loading
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር እድሪስ ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ የተጠራው የጎዳና ላይ የአፍጥር ፕሮግራም በኛ በኩል እውቅና አልነበረውም አሉ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር እድሪስ ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ የተጠራው የጎዳና ላይ የአፍጥር ፕሮግራም በኛ በኩል እውቅና አልነበረውም አሉ:: ተቀዳሚ ሙፍቲው ይህን ያሉት የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት ነው፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር እድሪስ በመልዕክታቸው በዓሉ በሰላም […]

አውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎቼን ወደ ኢትዮጵያ እልካለሁ ማለቱ ተሰማ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 ህብረቱ ከአሁን ቀደም ምርጫውን ለመታዘብ ያስቀመጣቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጋፉ ቅድመ ሁኔታዎች በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት አላገኙም ነበር፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ሩሲያ፣ አሜሪካና ሌሎች ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ባለሙያዎቻቸውን እንደሚልኩ አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በመግለጫው የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮ ሱዳን የድንበር […]

አዲስ የግብይት አማራጭ ይዞ ብቅ ያለው አሪፍ ፔይ በአሜሪካን ሀገር በሚገኘው የፋይናስ ተቋም አሸናፊሆነ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 አዲስ የግብይት አማራጭ ይዞ ብቅ ያለው አሪፍ ፔይ በአሜሪካን ሀገር በሚገኘው የፋይናስ ተቋም አሸናፊሆነ፡፡ አፍሪ ፔይ ሰዎች የዕለት ተዕለት ግብይቶቻቸውን ጨምሮ የመብራትና የውሃ አገልግሎቶችን በቀለሉ መክፈል የሚያስችላቸው የክፍያ ሲስተም ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ በተለይም በገጠር አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቀላሉ ግብይት የሚፈፅሙበት እና የብድር አግልግሎት የሚያገኙበት እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡ […]

በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እናስቁም በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እናስቁም! በሚል ነፃ የሰልክ መስመር ተዘጋጀ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013 በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እናስቁም በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እናስቁም! በሚል ነፃ የሰልክ መስመር ተዘጋጀ:: የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ከዩ ኤን ኤፍ ፒ ኤ እና ካናዳ ኢምባሲ ጋር በጋራ በመሆን የህግ ድጋፍ እና ማማከር አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎችም አገልግሎቶችን በዘላቂነት የሚሰጥ 7711 ነፃ የስልክ […]

የቤተክርስቲያኗን የአደባባይ በዓላት በአለማዊ ክንዋኔዎች እንዳይበረዙ መጠበቅ ያስፈልጋል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013 የቤተክርስቲያኗን የአደባባይ በዓላት በአለማዊ ክንዋኔዎች እንዳይበረዙ መጠበቅ ያስፈልጋል ተባለ::የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት የሰበካ ጉባኤ የአደባባይ በዓላት ስኬቶችና ተግዳሮቶች በሚል ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ የቤተክርስቲያኗን የአደባባይ በዓላት የበዓላቱን አከባበር ዝግጅት የሚያስተባብር ቋሚ አደረጃጀት ሊኖር ይገባል ብሏል፡፡ በጉዳዩ ላይ መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት መምህር ማለዳ ዘሪሁን […]

ከህግ ያፈነገጠው የአማኑኤል ወንድሙ ግድያ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013   የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ደንቢ ዶሎ ቄለም ወለጋ ዞን በግንቦት 3 2013 ዓም በ ፀጥታ ሀይሎች በአደባባይ ላይ የተገደለው አማኑኤል ወንድሙ ሞት እጅግ ጭካኔ የተሞላበት እና ከህግ ያፈነገጠ ነው ሲል ገልጸ፡፡ ኮሚሽኑ ሁሉንም አይነት ህገ ወጥነት የሞላባቸው ግድያዎችን እንደሚቃወም የገለፀ ሲሆን ሰላም አስከባሪ ሀይላት ሰላም በማስከበሩ […]

በአብዬ በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ ለተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ- 19 ክትባት ተሰጣቸው፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013  በአብዬ በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ ለተሰማሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ- 19 ክትባት ተሰጣቸው፡፡ በሱዳን አብዬ ግዛት የሚገኙት የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስለባሪ ሻለቃ አባላት አስትራዜኒካ የተባለው የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ነው የተሰጣቸው፡፡ የሻለቃው የህክምና ሃላፊ ሻለቃ ፀሃይ በላቸው ሰራዊቱ እራሱን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል የተሰጠውን አገራዊና […]

ማኅበረሰቡ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሳበ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013 ማኅበረሰቡ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሳበ፡፡ ኢንስቲትዩቱ በህንድ የተከሰተው አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ አሳሳቢ እየኾነ መምጣቱን በማስታወስ ማህበረሰቡ እንዳይዘናጋ አስጠንቅቋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በህንድ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ዓለም አቀፍ ስጋት እየሆነ እንደመጣ መግለጹን ኢኒስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡ ቫይረሱ እስካሁን በ44 ሀገራት እንደተሰራጨ መገለጹን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል፡፡ […]

በሱዳን በኩል ወደ ሀገር ሊገባ ሲል የተደመሰሰው የህወሃት ቡድን

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2013 ከሱዳን በመነሳት በማይካድራ አድርገው ወደ ሀገር ሊገቡ የነበሩ 320 የህወሃት ሀይል አባላት ተደመሰሱ፡፡ የህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ሀላፊ ተወካይ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳሉት ይህ ቡድን በማይካድራ ጭፍጨፋ አድርሶ ወደ ሱዳን ሸሽቶ የነበረ ነው፡፡ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ በሰጡት መግለጫ ቡድኑ ዳግም ተደራጅቶ የተለያዩ የመገናኛ መሳሪያዎችንና መድሀኒቶችን በመያዝ ወደ […]

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉ አለፈ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2013 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 20 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉ አለፈ፡፡ የጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰአታት የኮቪድ 19 ስርጭት መረጃ ባሳወቀበት ወቅት እንደገለጸዉ፤ ባለፈት 24 ሰኣታት ዉስጥ 20 ሰዎች በኮቪድ 19 ህወታቸዉን አጥተዋል፡፡ የህም ባጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎችን ቁጥር 3 ሺህ 9 መቶ 96 ደርሷል፡፡ ባለፉት 24 […]