loading
ሶማሊያ በጥቅምት ወር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ አቅዳለች ተባለ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23፣ 2013 ሶማሊያ በጥቅምት ወር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለማድረግ አቅዳለች ተባለ፡፡ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ የፖለቲካ መሪዎች የዘገየውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጥቅምት 10 ለማካሄድ መስማማታቸውን አስታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮቤል በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ የተካሄደውን የሁለት ቀናት ውይይት ተከትሎ ባለድርሻ አካላት በውክልና የሚካሄደውን የፓርላማ እና […]

የአገዛዝ እንጂ የፖሊሲ ለዉጥ አንፈልግም -ሱዳናዊያን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013  በሱዳን የተቀሰቀሰው ህዝባዊ አመፅ መንግስት ይቀየር ወደሚል አጀንዳ መሸጋገሩ ተሰማ፡፡ ሱዳን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ምክረ ሀሳብን ተቀብላ ተግባራዊ ያደረገችው የኢኮኖሚ መሻሻያ የፈጠረው የዋጋ ንረት ነው በሀገሪቱ ህዝባዊ አመፅ የቀሰቀሰው ተብሏል በተለያዩ የሱዳን ከተሞች በርካታ ሰዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስልጣኑን ይልቀቅ የሚል መፈክር ይዘው ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል ነው የተባለው፡፡ አጃንስ […]

ካይሮ የግድቡ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት መጀመሩን የሚገልፅ ደብዳቤ ከአዲስ አበባ ደርሶኛል አለች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29፣ 2013 ካይሮ የግድቡ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት መጀመሩን የሚገልፅ ደብዳቤ ከአዲስ አበባ ደርሶኛል አለች፡፡ የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ሞሀመድ አብደል አቲ የኢትዮጵያው የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ኢንጂኔር ስለሺ በቀለ በላኩልኝ ይፋዊ ደብዳቤ ሀገራቸው በተናጠል ውሳኔዋ ፀንታ ሁለተኛውን ዙር ሙሌት መጀመሯን አረጋግጠውልኛል ብለዋል፡፡ አብደል አቲ ለኢንጂኔር ስለሺ በጻፉት የመልስ ደብዳቤ ግብፅ የኢትዮጵያን […]

የፀጥታው ምክር ቤት በህዳሴው ግድብ ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነት የለውም-የናይል ተፋሰስ ሀገራት

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013  የፀጥታው ምክር ቤት በህዳሴው ግድብ ውሳኔ የመስጠት ኃላፊነት የለውም-የናይል ተፋሰስ ሀገራት የናይል ተፋሰስ ሀገራት በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት የሚደረገው የግድቡ ድርድር ሂደት ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ትክከለኛው መንገድ መሆኑን ገለጹ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ድርድሩ ያለበትን ደረጃ በሚመለከት በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተፋሰሱ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ገለፃ አድርገዋል፡፡ […]

ዙማ ከፖሊስ ጋር ድብብቆሽ በቃኝ አሉ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2013 የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮቭ ዙማ ለፖሊስ እጃቸውን መስጠታቸው ተሰማ፡፡ የተመሰረተባቸውን የሙስና ክስ ችሎት ቀርበው እንዲያስረዱ የሀገሪቱ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ባለማክበር የ15 ወራት እስር የተፈረደባቸው ዙማ ቅጣቱ እንዲቀርላቸው አቤት ብለው ነበር፡፡ የተወሰነባቸውን ቅጣት እንዲፈፅሙ ሲጠየቁ አሻፈረኝ ብለው የነበሩት ፕሬዚዳንቱ ፖሊስ በሃይል ይዞ ወደ አስር ቤት ሊወስዳቸው በሚዘጋጅበት በገዛ […]

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው በአበይት ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና የዜጋ ዲፕሎማሲ ክንውኖችን ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው በአበይት ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና የዜጋ ዲፕሎማሲ ክንውኖችን ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡ ትናንት በመንግሥታቱ የድርጅት ፀጥታ ምክር ቤት የቀረበው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የሶስትዮሽ ድርድሩ ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ የሚል ሀሳብ መቅረቡ ትልቅ ዲፕሎማሲ ስኬት ነው ብለዋል። ቋሚ አባላትም ሁሉም በሚባል […]

ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ግልፅ መርህ አስቀምጣ እየተጓዘች ነው-ኢንጅኔር ስለሺ በቀለ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ ግልፅ መርህ አስቀምጣ እየተጓዘች ነው-ኢንጅኔር ስለሺ በቀለ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ማብራርያ ሰጡ፡፡ ሚኒስትሩ ለዋና ጸሐፊው ግንባታው ስላለበት ሁኔታ፣ ስለሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ስለሚካሄደው ድርድር ተገቢውን ማብራሪያ ሰጥተዋል ። […]

ግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት አባላት ላይ የዕድሜ ልክ እስራ  ውሳኔ አስተላለፈች፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6፣ 2013 ግብፅ የሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት አባላት ላይ የዕድሜ ልክ እስራ  ውሳኔ አስተላለፈች፡፡ የሀገሪቱ ከፍተኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት የፖሊስ አባላትን በመግደልና እስር ቤት ሰብረው እስረኞችን በማስመለጥ ወንጀል በተከሰሱ የህብረቱን መሪ ሞሐመድ ባዴን ጨምሮ በ10 ግለሰቦች ላይ ነው ወሳኔውን ያሳለፈው፡፡ ተከሳሾቹ እንደ አውሮፓያኑ አቆጣጠር በ2011 በግብፅ በተቀሰቀሰው አብዮት 20 ሺህ የሚሆኑ እስርኞችን እንዲያመልጡ […]

በትግራይ ኤርትራዊያን ስደተኞች ደህንነታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8፣ 2013 በትግራይ ኤርትራዊያን ስደተኞች ደህንነታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ:: አሸባሪው ህወሓት ስደተኞች በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ጥቃቶች መክፈቱን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ኤጀንሲው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባለከው መግለጫ እንደገለጸው፤ ህወሓት የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ውድቅ አድርጎ ስደተኞች ላይ ጥቃት እየፈጸመ ነው። በዚህ የህወሓት ጥቃት ምክንያት በማይ-ዓይኒ እና በአዲ-ሐሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች […]

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቀቀ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12፣ 2013 የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቀቀ::ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ መጀመሩ ተነግሯል ዛሬ ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ መጀመሩን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው ላይ ውሃው በግድቡ […]