loading
በባንኮች ላይ እተፈጸመ ያለው የማጭበርበር ወንጀል አሳሳቢ ሆኗል-ፍትህ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 ፍትህ ሚኒስቴር በጥናት ደረስኩበት ያለውን በባንኮች ላይ የተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ይፋ አደረገ፡፡ ሚኒስቴሩ በጉዳዩ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት በባንኮች ላይ ከ370 ቢሊዮን ብር በላይ የማጭበርበር ወንጀል ሙከራ ተደርጓል ብሏል። በዚህም በተለያዩ ባንኮች ከ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ምዝበራ እንደተፈጸመባቸው ነው የተነገረው፡፡ […]

በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የተመረቀው ማዕከሉ ቀድሞ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ እንደሚያሳድገው ተነግሯል፡፡ ይህም ለኩላሊት ህመምተኞች እፎይታን ይሰጣል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት ከከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕከሉን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ባዩት […]

ውስጣዊና የውጭ ጫና የበረከተባት ሱዳን የጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 ውስጣዊና የውጭ ጫና የበረከተባት ሱዳን የጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳች፡፡ ወታደራዊ አስተዳደሩን የሚመሩት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ከወራት በፊት ተጥሎ የነበረው የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ መነሳቱን ይፋ ሲያደርጉ ከአዋጁ ጋር በተገናኘ የታሰሩ ሰዎች እደሚፈቱም ፍንጭሰጥተዋል ተብሏል፡፡ የአዋጁ መነሳት የተሰማው በሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ በሳምንቱ መጨረሻ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ባፀጥታ ሃይሎች መገደላቸው […]

በከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት

አዲስ አበባ፣ግንቦት 23፣2014 ባለሀብቶችን በመሰለል፣ በማገት እና በማስፈራራት ገንዘብ በጠየቁ እና በተቀበሉ የመከላከያ ሚኒስቴር አባላትና ግብረአበሮቻቸው ላይ ክስ ተመሰረተ፡፡ ወንጀሉን ፈጽመዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው በመከላከያ ሚኒስቴር በ93ኛ እና 94ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር አባል የሆኑት 1ኛ መቶ አለቃ ሀጂ ቱሉ߹ 2ኛ ኦፊሰር መንግስቱ በቀለ߹ 3ኛ ሻምበል ካህሊ መላክ߹ 4ኛ ሻለቃ ዱጉማ ዲምሳ ናቸው፡፡ በንግድ ስራ ተሰማርተው […]

በመጪው የክረምት ወቅት ጎርፍና መሰል አደጋዎች ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ስለሚኖር የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

አዲስ አበባ፣ግንቦት 23፣2014 በመጪው የክረምት ወቅት ጎርፍና መሰል አደጋዎች ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ ስለሚኖር የጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ። ሰሞኑን የታየው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች የመጣ መሆኑተጠቁሟል። በኢንስቲትዩቱ የአየር ሁኔታና የአየር ጠባይ ትንበያ ባለሙያው ታምሩ ከበደ እንደገለጹት፤በቀጣዩ ክረምት ወቅት ከመደበኛው በላይ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ትንበያዎች ያመለክታሉ። የላሊና […]

ቻይና የታይዋን የአየር መከላከያ ክልል ጥሳ በመግባት የጠብ አጫሪነት ተግባር እየፈጸመች ነው ስትል አሜሪካ ወቀሰች፡፡

አዲስ አበባ፣ግንቦት 23፣2014 ቻይና የታይዋን የአየር መከላከያ ክልል ጥሳ በመግባት የጠብ አጫሪነት ተግባር እየፈጸመች ነው ስትል አሜሪካ ወቀሰች፡፡ የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ 30 የቤጂንግ የውጊያ አውሮፕላኖች ወደ አየር ክልላችን ዘልቀው ገብተዋል፤ ከነዚህ መካከል ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑት ተዋጊ ጄቶች ናቸው ብሏል፡፡ ቻይና በታይዋን ሁለተኛውን ግዙፍ ወታደራዊ ቅኝት ያደረገችው ትንሿ ደሴት ከአሜሪካ ጋር በደህንነትና በፀጥታ ዙሪያ […]

አዲሱ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ መሆን…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 በቅርቡ የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡ በዚህም መሰረት በሚኒ ባስ እና በሚዲ ባስ ተሸከርካሪዎች ከ50 ሳንቲም እስከ 3 ብር ከ50 ሳንቲም ጭማሪ ስለመደረጉ ተነግሯል፡፡ ጭማሪው ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከታሪፍ በላይ ክፍያ የሚጠይቁ አገልገሎት ሰጭዎች ካጋጠሙ ማህበረሰቡ ለሚመለከተው አካል […]

የመመስረቻ መስፈርት አሟልተው የተገኙ ስምንት አዳዲስ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 የመመስረቻ መስፈርት አሟልተው የተገኙ ስምንት አዳዲስ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡በፋይናንስ ዘርፉ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ለውጦችን ተከትሎ በርካታ ባንኮች የመመስረቻ ፈቃድ ለማግኘት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ቁጥጥር ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው ባንክ ለመመስረት የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የካፒል መጠን ከ500 ሚሊዮን ወደ 5 ቢሊዮን ብር ከፍ መደረጉን አስታውሰው […]

ሞሳድ የኢራኑን ፕሬዚዳንት ለመግደል አሲሯል-የኢራን የስለላ ምንጮች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 እስራኤል የኢራኑን ፕሬዚዳንት ለመግደል ማቀዷን ደርሸበታለሁ ሲል የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አስታወቀ፡፡ ቴልአቪቭ ይህን የምታርገው በኢራን መረጋጋት እንዳይፈጠር ለማድረግ መሆኑንም አብዮታዊ ዘቡ አብራርቷል፡፡ ተቋሙ በይፋዊ የቴሌግራም ቻናሉ ባሰፈረው ጽሁፍ የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከቴህራን ውጭ በሚገኙበት ወቅት ግድያው እንዲፈጸምባቸው እቅድ መንደፉን የደህንነት መረጃ ያላቸው ምንጮች ነግረውኛል […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር በሀገራዊና ቀጠናዊ ዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር በሀገራዊና ቀጠናዊ ዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡ ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያና ጣሊያን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ምሽት አዲስ አበባ […]