loading
ትራምፕ ነጩን ቤት ከመልቀቃቸው በፊት በቀረቻቸው ሽርፍራፊ ሰዓት አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው::

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 ትራምፕ ነጩን ቤት ከመልቀቃቸው በፊት በቀረቻቸው ሽርፍራፊ ሰዓት አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው:: የትራምፕ የቅርብ ሰዎች በተለይ ለስቲቭ ባኖን ይቀርታ እንዳያደርጉ ቢመክሯቸውም በምጫው ያነሱትን ቅሬታ በመደገፋቸው ነው ይቅርታው የተደረገላቸው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡

በምዕራብ ጉጂ ዞን የጥምቀት በዓል በሰላም መከበሩ ተገለፀ ::

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 በምዕራብ ጉጂ ዞን የጥምቀት በዓል በሰላም መከበሩ ተገለፀ :: የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች የከተራና የጥምቀት በዓል በሠላም ተከብሯል ፡፡ በዓሉን በ ገላና ወረዳ ከቶሬ ከተማ የከበሩ ነዋሪች በሰጡት አሰተያየት የዘንድሮ የጥምቀት በዓል ልዩ ነው የሌላ እምንት ተከታዮች ለበአሉ ድምቀት ያደረጉት በጎ ተግባር ፍቅራችን ይበልጡን እንዲዳብር አድርጎታል ብለዋል፡፡ […]

ቱኒዚያዊያን በመንግስት ላይ የጀመሩት ተቃውሞ ከአራት ቀናት በላይ አስቆጥሯል::

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 ቱኒዚያዊያን በመንግስት ላይ የጀመሩት ተቃውሞ ከአራት ቀናት በላይ አስቆጥሯል:: ተቃዋሚዎቹ ጎዳናዎችን በመዝጋትና ቁሳቁሶችን በእሳት በማቀጣጠል ቁጣቸው በአደባባይ ሲያሰሙ ታይተዋል፡፡ የተቃውሟቸው መነሻ በሀገሪቱ የተንሰራፋው ድህነትና የስራ አጥነት መባባስ መሆኑን ለተቃውሞ በወጡበት ወቅት ገልፀዋል፡፡ አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው ሰልፈኞቹ የተለያዩ ሱቆችንና የንግድ ተቋማትን በመዝረፍ ተግባር ላይ መሰማራታቸውም ተሰምቷል፡፡ ይህን ተከትሎም የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰይድ […]

ኢራን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ወታራዊ ልምምዶችን ማድረጓ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 ኢራን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ወታራዊ ልምምዶችን ማድረጓ ተሰማ፡፡ የአሜሪካ ቢ 52 ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች በመካከለኛው ምስራቅ መብረራቸውን ተከትሎ ቴህራን በሀገሪቱ ደቡባዊ ጠረፍ አካባቢ ከባድ ልምምዶችን አድርጋለች ነው የተባለው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ባለፈው ጃኑዋሪ 3 በጄኔራል ቃሲም ሰይማኒ ላይ ግድያ ከተፈፀመ ወዲህ የአሜሪካ ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች በአካባው ሲበሩ የመጀመሪያቸው ነው፡፡ ኢራን በሁለት […]

ግብፅ በመላ ሀገሪቱ ጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአስራአምስተኛ ጊዜ አራዘመች::

አዲስ አበባ፣ጥር 16፣ 2013  ግብፅ በመላ ሀገሪቱ ጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአስራአምስተኛ ጊዜ አራዘመች:: በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ተግባዋ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አቃጅ ዳግም የታደሰው በፓርላመው ውሳኔና በፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ይሁንታ ነው፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ግብፅ የመጀመሪያውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጣለቸው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2017 ነበር፡፡ በወቅቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገው የሽበርተኝነትን አደጋ ለመከላከል በሚል […]