loading
በቡርኪናፋሶ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት ብዙዎች ህይወታቸዉ አለፈ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30፣ 2013  በቡርኪናፋሶ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት የሟች ቁጥር ከ130 በላይ መድረሱ ተሰማ  መረጋጋት በተሳነው ምእራባዊ የሀገሪቱ ክፍል የ132 ሰዎችን ህይዎት የቀጠፈውን የታጣቂዎች ጥቃት የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በፅኑ አውግዞታል፡፡ ታጣቂቂዎች ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ጥቃቱን ያደረሱት ዮጋ ተብላ በምትጠራው ግዛት በምትገኘውና ከኒጀር ጋር በምትዋሰነው የሶልሃን መንደር ነው፡፡ የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት […]

በቤት ሰራተኛዋ ላይ ግፍ ስትፈፅም የቆየችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1፣ 2013  የቤት ሰራተኛዋን ከ1 ዓመት በላይ ከቤት እንዳትወጣና ምግብ በመከልከል ከፍተኛ በደል ስትፈፅም የነበረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ገልጿል። የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሲ.ኤም.ሲ አልታድ መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ ተጠርጣሪዋ በቤት ሰራተኛዋ ላይ ከፈፀመቻቸው አሰደቃቂ ድርጊቶች መካከል ከቤት እንዳትወጣና የፀሃይ ብርሃን እንዳታገኝ ማድረግ፣ ከፍተኛ […]

ሕገ ወጥ ግብይት ለምግብ ደኅንነት ችግር ቀዳሚ መንስኤ ነው-ኢንስቲትዩቱ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1፣ 2013 ሕገ ወጥ ግብይት ለምግብ ደኅንነት ችግር ቀዳሚ መንስኤ ነው-ኢንስቲትዩቱ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከ40 በመቶ በላይ ሕጻናት የምግብ ደኅንነት ችግር እንደሚገጥማቸው ገለጸ፡፡በኢንስቲትዩቱ የምግብ ሳይንስ እና የስነ-ምግብ ምርምር ዳሬክተር ዶክተር ማስረሻ ተሰማ በምግብ ደኅንነት ዙሪያ በርካታ ችግሮች እንደሚስተዋሉ ነው የገለጹት፡፡ ዳይሬክተሩ ከ40 በመቶ በላይ ሕጻናት ከምግብ ደኅንነት ችግር ጋር በተየያዘ […]

አፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ ማግኘት እንሚገባው ኬኒያ አሳሰበች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1፣ 2013 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋረ ከኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሪይቸል ኦማሞ ጋር በሁለትዮሽ እና በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ በጽሕፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል። አምባሳደር ሬድዋን በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንዲሁም የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለአምባሳደሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል። […]

ቦርዱ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት የገጠማቸውን የምርጫ ክልሎች ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት መከሰቱን አረጋግጫለሁ አለ፡፡ ቦርዱ ይህን ያለው በሎጀስቲክስ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ባደረገው ውይይት ነው፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሪፖርታቸውን በዝርዝር ካቀረቡ በኋላ ከፓርቲዎች ጋር በችግሮቹና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ […]

የአፍሪካ ቀንድን የሚያስተሳስረው የልህቀት ማእከል ዕውን ሊሆን ነው…

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 የአፍሪካ ቀንድን የሚያስተሳስረው የልህቀት ማእከል ዕውን ሊሆን ነው… በኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ550 ሚሊዮን ብር በጀት የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክ ትምህርትና ስልጠና የልህቀት ማዕከል ግንባታ ተጀመረ፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹትበኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የበለጸገ ብቁ ዜጋ ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ ሚንስትሩ ለግንባታው ከ550 ሚሊዮን ብር […]

በሱዳን የተከሰተው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የህዝባዊ አመፅ ስጋት ፈጥሯል ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 በሱዳን የተከሰተው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የህዝባዊ አመፅ ስጋት ፈጥሯል ::ሱዳን ድጎማ ማንሳቷን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በሊትር የ140 የሱዳን ፓውንድ ጭማሪ ማሳየቱ ተሰማ፡፡ ካርቱም የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት ምክር ተቀብላ የነዳጅ ድጎማ ማንሳቷ ያስከተለው የዋጋ ንረት ህዝባዊ ከባድ አመፅ እንዳይቀሰቀስ ስጋት ላይ ጥሏታል ነው የተባለው፡፡ በዚህም የተነሳ ለአልበሽር ከመንበራቸው መወገድ […]

የግድቡ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ የወቅቱ ወሳኝ ጥያቄ ነው ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 በታላቁ የህደሴ ግድብ ግንባታ ዓለም አቀፍ የውሃ ህጎች ላይ የሚመክር 9ኛው ሃገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉባኤ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ተጀመረ። ለሁለት ቀን በሚቆየው ጉባኤ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዓለም አቀፍ የውሃ ህጎችን መሰረት ያደረጉ ሰባት ጥናታዊ ፅሁፎች በምሁራን ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ታውቋል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ድኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ […]

ልብን ለማዳን የልበ ቀናዎች የዘወትር ትጋት ያስፈልጋል…

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2013 ማህበራዊ ድረ ገፅን ለበጎ አላማ በማዋል ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል አንድ ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ፡፡ ማህበራዊ ድረ ገፅን ለበጎ አላማ የማዋል ዓላማ ይዛ በመነሳት የገንዘብ ድጋፉን ያሰባሰበችው ነዋሪነቷን በአሜሪካ ሀገር ያደረገች ህይወት ታደሰ የተበለች ጋዜጠኛ ናት፡፡ የማዕከሉ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አርቲስት መሰረት መብራቴ በርክክቡ ወቅት በተለይም ማህበራዊ ሚድያን […]

ኢትዮጵያ የላሙን ወደብ ልትጠቀም ነዉ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4፣ 2013 የኬንያ መንግስት የላሙ ወደብ ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት ሁኔታዎችን እያመቻች መሆኑን ገለጸ:: የኬንያ መንግስት የላፕሴት ኮሪደር ልማት አካል የሆነውን የላሙ ወደብ ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት ሁኔታዎችን እያመቻች መሆኑን ገልጿል። የላፕሴት ኮሪደር ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ሚኒስትር ሜና አኬንዶ በኬንያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ጉብኝት በማድረግ ከአምባሳደር መለስ ዓለም ጋር ተወያይተዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚው የኢትዮጵያ […]