loading
ኑ ለኢትዮጵያና ስለድኻው ወገናችን ስንል ዝቅ እንበል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሚቻለውን በቀለኝነት ትተን የማይቻለውን ይቅርታ እንዘምር ሲሉ መልእክት አስተላለፉ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የጥምቀትን በዓል አስመልክተው ለክርስትና እምነት ተከታዮች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዚሁ መልእክታቸው ፍቅራችንን፣ ትህትናችንንና ክብራችንን ለሀገራችንና ለወገናችን እናሳይ፣ በተለመደው መንገድ ብቻ ሄደን ሀገራችንን እንደማናድናት እንገንዘብ ብለዋል። ኑ ለኢትዮጵያና ስለድኻው […]

በታላቁ ቤተ-መንግሥት የዕራት መርሐ-ግብር ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 በታላቁ ቤተ-መንግሥት የዕራት መርሐ-ግብር ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡ በታላቁ ቤተ-መንግሥት በተካሄደው የዕራት መርሐ-ግብር ከትኬት ሽያጭ በቀጥታ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ። በመርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዳያስፖራ አደረጃጀት መሪዎች፣ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር […]

የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ሃይማኖታዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ ህዝበ ክርስቲያኑ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ጥሪ አቀረበች።

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ሃይማኖታዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ ህዝበ ክርስቲያኑ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ጥሪ አቀረበች። የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል እንደ ወትሮው ሁሉ ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዝግጅት ማድረጓን በቤተ ክርስቲያኗ የብፁዕ ወ ቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽህፈት ቤትና የውጭ ጉዳይ […]

ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ከክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል አንዱ የሚገኝበትን ቀብሪበያን […]

ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት እርዳታ ተስተጓጉሏል

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት እርዳታ ተስተጓጉሏል አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በኩል በከፈተው አዲስ ጥቃት ምክንያት የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ መቀሌ ሲጓዙ የነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደኋላ ለመመለስ መገደዳቸው ተገለፀ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ህወሓት በአፋር በኩል እየፈፀመ ባለው ትንኮሳ እና ወደ መኖሪያ አካባቢዎች […]

የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት የአገራቱን የሻከረ ግንኙነት እንደሚያስተካክለው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት የአገራቱን የሻከረ ግንኙነት እንደሚያስተካክለው ተገለጸ የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ በዚህ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሻከረውን የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማስተካከል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡ አምባሳደር ዲና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት […]

የወይብላን ጉዳይ ለማጣረት በግብርኃይል እየተመረመረ ነው- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን የተፈጸመውን ድርጊት ግብርኃይል ተቋቁሞ እየመረመረ እንደሚገኝ መንግሥት አስታወቀ፡፡የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ ግብርኃይሉ ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጣ እንደሆነ ገልጸው ውጤቱ ሲደርስ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ብለዋል፡፡ ሌሎች […]

አሸባሪው ህወሓት እንደ አዲስ ከወረራቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጣና በቀጠናው የከፈተውን ጦርነት እንዲያቆም የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሳሰበ።

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 አሸባሪው ህወሓት እንደ አዲስ ከወረራቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ እንዲወጣና በቀጠናው የከፈተውን ጦርነት እንዲያቆም የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሳሰበ።የክልሉ መንግስት በጉዳዩ ላይ በሰጠው መግለጫ ከሰሞኑ አሸባሪው ቡድን በተደራጀ መልኩ በአብአላ፣ በመጋሌና ኤረብቲ ወረዳዎችን በመቆጣጠር እና በራህሌ ወረዳንም ከፊል ቀበሌዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት ከባድ ጥቃት ከፍቶ ንፁሀንን በመግደል እና በማሳደድ ወረዳዎቹን እያወደመ እንደሚገኝና […]

የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ ፈተናዎቿን በድል ተሻግራ ችግሯን በራሷ ፈታ ወደፊት የቀጠለች መሆኑን የምናሳይበት ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ::

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ ፈተናዎቿን በድል ተሻግራ ችግሯን በራሷ ፈታ ወደፊት የቀጠለችመሆኑን የምናሳይበት ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ::የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡትመግለጫ በአዲስ አበባ የሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያ ፈተናዎቿንበድል ተሻግራ በቁርጥ ቀን ልጆቿ ችግሯን በራሷ ፈታ ወደፊት የቀጠለች መሆኑን […]

በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የሕክምና ድጋፎች ለመስጠት አንድ መቶ በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ወደ አማራ ክልል አቀኑ።

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የሕክምና ድጋፎች ለመስጠት አንድ መቶ በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ወደ አማራ ክልል አቀኑ። የሕክምና ባለሙያዎቹ ከጥር 22 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል የሕክምና ምርመራ፣ ሕክምናና የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፤ መድኃኒትም ያቀርባሉ ተብሏል። በጎ ፍቃደኞቹ የሕክምና ድጋፋቸውን የሚሰጡባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ሸዋሮቢት፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ […]