loading
የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል ዘርፉን በእውቀት መምራት ያስፈልጋል- ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22፣ 2013 የፍርድ አፈፃፀም መጓተት ችግሮችን ለመፍታት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር መተግበር ይገባል ተባለ፡፡ የፌዴራል የፍትህ የህግ ምርምር እና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ አውደ-ጥናት አካሂዷል። በአውደ-ጥናቱ ላይ  ከፍርድ አፈፃፀም ጋር ያሉ ችግሮች፣ ከአዕምሮ ጤና ህግ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንዲሁም ባህላዊ የግጭት አፈታት ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል። የፌዴራል ጠቅላይ […]

የመሪያቸው ሸንቃጣነት ያሳሰባቸው ሰሜን ኮሪያዊያን…

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22፣ 2013 ሰሜን ኮሪያዊያን የመሪያቸውን ክብደት መቀነስ ከጤናቸው ሁኔታ ጋር አያይዘው ሀሳብ ገብቷቸዋል ተባለ፡፡ ለወትሮው በሰፋፊ ልብሶቻቸው ፈርጠም ባለ ሰውነታቸው የሚታወቁት ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሸንቀጥ ብለው ታይተዋል ነው የተባለው፡፡ ይህ ደግሞ ለሰሜን ኮሪያዊያን እንደ መልካም ዜና እንደማይቆጠር መገናኛ ብዙሃን በስፋት እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡ የሀገሪቱ ቴሌቭዥን ጣቢያ በሳምንቱ መጨረሻ […]

ቶጎ በምዕራብ አፍሪካ ግዙፍ የተባለውን የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22፣ 2013 ከዋና ከተማዋ ቶጎ በደቡባዊ አቅጣጫ 250 ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝው ይህን ፕሮጀክት የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ ፕሮጀክቱ 158 ሺህ የሚሆኑ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን በቀጣይ ለማዳረስ ዕቅድ ተይዞለታል ነው የተባለው፡፡ በአቡዳቢው ልኡል ሼክ ሙሃመድ ቢን ዛይድ የተሰየመው ይህ ፕሮጀከት 64 ነጥብ 7 ሚሊዮን […]

ትግራይ ውስጥ ለሚከሰት ችግር መንግስት ተጠያቂ አይደለም አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23፣ 2013 ከዚህ በኋላ ትግራይ ለሚከሰት ችግር የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ አይሆንም ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለፁ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና መከላከያ ሰራዊት በጋራ በሰጡት መግለጫ “ከዚህ በኋላ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሚከሰት ችግር የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ” እንደማይሆን አስታውቀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዴኤታው ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በሰጡት መግለጫ የፌዴራል መንግስት ከዚህ በኋላ በትግራይ […]

ሶማሊያ በጥቅምት ወር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ አቅዳለች ተባለ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23፣ 2013 ሶማሊያ በጥቅምት ወር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ አቅዳለች ተባለ፡፡ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ የፖለቲካ መሪዎች የዘገየውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጥቅምት 10 ለማካሄድ መስማማታቸውን አስታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮቤል በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ የተካሄደውን የሁለት ቀናት ውይይት ተከትሎ ባለድርሻ አካላት በውክልና የሚካሄደውን የፓርላማ እና […]

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013  በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮቪድ -19 ምክንያት የሞት መጠን አልተመዘገበም ተባለ፡፡ የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓትን ሪፖርት ባወጣዉ መረጃ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከረጅም ግዜ በኋላ በኮቪድ- 19 ምክንያት ሞት ያልተመዘገበበት ቀን ሆኗዋል፡፡ በ24 ሰዓቱ በተደረገ 4 ሺህ 974 የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በጽኑ የታመሙ 145 ሰዎች ሲሆኑ ከበሽታዉ ያገገሙ […]

የአገዛዝ እንጂ የፖሊሲ ለዉጥ አንፈልግም -ሱዳናዊያን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013  በሱዳን የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመፅ መንግስት ይቀየር ወደሚል አጀንዳ መሸጋገሩ ተሰማ፡፡ ሱዳን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ምክረ ሀሳብን ተቀብላ ተግባራዊ ያደረገችው የኢኮኖሚ መሻሻያ የፈጠረው የዋጋ ንረት ነው በሀገሪቱ ህዝባዊ አመፅ የቀሰቀሰው ተብሏል በተለያዩ የሱዳን ከተሞች በርካታ ሰዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስልጣኑን ይልቀቅ የሚል መፈክር ይዘው ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል ነው የተባለው፡፡ አጃንስ […]

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013 በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም:: በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮቪድ -19 ምክንያት የሞት መጠን አልተመዘገበም ተባለ፡፡ የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓትን ሪፖርት ባወጣዉ መረጃ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከረጅም ግዜ በኋላ በኮቪድ- 19 ምክንያት ሞት ያልተመዘገበበት ቀን ሆኗዋል፡፡ በ24 ሰዓቱ በተደረገ 4 ሺህ 974 የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች […]

እስካሁን የምርጫ ውጤት ተጠቃልሎ አልደረሰኝም-ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013  በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን የሁሉንም ምርጫ ክልሎች ውጤት ይፋ ማድረግ አለመቻሉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ። እስካሁን ባለው ሂደት ምርጫ ከተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች የ26ቱ ውጤት አለመድረሱን ቦርዱ አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ፤ በድምር መዘግየት፣ በትራንስፖርት ችግር እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ምክንያት የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ማዕከል ተጠቃሎ አልደረሰም ብለዋል። […]

ህንድ በ39 ቀናት 100 ሺህ ዜጎቿን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ አጣች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013  በህንድ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ400 ሺህ በላይ ሲያሻቅብ ከዚህም ግማሽ ያህሉ ሞት በሁለተኛው ዙር ወረርሽኝ የተከሰተ ነው ተባለ፡፡ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ የተመታችው ህንድ እስካሁን ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ መጠቃታቸውን ይፋ አድርጋለች፡፡ በህንድ 400 ሺህ 312 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ህይዎታቸውን ሲያጡ ከነዚህ መካከል 100 ሺህ የሚሆኑት የሞቱት በ39 ቀናት […]