loading
የፒኮክ መናፈሻ አዲስ ዙ ፓርክ ተከፈተ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4፣ 2013  የፒኮክ መናፈሻ አዲስ ዙ ፓርክ በይፋ ተመርቆ ተከፈተ ። ፓርኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታአቶ ጌታቸው ኃይለማርያም ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ባለድርሻ አካላትና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ተመርቆ በይፋ ስራ […]

በኢትዮጵያ ኮሮና ወረርሽኝ የመያዝና በቫይረሱ የመሞት ምጣኔ መቀነሱ ተነገረ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013 በኢትዮጵያ ኮሮና ወረርሽኝ የመያዝና በቫይረሱ የመሞት ምጣኔ መቀነሱ ተነገረ:: የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው ዓባይነህ በኮሮና ወረርሽኝ የመያዝና በቫይረሱ የመሞት ምጣኔ መቀነሱን አስታውቋል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት መቀነሱ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከጤና ሚኒስቴር ጋር ለ15 ወራት ሥጋት ሆኖ በዘለቀው የኮሮና ወረርሽኝ ላይ የተደረጉ የምርምር ጥናቶች […]

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ራሳቸዉን ከምርጫ አገለሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7፣ 2013  ለመጪው ሀገራዊ ምርጫ በግል ለመወዳደደር ተመዝግበው የነበሩት ኡስታዝ አህመድ ጀበል በምርጫው እንደማይሳተፉ ተናገሩ፡፡ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በምርጫው ለመሳተፍ እንቅስቃሴ እያደረጉ የቆዩ ቢሆንም በግል ምክንያት እራሳቸውን ማግለላቸውን በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። ኡስታዝ አህመዲን ጀበል 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጅማ ከተማ ተወካይ ለመሆን እጩ ሆነው ቀርበው ነበር። […]

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጊዜያዊ ስምምነት ለማድረግ ጠየቀች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013 ሱዳን ከኢትዮጵያነ ጋር በግድቡ ዙሪያ ጊዜያዊ ስምምት ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አለች፡፡ የሱዳኑ የውሃ ሚኒስትር ያሲር አባስ ካርቱማ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ከመጀመሯ አስቀድሞ በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ጊዜያዊ ውል ማሰር አለብን ብለዋል፡፡ ሚንስትሩ እንደ ቅድመ ሁኔታ አድርገው ካነሷው ነጥቦች መካከልም ከአሁን ቀደም የደረስንባቸው ስምምነቶችና […]

ላውረን ባግቦ ወደ ሀገራቸው ሲገቡ ፕሬዚዳንታዊ አቀባበል ሊደረግላቸው መሆኑ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013  የቀድሞው የኮትዲቯር ፕሬዚዳንት ላውረን ባግቦ ከአስር ዓመት ስደት በኋላ በመጭው ሀሙስ ወደ ሀገራቸው እንደሚገቡ የፓርቲያቸው ዋና ፀሃፊ ተናግረዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲያቸው ፖፑላር ፍሮንት በሰጠው መግለጫ ባግቦ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ በቪአይፒ ክፍል እንዲያርፉ ተደርጎ ፕሬዚዳንታዊ የክብር አቀባበል ይደረግላቸዋል ብሏል፡፡ የቀድሞ ተቀናቃኛቸውና የወቅቱ ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ባግቦ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው […]

ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ዳግም ወደ ጥብቅ የእንቅስቃሴ እቀባ ተመለሰች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013 ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ በሰጡት መግለጫ በሀገሪቱ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በ59 በመቶ መጨመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የምሽት የሰዓት እላፊ እና የአልኮል ሽያጭ ላይ ገደቦችን መጣል ግድ ሆኖብናል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፡፡ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ሲባል ከምሽቱ አራት ሰዓት እስከ ሌሊቱ አስር ሰዓት ያሉ እንቅስቃሴዎች እንዲገደቡ […]

ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉት አራት ቀናት የጥሞና ወቅት ናቸዉ ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013   ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉት አራት ቀናት የጥሞና ወቅት በመሆናቸዉ የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ  እንደማይደረግባቸዉ ተገለፀ የጥሞና ወቅት በቅድመ የምርጫ ዑደት ውስጥ የሚገኝ ጊዜ ሲሆን በኢትዮጵያ የምርጫ ዑደት መመሪያ መሠረት ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉትን አራት ቀናት ያካትታል የሚያትት ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች እና ደጋፊዎቻቸው ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚየካሂዱት የምርጫ ውድድር […]

በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አግባብ አይደለም-¬ቻይና፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11፣ 2013 ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደማያስፈልጋት ቻይና ገለጸች፡፡ አምባሳደር መለስ ዓለም በኬንያ ከቻይና አምባሳደር ዦ ፒንጂያን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅት አምባሳደሩ በአገሮች የውስጥ ጉዳይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት ቻይና እንደምትቃወም ተናግረዋል። የውስጥ ጉዳይ የየአገራቱ ኃላፊነት በመሆኑ ሌሎች አገሮች በተናጥል ጣልቃ መግባት እንደሌለባቸው አምባሳደር ፒንጂያን […]

ዛምቢያ የነፃነት አባቷን በሞት ተነጠቀች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11፣ 2013 በዛምቢያዊያን ዘንድ የነፃነት አባት በመባል የሚታወቁት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኬኔት ካውንዳ በ97 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ካውንዳ ከቀናት በፊት ሉሳካ ወደሚገኘው ወታደራዊ ሆስፒታል ገብተው ህክምናቸውን ቢከታተሉም ሀኪሞቻቸው ህይዎታቸውን ማትረፍ አልተቻላቸውም፡፡ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በሰጡት መግለጫ በሽታቸው ከሳንባ ምች ጋር የተገናኘ እንደሆነ ይፋ አድርገዋል፡፡ ረዳታቸው ሮድሪክ ንጎሎ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት ቃለ […]

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በምርጫ ጣቢያ 05 የክልል ምክር ቤት የምርጫ ወረቀት በመቀያየሩ ምርጫው ከ 2 ሰዓት ተኩል በላይ ዘግይቷል፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14፣ 2013 በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በምርጫ ጣቢያ 05 የክልል ምክር ቤት የምርጫ ወረቀት በመቀያየሩ ምርጫው ከ 2 ሰዓት ተኩል በላይ ዘግይቷል፡፡ በክፍለ ከተማው ወረዳ 3 በምርጫ ክልል 23 የቦሌ ክፍለ ከተማ የምርጫ ወረቀቶች በስህተት በመላካቸው ነው ምርጫው በሰዓቱ ያልተጀመረው፡፡ በዚህ የምርጫ ክልል ለአዲስ አበባ ክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩት ምክትል […]