loading
ኢንጂኔር ታከለ ኡማ በከንቲባነት ዘመናቸው ላደረጉላቸው ድጋፍ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አመሰገኑ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ኢንጂኔር ታከለ ኡማ በከንቲባነት ዘመናቸው ላደረጉላቸው ድጋፍ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አመሰገኑ:: ከአዲስ አበባ ከንቲባነት ቦታቸው ተቀይረው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ሆነው የተሸሙትምክትል ከንቲባው በነበራቸው የሁለት ዓመት የሥራ ዘመን የከተማዋ ነዋሪዎች እና የስራ ባለደረቦቻቸው ድጋፍ እንዳልተለያቸው በፅህፈት ቤታቸው ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ አስፍረዋል፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ይህችን ታሪካዊ ከተማ ለመምራት የተገኘውን ትልቅ ዕድል ላለማባከን […]

ሱዳናዊያን በሀገሪቱ የስልጣን መጋራት ስምምት የተደረገበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ሰልፍ አካሂደዋል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ሱዳናዊያን በሀገሪቱ የስልጣን መጋራት ስምምት የተደረገበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ሰልፍ አካሂደዋል:: ነዋሪዎቹ ካርቱም ውስጥ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ አሁን ባለው የሉዓላዊ ምክር ቤት አስተዳደር ቅሬታ እንደገባቸው ተናግረዋል፡፡ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት ፕሬዚዳንት አልበሽርን በሃይል ከስልጣናቸው ያስወገዱት ጄኔራሎችና ህዝቡን ወክለው ስልጣን የተጋሩት ፖለቲከኞች ሀገር መምራት ከጀመሩ አንድ ዓመት ቢያስቆጥሩም የተፈለገው ለውጥ አልመጣም በማለት ነው፡፡ […]

የሞሳድ ሹም በአቡዳቢ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 የሞሳድ ሹም በአቡዳቢ የእስራኤሉ ሞሳድ የስለላ ድርጅት ሀላፊ በደህንነት ዙሪያ ለመወያየት አቡዳቢ ገብተዋል:: ሀላፊው ዮሲ ኮኸን እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የዲፕሎማሲ ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ አቡዳቢን የጎበኙ የመጀመሪያው ባለ ስልጣን ሆነዋል፡፡ ኮኸን ከኤሜሬቶች የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሼክ ታኑም ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ሁለቱ ሀገራትበደህንነት እና ፀጥታ ዙሪያ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች […]

አንድ የቻይና ከፍተኛ ዲፒሎማት በሁለቱ ኮሪያዎች ጉዳይ ለመምከር ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዙ ነው::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 አንድ የቻይና ከፍተኛ ዲፒሎማት በሁለቱ ኮሪያዎች ጉዳይ ለመምከር ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዙ ነው:: በሰሜን እና ደቡብ ኮሪያዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት ተሟሙቆ የነበረውን አዲስ ግንኙነት ጥላ አጥልቶበታል፡፡ ሁለቱ ሀገራት በድንበር አካባቢ ቀለል ያለ የተኩስ ልውውጥ እስከማድረግ ያደረሳቸው ግጭት ውስጥ መግባታቸው ሳያንስ ለሽምግልና በሮቻቸውን መዝጋታቸውም ስጋቱን ከፍ አድርጎታል፡፡ ከሴኡል […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ።

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ የዛሬ ዓመት ቃል የገባነውን ፈጽመን በተግባር አሳይተናል ብለዋል። በገበታ ለሀገር ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን እንዲያዋጡ የተዘጋጀውን የባንክ ሂሳብም ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህም የ10 ሚሊየን እና የ5 ሚሊየን ብር ገቢ ለማድረግ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ማንኛውም […]

ስምንተኛዉ የበጎ ሰዉ ሽልማት መርሃግብር ጳጉሜ 1 ሊካሄድ ነዉ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 ስምንተኛዉ የበጎ ሰዉ ሽልማት መርሃግብር ጳጉሜ 1 ሊካሄድ ነዉ፡፡ “በጎ ሰዎችን በማክበር እና እዉቅና በመስጠት ሌሎች በጎ ሰዎችን እናፈራለን” በሚል መረሃግብር በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን በአስር ዘርፎችም ለአገራቸዉ በሞያቸዉ የላቀ ተግባር ላበረከቱ ሰዎች ይበረከታል፡፡ የበጎ ሰዉ ሽልማት ድርጅት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ የዘንድሮ የሽልማት መርሀግብር ከየካቲት 1 አስከ መጋቢት 15 ከ200 በላይ […]

የማሊ ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ አዲስ ምርጫ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ እየሰጡ ነው::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 14፣ 2012  የማሊ ተቃዋሚዎች በሀገሪቱ አዲስ ምርጫ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ እየሰጡ ነው:: በማሊ መፈንቅለ መንግት መካሄዱን ተከትሎ አለመረጋጋት እንዳይፈጠር እና ህዝቡ ወደብጥብጥ እንዳይገባ ከፍተኛ ስጋት ተፈጥሯል፡፡ ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንት ቡበከር ኬታን እና ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን በቁጥጥር ስር ያደረገው የሀገሪቱ ጦር ሃይል ስጋት አይግባችሁ አዲስ ምርጫ ተካሂዶ ማሊ ወደ ቀድሞ ሰላሟ ትመለሳለች ብለዋል፡፡ ሲ ጂ ቲ […]

በካሊፎርኒያ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ሲያፈናቅል የአንድ ሰው ህይዎት ማለፉ ተሰምቷል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 14፣ 2012 በካሊፎርኒያ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ሲያፈናቅል የአንድ ሰው ህይዎት ማለፉ ተሰምቷል:: አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው በእሳት አደጋው ህይዎቱ ያለፈው ግለሰብ በስራ ላይ የተሰማራ የእሳት አገደጋ ሰራተኛ ነው፡፡ እሳቱ ከ20 ሺህ ሄክታር በላይ በሚሸፍን ቦታ ላይ ከፍተኛ ጥፋት ማድረሱን የግዛቲቱ ባለ ስልጣናት ተናግረዋል፡፡ የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪ ጋቪን ኒውሰም እንዲህ አይነት የከፋ […]

ባለፉት ስምንት ዓመታት በመላው ሀገሪቱ ከ130 ሺህ በላይ ሰዎች በተሸከርካሪ አደጋ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 15፣ 2012  ባለፉት ስምንት ዓመታት በመላው ሀገሪቱ ከ130 ሺህ በላይ ሰዎች በተሸከርካሪ አደጋ ጉዳት እንደደረሰባቸዉ ተገለፀ፡፡የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ለአርትስ በላከዉ መግለጫጉዳት ከደረሰባቸዉ ዉስጥም ካሳ የተከፈላቸው ቁጥር ከ 25ሺ እንደማይበልጥ ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የመንገድ ትራፊክ አደጋ በየዓመቱ ከ 4 ሺህ በላይ ሞትና ከ 15 ሺህ በላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም በንብረትም ከ1 ቢሊዮን […]

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በእስራኤል ኤምባሲዋን ልትከፍት ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 15፣ 2012 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በእስራኤል ኤምባሲዋን ልትከፍት ነው፡፡የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንዋር ጋርጋሽ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይት ወቅት በቴልአቪቭ ኤምባሲያችንን እንከፍታለን ማለታቸውን አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት ከእስራኤል ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታውሰው፤ በዓለም አቀፍ መርህ ሁለት ሀገራት ሊኖራቸው በሚገባው ግንኙነት መሰረት አቡዳቢ በቴላቪቭ ኤምባሲዋን ትከፍታለች ብለዋል፡፡ሚኒስትሩ […]