የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2010 በጀት አመት ከ89 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘሁ አለ፡፡
ገቢዉ ካለፈዉ አመት ጋር ሲነጻጸር የ1/4ኛ አድገት ማሳየቱንና፤ የተጣራ 6.8 ቢሊዮን ብር ማትረፉንም ተናግሯል፡፡ ዛሬ አየር መንገዱ የዘንድሮውን አመት እቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ባቀረበዉ ሪፖርት እንደጠቆመዉ በዚህ ዓመት በአፍሪካ ሀገራት የነበረዉን አለመረጋጋት፣የንግድ ጦርነት ፣የነዳጅ ዋጋ መጨመር ችግር የነበረ ሲሆን፤ከአየር መንገዱ አጠቃላይ ወጪ 40 በመቶ የሚሆነዉ ለነዳጅ ወጪ ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ […]