loading
በአዲስ አበባ አዋሬ ገበያ በደረሰ የእሣት አደጋ አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2013 በአዲስ አበባ አዋሬ ገበያ በደረሰ የእሣት አደጋ አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ ::በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተለምዶ አዋሬ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የእሣት አደጋ አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።የከተማ አስተዳደሩ የእሣትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ የእሣት አደጋው […]

ማላዊ በኢየሩሳሌም ኤምባሲዋን ልትከፍት መሆኑን ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2013 ማላዊ በኢየሩሳሌም ኤምባሲዋን ልትከፍት መሆኑን ይፋ አደረገች::በእስራኤል የስራ ጉብኝት ያደረጉት የማላዊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይዘን አወር ምካካ ውሳኔውን ግልፅና ጠቃሚ ብለውታል፡፡የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋቢ አሽኬናዚ በበኩላቸው የማላዊን ኤምባሲ በቅርቡ በእየሩሳሌም ከተማ ሲከፈት ማየት ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የሷን ፈለግ እንደሚኬተሉ ተስፋ አለኝ ብለዋል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘደበው አይዘን አወር […]

ቻይና በፈረንጆቹ 2025 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከሪዎችን ቁጥር በ20 በመቶ ለማሳደግ ማቀዷ ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2013 ቻይና በፈረንጆቹ 2025 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከሪዎችን ቁጥር በ20 በመቶ ለማሳደግ ማቀዷ ተነገረ፡፡ቻይና ታዳሽ ሃይል የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎችን በሚመለከት ከፈረምጆቹ 2021 እስከ 2035 ለመተግበር ያወጣችውን እቅድ ይፋ ያደረገች ሲሆን ይህም በዘርፉ እመርታን ለማምጣት በእጅጉ ይረዳታል ነው የተባለው፡፡ ሀገሪቱ በዘርፉ ያስቀመጠችው እቅድ የቴክኖሎጂና የፈጠራ አቅምን ማጎልበት፣ ከአከባቢ ብክለት ጋር የሚስማሙ ኢንዱስትሪዎች ማስፋፋትና ማልማትን […]

በሕዳሴ ግድቡ የሦስትዮሽ ድርድር የአፍሪካ ሕብረት ባለሞያዎች ሚና ከፍ ይበል በሚለው የኢትዮጵያ ሐሳብ ግብጽ ሳትስማማ መቅረቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 በሕዳሴ ግድቡ የሦስትዮሽ ድርድር የአፍሪካ ሕብረት ባለሞያዎች ሚና ከፍ ይበል በሚለው የኢትዮጵያ ሐሳብ ግብጽ ሳትስማማ መቅረቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ::በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች ሚና ከፍ ይበል በሚለዉ ዙሪያ ግብፅ እንዳልተስማማች የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሃሳቡ ላይ ሱዳን ስትስማማ ግብጽ ሳትቀበል መቅረቷን ነዉ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የገለጸዉ፡፡ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን ችግሮች […]

የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 የገጽ ለገጽ የመማር ማስተማር ሂደት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ከ8ኛና 12ኛ ክፍል ዉጪ በተቀሩ ክፍሎች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በኮቪድ19 የቀዉስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ እቅድ ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ሟሟላት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነዉ ፡፡ ከጥቅምት 30 ጀምሮ ይጀመራል የተባለዉ ትምህርት አስፈላጊ […]

በትግራይ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው ህግን የማስከበር ስራ በታቀደው መንገድ እየሄደ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2013 በትግራይ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው ህግን የማስከበር ስራ በታቀደው መንገድ እየሄደ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ ገለፁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ዘመቻው በክልሉ ተቀባይነት ያለው ህጋዊ አስተዳደር ሲመሰረት እንደሚጠናቀቅም አስታውቀዋል፡፡በተያያዘም የአገር መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ኤርፖርትን መቆጣጠሩ ተሰምቷል፡፡ የአገር መከላከያ ሰራዊት ህውሓት ከጠላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት የነበረውን የሁመራ ኤርፖርት […]

በኮትዲቯር ፕሬዚዳተታዊ ምርጫ ያሸነፉት አላሳኒ ኦታራ ለተቃዋሚዎች የውይይት ጥሪ አቀረቡ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2013 በኮትዲቯር ፕሬዚዳተታዊ ምርጫ ያሸነፉት አላሳኒ ኦታራ ለተቃዋሚዎች የውይይት ጥሪ አቀረቡ:: የሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ካውንስል በሰጠው ማረጋገጫ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ አገሪቱን መምራት የሚያስችል ድምፅ አግኝተዋል፡፡ የ78 ዓመቱ ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ በምርጫው 94 በመቶ የሚሆነውን የመራጮች ድምፅ አግኝተዋል ቢባልም ተቃዋሚዎች ውጤቱን አልተቀበሉትም፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ምርጫው ከጅምሩ ህገ መንግስታዊ ስላልሆነ […]

ጆ ባይደን ክትባት እስኪጀመር 200 ሺህ አሜሪካዊያን በኮሮናቫይረስ ሊሞቱ ይችላሉ ሲሉ አሰጠነቀቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2013 ጆ ባይደን ክትባት እስኪጀመር 200 ሺህ አሜሪካዊያን በኮሮናቫይረስ ሊሞቱ ይችላሉ ሲሉ አሰጠነቀቁ፡፡ አዲሱ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ይህን ያሉት አዲስ ከተቋቋመው የአሜሪካ የኮሮናቫይረስ አማካሪ ቦርድ ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡ ባይደን 90 በመቶ ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ ክትባት መኖሩን ከቦርዱ በተደረገላቸው ገለጻ መስማታቸውን እንደ መልካም ዜና ቢቆጥሩትም አሁንም ገና በርካታ ወራትን መጠበቅ ግድ ስለሚል […]

በአሜሪካ የጆ ባይደን መመረጥ በአፍሪካ ተስፋንም ጥርጣሬንም ይዞ መጥቷል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 02፣ 2013 በአሜሪካ የጆ ባይደን መመረጥ በአፍሪካ ተስፋንም ጥርጣሬንም ይዞ መጥቷል ተባለ፡፡ ጆ ባይደን አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ዋሽንግተን ከአፍሪካ ጋር ስለሚኖራት ግንኙነት ከወደዲሁ መላ መላ ምቶች ተበራክተዋል፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የባይደን ወደ ስልጣን መምጣት ለአህጉሪቱ ቀና አመለካት የላቸውም በሚባሉት ዶናልድ ትራምፕ ዘመን የሻከሩ ግንኙነቶች ይስተካከላሉ የሚል ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በተለይ […]

ክሬት በተባለችው የግሪክ ደሴት የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በንብረት ላይ ትልቅ ውድመት አደረሰ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 02፣ 2013 ክሬት በተባለችው የግሪክ ደሴት የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በንብረት ላይ ትልቅ ውድመት አደረሰ:: የደሴቷ ባለ ስልጣናት እንዳሉት የመንገድ አውታሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በአደጋው ወድመዋል፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ጎርፉ በርካታ ቤቶችን ከማጥለቅለቁ በሻገር ተሸከርካሪዎችን ወደ በባህር ሲወስዳቸው ታይቷል፡፡ ጎርፉ በርካታ የመሰረተ ልማቶች ላይ ከባድ ጉዳት ቢያደርስም እስካሁን በሰው ህይዎት ላይ የደረሰ […]