በኃላ ተይዟል፡፡ እቃው ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ […]

ዜጎች በምርጫ የሚሳተፉባቸው አማራጭ መንገዶች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 በምርጫ ወቅት ዜጎች በንቃት የሚሳተፉባቸው በርካታ አማራጭ መንገዶች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ገለጹ፡፡ በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲወለድ የዜጎች ንቁ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም በተግባር ሊያረጋግጡ ይገባል ብለዋል፡፡ ዜጎች በምርጫ ወቅት ተሳትፎአቸውን ከሚያረጋግጡባቸው መነገዶች አንዱ ካርድ ወስደው በሰላማዊ መንገድ የሚሆናቸውን ለመምረጥ ራስን ከማዘጋጀት ይጀምራል ነው […]

የሱዳን ተለዋዋጭ አቋም

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013  ሱዳን የግድቡ ድርድር እንዲሳካ የአፍሪካ ህብረት መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል ገለጸች::የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ህብረቱ በግድቡ ዙሪያ ያሉ አለመገባባቶችን በፍጥነት ለመፍታት በሚያደርገው ጥረት እምነት አለን ብሏል፡፡ ካርቱም በግድቡ ዙሪያ ያላትን አቋም ለማስረዳት የሱዳኗ የውጭ ጉደይ ሚኒስትር ማሪያም አልማሃዲ የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝታቸውን በይፋ ጀምረዋል፡፡ጉብኝቱ ከኬንያ ተጀምሮ ዲሞክራቲክ […]

የግብጹ አስዋን ግድብ አቅራቢያ በመሬት መንቀጥቀጥ መመታቱ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2013 የግብጹ አስዋን ግድብ አቅራቢያ በመሬት መንቀጥቀጥ መመታቱ ተገለጸ:: በግብጽ አስዋን ግድብ አቅራቢያ በትናንትናው ዕለት የመሬት መንቀጥቀጥ መመዝገቡን የአገሪቱ የአስትሮኖሚ እና ጂዮፊዚክስ ሃላፊን ጠቅሶ ኢጅፕት ኢንድፐንደንት ዘግቧል። የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከግድቡ ደቡባዊ አቅጣጫ ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የመሬት መንቀጥቀጡም በሬክተር ስኬል መለኪያ 3 ነጥብ 1 ሆኖ መመዝገቡ ተጠቁሟል። በዚሁ መሬት […]

የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ ምርጫው በስድስት ወር እንዲራዘም ጠየቀ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2013 የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ ምርጫው በስድስት ወር እንዲራዘም ጠየቀ:: በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተቀመጠውን መስፈርት አላሟሉም ተብለው ፈቃዳቸው ከተሰረዙ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የገዳ ፓርቲ መጪው ብሔራዊ ምርጫ በስድስት ወር እንዲራዘም ጠየቀ። የገዳ ሥርዓት ለኦሮሞ ነጻነት ፓርቲ-ገዳ ቢሊሱማ ከምርጫ ቦርድ ጋር በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲያካሄድ በነበረው ክርክር ፈቃዱ […]

በሰሜን አሜሪካ በአዉሮፓ በአዉስትራሊያ እና በአፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች ኢትዮጵያን የሚያፈርሱ አካሄዶችን እንደሚቃወሙ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2013 በሰሜን አሜሪካ በአዉሮፓ በአዉስትራሊያ እና በአፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች ኢትዮጵያን የሚያፈርሱ አካሄዶችን እንደሚቃወሙ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች ወቅታዊ የሀገራቸዉን ሁኔታ በተመለከተ ባወጡት የጋራ መግለጫ ፤ አደገኛ የዉስጥ ግጭት እና የዉጭ ከበባና ዛቻ ባለበት በዚህ የታሪክ ወቅት ልዩነታችን ላይ እያተኮርን የምንበታተንብት ጊዜ ሳይሆን፤ የተነሳብንን አደጋ በጥልቀትና አርቆ በማሰብ መርምረን በምን መልኩ […]

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቅሬታ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቅሬታውን ገለፀ ፡፡ የኢ/ያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዚያ 19 ባደረገው 7ኛ መደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚሳተፉ የማራቶን ተወዳዳሪ አትሌቶች በኑከራ ውድድር መምረጥ አስፈላጊ በመሆኑና በፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ኮሚቴ፣ በአሰልጣኞችና በአትሌቶቹም ጭምር በጋራ በተደረገ በመሆኑ እንድትሳተፉ ሲል በወንዶች የ12 እንዲሁም በሴቶች የ8 […]

የአብን ማሳሰቢያ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 የአገራችንን ምኅዳር ለአንድ ወገን ዘረኛና ያልተገራ ሽምጥ ግልቢያ የሚያመቻቹ ኃይሎች ከወዲሁ ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ሲል አብን አሳሰበ፡፡ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ባወጣዉ መግለጫ፤ የአማራ ሕዝብ በአገዛዙ ላይ የቀረውን ተስፋና በጎ ግምት ሁሉ አስተባብሎ መጨረሱን እና በየቦታው በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ጭፍጨፋና ፖለቲካዊ አሻጥር በማያሻማ ሁኔታ በአገር ቤትና በውጭ አገር […]

የፖሊስ ልዩ የበዓል ዝግጅት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2013 የስቅለት እና የትንሳኤ በዓላትን ምክንያት በማድረግ ወቅቱን ያገናዘበ የፀጥታ ዕቅድ አውጥቶ ወደ ተግባር መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡በበዓላት መዳረሻ ወቅቶች ከወትሮው በተለየ ጨምሮ የሚታየውን የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተከትሎ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት እና በተለይም በግብይት፣ በመዝናኛ ሰፍራዎች እና በዕምነት ተቋማት አካባቢ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ከወትሮው የተለየ ዝግጅት በማድረግ የፀጥታ […]