loading
በናይጄሪያ በደረሰ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ደርሷል ተባለ ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 በናይጄሪያ በደረሰ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ደርሷል ተባለ :: በአህመድ ላዋን የተመራው የናይጄሪያ ሴኔት ልዑክ፤ በሳምንቱ መጨረሻ በገበሬዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት፤ የሰሜን ምስራቅ ቦርኖ ጉብኝት አድርጓል ፡፡ በተፈፀመው ጥቃት 43 አርሶ አደሮች መገደላቸው የተዘገበ ሲሆን ከአከባቢው ባለሥልጣናት ተሻሽለው እየወጡ ያሉ አኃዛዊ መረጃዎች የሟቾች ቁጥር ወደ […]

የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት አዲስ የጥምር ፓርቲ ለመመሰረት መወሰናቸውን ይፋ አደረጉ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት አዲስ የጥምር ፓርቲ ለመመሰረት መወሰናቸውን ይፋ አደረጉ:: ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ይህን ያሉት በሳቸውና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ፓርቲዎች መካከል አለመግበባት በመፈጠሩ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በፓርላማው ብዙ መቀመጫ ያላቸው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ካቢላ ደጋፊዎችና ሀገሪቱን በመንግስትነት የሚያስተዳድረው የሺሴኬዲ ፓርቲ ፖለቲካዊ ልዩነታቸውን ማስታረቅ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ […]

የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል በወንጀል የሚፈለጉትን ሰዎች ለሕግ ለማቅረብ እየሰራ መሀኑን የ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽቤት አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል በወንጀል የሚፈለጉትን ሰዎች ለሕግ ለማቅረብ እየሰራ መሀኑን የ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽቤት አስታወቀ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረው የሕግ ማስከበር ዋናኛ ምዕራፍ መጠናቀቁን ገልጾ፣ የፌዴራል መንግስት በክልሉ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን ለሕግ ለማቅረብ፣ እንዲሁም በአከባቢው ሕግና ስርዓት እንዲኖር እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ […]

ለሕገ ወጥ ስደትና ለጎዳና ኑሮ የሚዳረጉ ህጻናትን ለመታደግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ሚኒስቴሩ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 ለሕገ ወጥ ስደትና ለጎዳና ኑሮ የሚዳረጉ ህጻናትን ለመታደግ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ሚኒስቴሩ አስታወቀ፡፡ የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በሕገ ወጥ የሕፃናት ዝውውር ላይ ያተኮረ የባለ ድርሻ አካላት ውይይት ተካሄዷል። በርካታ ሕፃናት በመማሪያ እድሜያቸዉ ለሕገ-ወጥ ስደት የሚዳረጉ ሲሆን በሀገራችን በተለያዩ ከተሞች ሕፃናት ውሎና አዳራቸውን […]

የዩኒቨርቲዎች ስትራቴጂክ ዕቅድ ግምገማ መድርክ እየተካሄደ ነው::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 የዩኒቨርቲዎች ስትራቴጂክ ዕቅድ ግምገማ መድርክ እየተካሄደ ነው:: የዩኒቨርቲዎች ስትራቴጂክ ዕቅድ ግምገማ መድርክ እየተካሄደ እንደሚገኝ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቀ፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እንደገለጹት፣የትምህርት ስርዓታችንን በተለመደው መልኩ የምንመራው ሳይሆን ብቁና ጥራት ያለው ዜጋ ለማፍራት በስትራቴጂክ ዕቅዳችን በማካተት የትምህርት ተቋማት በግልጽ ማቀድና መተግበር ይኖርባቸዋል፡፡ በሀገር ደረጃ በተዘጋጀው […]

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በኃይል ገመድና ኬብል ስርቆት መቸገሩን አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በኃይል ገመድና ኬብል ስርቆት መቸገሩን አስታወቀ:: የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት የኃይል ገመዶች እና ኬብሎች ስርቆት ሳቢያ ተገልጋዮቹ መንገላታታቸውና ኮርፖሬሽኑም ለተደጋጋሚ ኪሳራ መዳረጉን ገለጿል። የአገልግሎቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሙሉቀን አሰፋ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ፣የኃይል ገመዶች እና ኬብሎች በሌቦች ተቆርጠው በመወሰዳቸው ምክንያት ሰሞኑን […]

የኒውዚ ላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደርን በክሪስት ቸርች የጅምላ ግድያ ህዝባችውን ይቅርታ ጠየቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 የኒውዚ ላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደርን በክሪስት ቸርች የጅምላ ግድያ ህዝባችውን ይቅርታ ጠየቁ:: ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይቅርታ የጠየቁት ብሪንተን ታራንት የተባለው ትውልደ አውስትራሊያዊ ወጣት ያደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ ከጦር መሳሪያ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ስህተት ነበር በማለት ነው፡፡ የሀገሪቱ የወንጀል መርማሪ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ፖሊስ ግለሰቡ የጦር መሳሪያ ፈቃድ ሲሰጠው አስፈላጊውን ማጣራት […]

ሶማሊያ ለኬንያ ዜጎች ፈቅዳው የነበረውን የጉዞ መዳረሻ ቪዛ መከልከሏን ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 ሶማሊያ ለኬንያ ዜጎች ፈቅዳው የነበረውን የጉዞ መዳረሻ ቪዛ መከልከሏን ይፋ አደረገች:: በሁለቱ ሀገራት መካከል በቅርቡ የጠፈጠረው የዲፕሎማሲ መሻከር ነወ ሶማሊያን ለዚህ ወሳኔ ያነሳሳት ተብሏል፡፡ የሶማሊያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ባለስልጣን መስሪያቤት ከዚህ በኋላ ወደ ሶማሊያ የሚጓዙ ኬንያዊያን አስቀድመው ቪዛ ማስመታት ይጠበቅባቸዋል ብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የዲፕሎማሲ ጉዙ የሚያደርጉ ግለሰቦች ሳይቀሩ ከሶማሊያ […]

የትግራይ ክልል ወደቀደመው መረጋጋትና ሰላም እየተመለሰ መሆኑ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013  የትግራይ ክልል ወደቀደመ ሰላሙና መረጋጋት እየተመለሰ መሆኑን የትግራይ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል አስታወቁ:: በክልሉ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ብር መመደቡን ገለጸዋል፡፡ አቶ ነብዩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በህወሓት ቡድን ወደ አለመረጋጋት ገብቶ የነበረው የትግራይ ክልል አሁን ላይ ወደቀደመ ሰላምና መረጋጋቱ እየተመለሰ […]

አመንስቲ ኢንተርናሽናል አረጋዊያንን ከሽብርተኞች ጥቃት መጠበቅ ይገባል የሚል ጥሪ አቀረበ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013  በተለያዩ ሀገራት የሚደርሱ የሽብር ጥቃቶች በእድሜ የገፉ አረጋዊያን ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ነው ያለው ተቋሙ፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በተለይ እንደ ናይጄሪያ፣ ማሊ፣ እንዲሁም በአብዛኛው የመካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ችግሩ ከፋ ነው፡፡ የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ገና ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት የሚያደርሰውን ቦኩ ሃራምን […]