loading
ዛሬ በልደታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ የአራት ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡

ዛሬ በልደታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረቡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ የአራት ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን በመደገፍ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ የተደረገው ሰልፍ ላይ ከፈነዳው ቦምብ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ላይ ፍ/ቤቱ የተጠየቀውን ጊዜ ቀጠሮ ተቀብሏል፡፡

መሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ን የምትደብቁ ተጠንቀቁ ተብላችኋል፡፡

መሰረታዊ የንግድ ሸቀጦች ን የምትደብቁ ተጠንቀቁ ተብላችኋል፡፡ ይህንን ያላችሁ የኢፌድሪ የንግድ ሚኒስቴር ነዉ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በላከልን መግለጫ ስንዴ ፣ስኳርና ፓልም ዘይት በመንግስት ድጎማ ወደሀገር ዉስጥ እየገባ ቢሆንም ፤ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ባደረገዉ አሰሳና በህዝብ ጥቆማ መሰረታዊ ሸቀጦቹ እየተደበቁ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡ ሚኒስቴሩም መሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ህገወጥ ድርጊቶችን የምትፈጽሙ አካላት ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ ካልሆነ የሸማቹን […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ሁለቱም ፓትርያርኮች በእኩል የአባትነት ክብር እንዲያገለግሉ ተወሰነ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ሁለቱም ፓትርያርኮች በእኩል የአባትነት ክብር እንዲያገለግሉ ተወሰነ። ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየውን የሰላምና የእርቅ ጉባዔው ተከትሎ የተወሰኑ ውሳኔዎች ይፋ ሆነዋል። በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአንድ የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር እንድተመራ የተወሰነ ሲሆን፥ በሁለቱም ሲኖዶሶች የተላለፈው ቃለ ውግዘት በጋራ ምልዓተ ጉባኤ ይፈታል ተብሏል። የሁለቱም ቅዱሳን ፓትርያርኮች ስም ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ዓለም […]

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዐተ ጉባዔ በዛሬዉ ዕለት በውጭ በሚገኘው ሲኖዶስ ላይ አሳልፏቸዉ የነበሩ ውግዘቶችን እንደሚያነሳ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዐተ ጉባዔ በዛሬዉ ዕለት በውጭ በሚገኘው ሲኖዶስ ላይ አሳልፏቸዉ የነበሩ ውግዘቶችን እንደሚያነሳ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ሀገር ውስጥ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ በ1984፣ 1985 እና በ1999 ዓመተ ምህረቶች አሜሪካ በሚገኘው ሲኖዶስ ላይ አሳልፏቸው የነበሩ ውግዘቶችን በቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዐተ ጉባዔ ዛሬ እንደሚያነሳ ተናግሯል። በመግለጫው፥ በመጪው ረቡዕ ወደ ሀገር ቤት […]

የባንኮች አጠቃላይ ሀብት አንድ ትሪሊዮን ብር ደረሰ::

የግል ባንኮች ብድር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰጠው መብለጡም ተሰምቷል፡፡ ሪፖርተር እንደዘገበዉ የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዥና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ ጉዳዮች አማካሪና የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባል አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ እንደገለጹት፣ አሥራ ስምንቱ የአገሪቱ የግልና የመንግሥት ባንኮች በ2010 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ያስመዘገቡት የሀብት መጠን አንድ ትሪሊዮን ብር ሊደርስ የቻለው በ2002 ዓ.ም. ከነበረበት 167 ቢሊዮን ብር ተነስቶ […]

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ከዳሸን ቢራ ቦርድ አባልነት ተሰናበቱ

የዳሸን ቢራ ፋብሪካ የቦርድ አባል የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ታደሰ ካሳና አቶ ወንድወሰን ከበደ ከቦርድ አባልነት መሰናበታቸውን ዳሽን ቢራ አክሲዮን ማህበር ለአርትስ ቲቪ በላከዉ መግለጫ አረጋግጧል፡፡ መግለጫው ተሰናባቾቹን የቦርድ አባላት የተኩት አዳዲሶቹ አባላትን አሳዉቋል፡፡ አባላቱም የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ አብተው፣ በቅርቡ የብሔራዊ ባንክ ገዥ የሆኑት ዶክተር ይናገር ደሴ እና የጥረት […]

በፒያሳ የሚገኘዉ የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ሀውልት እድሳት ተጠናቀቀ::

ለስድስት ወራት በእድሳት ምክንያት ተሸፍኖ የቆየዉ ሀዉልትም በሚቀጥለዉ ሳምንት ለህዝብ ይፋ ይሆናል ተብሏል፡፡ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር አቶ ወርቁ መንገሻ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት የቅርስ እድሳቱ ከሴባስቶፖል መድፍ ጋር 5 ሚሊዮን ብር ፈጅቷል ፡፡ ዳይሬክተሩ ለሃውልቱ እድሳት የተያዘለት የዘጠኝ ወር ግዜ ቢሆንም ቀድሞ በስድስት ወር ጊዜ ዉስጥ እድሳቱ እንደተጠናቀቀ ተናግረዋል፡፡ እድሳቱ በአዲስ […]

የአራት ማረሚያ ቤቶች አስተዳዳሪዎች ከሃላፊነታቸው ተነሱ፡፡

ከሃላፊነታቸው የተነሱት የቂሊንጦ ፤ የቃሊቲ፤ የሸዋ ሮቢት እና የድሬዳዋ ማረሚያቤቶች አስተዳዳሪዎች መሆናቸዉን አርትስ ቲቪ ለማወቅ ችሏል፡፡ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ረዳት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አዲሱ ጴጥሮስ ለ አርትስ እንደለፁት፤ በቅርቡ ታራሚዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ የሠብዓዊ መብት ጥሠት እንደሚፈፀምባቸው በመናገራቸዉ እና ማረሚያ ቤቱም አስተዳዳሪዎቹ ጋር ችግር እንዳለ በማረጋገጡ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ የቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ […]

ኤርትራና ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል ተስማሙ ፡፡

ሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል የተስማሙት ከ15 አመታት በኋላ መሆኑን ኤርቲሪያን ፕረስ ዘግቧል፡፡ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዘዳንት መሃመድ ፋርማጆን ኤምባሲያቸውን ለመክፈትና አምባሳደር ለመሾም ተስማምተዋል፡፡ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ቀጠናዊ ግንኙነትን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ የሶማሊያው ፕሬዘዳንት መሃመድ ፋርማጆን በበኩላቸው በሁለቱም ሃገራት ዋና ከተሞች በቅርቡ ኢምባሲዎቻችንን ጠብቁ ብለዋል፡፡